ኢትዮጵያዊቷ የማራቶን ሯጭ አትሌት ዝናሽ ገዝሙ ማክሰኞ እለት በፓሪስ ከተማ ሉርሊይሱር ማርኔ በሚባለው አካባቢ በመኖሪያ ቤትዋ አፓርትመን ውስጥ ተገላ መገኘትዋን የፈረንሳይ ፖሊስ አስታውቋል።
እንደ ፖሊስ መረጃ የ27 ዓመቷ ወጣት አትሌት ዝናሽ ገዝሙ በ28 ዓመቱ የምስራቅ አፍሪካ ስደተኛ ሳትገደል አትቀርም ሲል ፖሊስ ገልጾ ተጠርጣሪውን በፓሪስ እስር ቤት በቁጥጥር ስር አውሎታል።
የአትሌቷ ጎረቤቶች ከመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ጩኧት መስማታቸውን ለፖሊስ ገልጸዋል። ''ሁሌም ግንኙነት መጀመርዋንና ቤተሰብ መመስረት እንደምትፈልግ ትነግረኛለች። ነገርግን ከማን ጋር እንደሆነ የማውቀው ነገር የለም።'' ሲል አንድ ጎረቤቷ ምስክርነቱን ሰጥቷል።
ሌላው ኒኮላስ ቫላት የተባሉ ፐርሺያዊ የቀድሞ ተወዳዳሪ በበኩላቸው ''ጧትና ማታ በባቡር ተሳፍራ ወደ ጽዳት ሥራዋ ስትሄድ አውቃታለሁ። እንደ እሷ ዓይነት ታታሪ ሰው አላውቅም።'' በማለት የአትሌቷን ጠንካራ ሰራተኝነት ተናግሯል።
አትሌት ዝናሽ በ2011 እ.ኤ.አ. ከአገሯ ኢትዮጵያ ተሰዳ ፈረንሳይ ውስጥ መኖር የጀመረች ሲሆን የመጨረሻ ውድድሯን በሆላንድ አምስተርዳም ከተማ በማድረግ በ2 ሰዓት ከ32 ደቂቃ በሆነ ጊዜ ውድድሩን አጠናቃለች።
በአትሌት ዝናሽ ገዝሙ አስከሬ ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው።
No comments:
Post a Comment