የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በፈርጆች አቆጣጠር ከ5 ቀናት በፊት በለደወይን በሚባለው የሶማሊያ ግዛት ውስጥ 17 ወታደሮች ማንነታቸው ባልታወቁ ሃይሎች ተገድለዋል። የተወኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችም ተቃጥለዋል። ጥቃቱን ያደረሱት ሃይሎች የኢትዮጵያን ጦር ዩኒፎርም የለበሱ እና አማርኛ የሚናገሩ ናቸው።
በቅርቡም ሃርትሸክ ላይ በሶማሊ ልዩ ሃይል ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። ይህ ማንነቱ ያልታወቀ ቡድን ላለፉት 8 ወራት በአካባቢው እየተንቀሳቀሰ በኢትዮጵያ ጦር ላይ ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱን ምንጮች ይገልጻሉ።
ጥቃቱ መፈጸሙን በተመለከተ በአገዛዙ በኩል ምንም መግለጫ አልተሰጠም። ነገር ግን የሶማሊ ልዩ ሃይልም ሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ይህን ማንነቱ ያልታወቀ ሃይል ለማደን ተደጋጋገሚ ሙከራዎችን ቢያደርጉም እስካሁን እንዳልተሳካላቸው ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

No comments:
Post a Comment