Tuesday, December 26, 2017

በአርባምንጭ ከተማ ፖሊሶች እስከ ጦር መሳሪያቸው መጥፋታቸው ታወቀ

የአካባቢው የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት በቅርቡ የኡራኤል በአል ሲከበር ለጥበቃ ከተላኩ ፖሊሶች መካከል የተወሰኑ ፖሊሶች ሙሉ ትጥቃቸውን ይዘው ጠፍተዋል። በበአሉ ላይ ከሰንደቃላማ ጋር በተያያዘ መጠነኛ የሆነ አለመግባባት በህዝቡ እና በፖሊሶች መካከል ተፈጥሮ ነበር። ህዝቡ “ አንመካም በጉልበታችንን” የሚል ዝማሪ እያሰማ ታቦቱን አጅቦ መጓዙን የሚገልጹት ምንጮች፣ ግጭት ይፈጠራል ተብሎ ቢፈራም ዝግጅቱ በሰላም መጠናቀቅ ችሎአል። በዝግጅቱ ላይ ከነበሩ ፖሊሶች መካከል የተወሰኑ ፖሊሶች ወደ ጽ/ቤታቸው ተመልሰው ሪፖርት አለማድረጋቸውንና ጠፍተዋል ተብሎ እምነት መያዙን ምንጮች ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በርካታ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታሰራቸው ታውቋል። በቅርቡ የተማሪዎችን አመራሮች ለመምረጥ በተደረገ ስብሰባ ላይ ተማሪዎች የተለያዩ ሃሳቦችን በመያዛቸው ለመስማማት ሳይችሉ መቅረታቸውን የሚገልጹት ምንጮች፣ ምሽት ላይ የግቢው የእቃ መጋዘን መጋየቱንና ከዚሁ ጋር ተያይዞ 20 የሚሆኑ ተማሪዎች እንታሰራለን በሚል ፍርሃት ከግቢው ሲጠፉ ፣ የተወሰኑ ተማሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ተማሪዎቹ ከቃጠሎው ጋር ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የታወቀ ነገር የለም።
ከዚሁ ከአርባምንጭ ሳንወጣ ቦንኬ በሚባል አካባቢ አንድ ከወለጋ አካባቢ የመጣ እና በኤልክትሪክ መስመር ዝርጋታ ላይ ይሰራ የነበረን ግለሰብ መቶ አለቃ ኤርምያስ የሚባል የአካባቢው ፖሊስ ተኩሶ የገደለው ሲሆን፣ ህዝቡ ፖሊሱን በመክበብ በቁጥጥር ስር አውሎ ለፖሊስ ማስረከቡን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

No comments:

Post a Comment