Thursday, December 28, 2017

ሕጻናትን ጨምሮ 8 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በኢትዮጵያ መጠለያ ካምፕ ጋምቤላ ውስጥ መገደላቸው ተሰማ

ሕጻናትን ጨምሮ 8 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በኢትዮጵያ መጠለያ ካምፕ ጋምቤላ ውስጥ መገደላቸው ተሰማ። ሬዲዮ ታማዙጅ የተባለ ጣቢያ ከሱዳን እንደዘገበው ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ የሙርሌ ጎሳ አባላት የሆኑ ሱዳናውያን ዲማ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል። የካምፑ የስራ ሃላፊ አንድሪው ካካ እንዳረጋገጡትም ከትላንት በስትያ ታህሳስ 17 ለሊት ላይ በስደተኞች መጠለያ ውስጥ ተኩስ ተከፍቶ 8ቱ ሰዎች ተገድለዋል። ከስምንቱ የሙርሊ ጎሳ አባላት መካከል 4ቱ ሕጻናት፣ 3ቱ ሴቶች አንዱ ደግሞ የ60 አመት አዛውንት መሆናቸውን ሬዲዮ ጣቢያው ዘግቧል። ሟቾቹ በደቡብ ሱዳን በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ በኢትዮጵያ በስደት ተጠልለው የነበሩ መሆናቸውን የካምፑ ሃላፊ ገልጸዋል። በዚሁ ጥቃት አንድ ሌላ ስደተኛም መቁሰሉ ተነግሯል። የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ወደ አካባቢው ቢደርሱም የሕወሃት ባለስልጣናት ግን ስለስደተኞቹ መሞት ማረጋገጫ አልሰጡም። በጋምቤላ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሙርሌ ጎሳ አባላት ላይ በተመሳሳይ ሁኔታ ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች በመቶ የሚቆጠሩ ሕጻናትን በሃይል መውሰዳቸውንና ግድያ ሲፈጽሙ እንደነበርም ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment