(ኢሳት ዜና ህዳር 6 ቀን 2017 ዓም)
በሲዳማ ዞን ይርጋዓለም ከተማ ለአባይ ግድብ መዋጮ አንከፍልም ያሉ መመህራን ስጋት ላይ መውደቃቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። መምህራን በብሄራቸው ሰበብ ጥቃት
የይርጋአለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት መምህራን ከኑሮዋቸው ጋር በማማያዝ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለመክፈል እንደማይችሉ አቋማቸውን ግልጽ ካደረጉ በሁዋላ፣ የአካባቢው ካድሬዎች ወደ ሌሎች ክልል ተወላጆች መመህራን በመሄድ፣ “ ለግድቡ መዋጮ እንዲከፈል የማይፈልጉ እንዲሁም በክልሉ አመጽ እንዲቀሰቀስ የሚፈልጉ አማሮች በመሆናቸው ተጠንቀቁ” እያሉ በመናገር ላይ መሆናቸውን መምህራኑ ገልጸዋል።

ለግደቡ ለማዋጣት አቅም እንደሌላቸው የገለጹት ሁሉም የወረዳው መምህራን ናቸው። መምህራኑን ለመከፋፈል እንዲመች የብሄር አጀንዳ ይዘው መምጣታቸውን መምህራን አውግዘውታል። መምህራኑ የካድሬዎችን ሃሳብ ባለመቀበልና በአቋማቸው በመጽናታቸው ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ ከደሞዛቸው በግድ እንደሚቆረጥባቸው ተነግሮአቸዋል
የመምህራኑን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የአማራ ተወላጅ መምህራን ጥቃት ይፈጸምብን ይሆናል በማለት ስጋታቸው እየገለጹ ይገኛሉ።
x
No comments:
Post a Comment