(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ትናንት ህዳር 17 እና ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም በቦረና ዞን በዱቡልቅ እና በያቬሌ ከተሞች ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። የተቃውሞ ሰልፉ 28 የቦረና ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
ሰልፈኞቹ “ እኛን የሚገድለን የሶማሊ ልዩ ሃይል ሳይሆን የወያኔ ልዩ ሃይል ነው፣ ከእንግዲህ በወያኔ አንገዛም፣ ወያኔ እርስ በርስ ማጋጨቱን ያቁም” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል።
ሰሞኑን በአሬሮ ወረዳ 24፣ በሞያሌ ደግሞ 4 የቦረና ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ተገድለዋል። ከያቬሎ ወደ ሞያሌ በሚወስደው መስመር መሃል በ50 ኪ/ሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ዱቡሉቅ ከተማም ዛሬ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ሲካሄድ ውሎአል

No comments:
Post a Comment