የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንሶ ህዝብ ያቀረበው የአስተዳደር ጥያቄ ለበርካቶች መታሰር ምክንያት ከሆነ በሁዋላ፣ የክልሉ ርእሰ ብሄር ቦታው ድረስ በመሄድ ህዝቡን አነጋግረው መፍትሄ እንደሚሰጡ ቃል ከገቡ በሁዋላ፣ የወረዳው አመራሮች እርስ በርስ እየተጣሉና እየተካሰሱ ሲሆን፣የታሰሩ መኖራቸውም ታውቋል።አመራሮቹ “በህዝብ የተረገመና ያልተረገመ “በሚል በሁለት ተከፍለው አንደኛው በሌላኛው ላይ ክስ ከማሰማት አልፎ፣ የህዝብ ወገን ናቸው የተባሉ አመራሮች ታስረዋል።
ባለፈው ቅዳሜ የካቲት 19፣ 2008 ዓም የወረዳው የአመራር አባላት ወደ አርባምንጭ በክልሉና በዞን አመራሮች ከተጠሩ በሁዋላ “ህዝብ ያልረገማቸው” ወይም የህዝብ ወገን ናቸው የተባሉት የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ ሌሎች 5 አመራሮች እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ሌሎች ህዝብ ወክሎአቸው ጥያቄውን ሲያቀርቡ የነበሩ 12 ግለሰቦችን ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመሩንም የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ።
ሌሎች ህዝብ ወክሎአቸው ጥያቄውን ሲያቀርቡ የነበሩ 12 ግለሰቦችን ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመሩንም የአካባቢው ምንጮች ይገልጻሉ።
No comments:
Post a Comment