የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በዋናው ወይኒ ቤት የተነሳውን ቃጠሎ ተከትሎ፣ በእስረኞችና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት በርካታ እስረኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል። እስረኞቹ ቃጠሎው እንደተጀመረ እንዲወጡ እንዲፈቀድላቸው ቢለምኑም፣ ፖሊሶቹ በጠመንጃ በማስፈራራት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ከድሬደዋ የተነሱ የእሳት አደጋ መኪኖች ወደ እስር ቤቱ ለመግባት ሲሞክሩ እስረኞች ተቃውሞአቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ጥሪ የተደረገላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ግቢው በመግባት በመቶዎች የሚቀጠሩ እስረኞችን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ የደበደቡዋቸው ሲሆን፣ እስረኞቹም ህይወት ፋና ሆስፒታልና ጀጉላ ሆስፒታል መግባታቸው ታውቛል።
እስካሁን ባለው መረጃ 50 የሚሆኑ እሰረኞች በቃጠሎው ጉዳት ሲደርስባቸው አንድ እስረኛ ህይወቱ አልፏል።
ቃጠለው በምን ምክንያት እንደተነሳ የታወቀ ነገር የለም።
እስካሁን ባለው መረጃ 50 የሚሆኑ እሰረኞች በቃጠሎው ጉዳት ሲደርስባቸው አንድ እስረኛ ህይወቱ አልፏል።
ቃጠለው በምን ምክንያት እንደተነሳ የታወቀ ነገር የለም።
No comments:
Post a Comment