ሲ ኤን ኤን የሲ አይ ኤን ቪዲዮ አባሪ አድርጎ ይፋ ባደረገ መረጃ የቢን ላደን ተመራጭና ተወዳጅ የሆነው ወንድ ልጁ ሀምዛ ቢን ላደን በሕጻንነቱ ከሚታወቀው ፎቶ ግራፉ ውጪ እስካሁን ምን ገጽታ እንዳለው በይፋ አይታወቅም ነበር። የአሜሪካው የስለላ ተቋም ሲ አይ ኤ የቢን ላደንን ልጅ የቅርብ ጊዜ መልክ የሚያሳዩ የቪዲዮ ምስሎችን ይፋ አድርጓል።-ምስሎቹ እስካሁን ይፋ ያልሆኑና የልጁን የቅርብ ጊዜ ገጽታዎችን የሚያሳዩ ናቸው። የቢን ላደን ተመራጭና ተወዳጅ የሆነውን ወንድ ልጅ ሀምዛ ቢን ላደንን በሕጻንነቱ ከሚታወቀው ፎቶ ግራፉ ውጪ እስካሁን ምን ገጽታ እንዳለው በይፋ አይታወቅም ነበር ሲል ሲ ኤን ኤን መረጃውን ይፋ ያደረገው የሲ አይ ኤን ቪዲዮ አባሪ በማድረግ ነው። ይሁን እንጂ ሀምዛ በአልቃይዳ በሚለቀቁ የፕሮፓጋንዳና የድምጽ የቅስቀሳ መልዕክቶች ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አመልክቷል። ሲ ኤን ኤን በዘገባው አንድ የጸረ
ሽብር ከፍተኛ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ሐምዛ ቢን ላደን አልቃይዳን ወደፊት ለመምራት እየተዘጋጀ የሚገኝና በድርጅቱ ውስጥ ተሰሚነቱ እየጨመረ የመጣ ወጣት ነው። በሲ አይ ኤ የተለቀቀው አዲስ ቪዲዮ ቢን ላደን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 ፓኪስታን ውስጥ በድብቅ በሚኖርበት ቤት እያለ ሲገደል ከተሰበሰቡት ማስረጃዎች አንዱ እንደሆነ ተጠቅሷል። ይህ የተለቀቀው ቪዲዮ ሐምዛ ቢን ላደን ከ2009 በፊት ኢራን ውስጥ በሰርጉ ስነስርአት ላይ የተቀረጸ እንደነበር ባላስልጣናት ተናግረዋል። ሐምዛ ከአንድ የአልቃይዳ ከፍተኛ አመራር ልጅ ጋር ትዳሩን እንደፈጸመና ቢን ላደንም ለዚህ ልጅ ትልቅ ቦታ መድረስ በጣም ጉጉት እንደነበረው የመከላከያና የዲሞክራሲ ፋውንዴሽን ባልደረባ የሆኑት ቢል ሮጂዎ ለሲ ኤን ኤን ተናግረዋል። ቪዲዮውንም ከሌሎች 500 ሺ ከሚሆኑ መረጃዎች ጋር ፋውንዴሽኑ እየመረመራቸው እንደሆነ አስታውቀዋል። በሐምዛ ሰርግ ወቅት ቢን ላደን ተደብቆ የነበረበት ግዜ ቢሆንም ሌሎች ከፍተኛ የአልቃይዳ መሪዎች በሰርጉ ላይ እንዲገኙ ግን አድርጓል። ከሰርጉ በኋላም ቪዲዮውን ለማየት ትልቅ ጉጉት ነበረው። አሁን በሃያኛው አጋማሽ እድሜ ላይ የሚገኘው ሐምዛ በ2001 በኒዮርክ በአልቃይዳ የሽብር ጥቃት ከመፈጸሙ በፊትና በኋላ ከአባቱ ጋር እንደነበር በኋላ ግን ወደ ኢራን በመሔድ እንደተሸሸገ ታውቋል። በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ሐምዛ የ10 ደቂቃ የድምጽ መልዕክት መልቀቁ የሚታወቅ ሲሆን የአልቃይዳ ተከታዮች በአይሁዶች፣በአሜሪካውያን፣በምዕራቡ አለም ሰዎች ብሎም በሩሲያ ዜጎች ላይ ጥቃት እንዲያደርሱ በመልዕክቱ ጥሪ አድርጓል።

No comments:
Post a Comment