የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ መላው የኦሮምያ ክልል የበላይና ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ከነገ ጅምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ለሚቆይ ግምገማ አዳማ በሚዘጋጀው ክልል አቀፍ የካድሬዎች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ታዘዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኙ የኦህደዴ አባላት ከሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባን ለቀው ወጥተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የኦሮምያ አካባቢዎች በክልሉ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በአጋዚ ወታደሮችና በፖሊስ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኑ ይታወቃል፡፡
የግምገማው አላማ በክልሉ ጸጥታ እና ከስልጣናት በተነሱት አመራሮች ዙሪያ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
የግምገማው አላማ በክልሉ ጸጥታ እና ከስልጣናት በተነሱት አመራሮች ዙሪያ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
No comments:
Post a Comment