የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በሶማሊ ልዩ ሃይሎች እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል የተጀመረው ግጭት ትናንትና ዛሬ ተባብሶ ቀጥሎአል። ሊበን ወረዳ፣ አሬሮ ወረዳና ሞያሌ ወረዳዎች ግጭቱ ተስፋፍቶ እስከ ሻቦ ድረስ ውጊያ መኖሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞያሌ ከተማ ባለው ግጭት ጣልቃ ገብተው ከ5 በላይ ሰዎችን ገድለዋል። በሌሎች ወረዳዎች በሚካሄደው የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የሚደርሰን መረጃ አመልክቷል።
ወደ ሞያሌ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ ተሽከርካሪዎች ማለፍ አልቻሉም።
በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል የሚካሄደው ግጭት ለወራት ቢቀጥልም፣ መከላከያ ሰራዊት ሊያስቆመው አልቻለም።

No comments:
Post a Comment