Tuesday, December 5, 2017

በጂንካ ሃና ሙርሲ መስመር በርካታ ሹፌሮች ተገደሉ

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት አንድ የሙርሲ ተወላጅ በመኪና መገጨቱን ተከትሎ፣ የሙርሲ ተወላጆች ወደ አካባቢው ለስራ በሚንቀሳቀሱ ሹፌሮች ላይ በወሰዱት ጥቃት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ለኢሳት በደረሰው መረጃ 24 ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ከ13 ያላነሱት ህይወታቸው ማለፉን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። 
ጥቃቱን ተከትሎ ከ ጅማ ወደ ሙርሲ የሚወስደው መስመር ተዘግቷል። የኦሞ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞችም በተፈጠረው ሁኔታ በመደናገጣቸው ስራ አቁመዋል። 
ሙርሲውን የገደለው አሽከርካሪ ወደ ጅንካ በመሄድ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል። 
አንዳንድ ሰዎች ከተገደሉት መካከል የኦሞ ስኳር ፋብሪካ እና የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ሹፌሮች እንደሚገኙበት ለኢሳት ገልጸዋል።
ኢሳት የጉዳቱን መጠን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃዎችን በመሰብሰብ ላይ ነው።

No comments:

Post a Comment