ተማሪዎቹ ቀደም ብሎ የትምህርት ማቆም አድማ አድርገው በነበረበት ወቅት፣ ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ለማግባባት በአባ ገዳዎች ቃል የተገባላቸው ነገር ሳይፈጸም፣ የጊዜ ገደቡ በመድረሱ ትምህርት አቋርጠው ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። አድማው ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም የተጀመረ ሲሆን፣ ዛሬ ህዳር 19፣ ሁሉም የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።
ተማሪዎች በወቅቱ ከጠየቁዋቸው ጥያቄዎች መካከል ፣ የሶማሊ ልዩ ሃይሎች በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ይቁም፣ በምስራቅ እዝ
ወታደራዊ አዛዦች የተሾሙትና ከህወሃት የደህንነት አካላት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ያሉዋቸውን የዩኒቨርስቲው ምክትል ፕሬዚዳንትነት ዶ/ር በላይነህ ለገሰ ይነሱየሚሉት ይገኙበታል ።
ሁሉም የግቢው ተማሪዎች በአንድነት የወጡ ሲሆን፣ የሃሮማያ ህዝብ ለተማሪዎቹ ገንዘብ በማዋጣት የትራንስፖርት ወጪያቸውን ለመሸፈን ሲሯሯጡ ታይቷል።
ተማሪዎቹ ትናንት ምሽት ላይ በግቢው ውስጥ በሚገኙ ወታደሮች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው የአይን እማኖች ገልጸዋል።
ትናንት ከግቢያቸው እንዲወጡ የተገደዱት የጂማ የምህንድስና ተማሪዎች ደግሞ ከከተማው እንዳይወጡና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዳይሄዱ በመናሃሪያ አካባቢ የሚገኙ የፌደራል ፖሊሶችና የመከላከያ አባላት መታወቂያቸውን እያዩ እየከለከሉ ነው።

No comments:
Post a Comment