የአካባቢው ህዝብ ተደጋጋሚ ተቃውሞ ማድረጉን ተከትሎ ኦህዴድ በሃረሪ ክልል የሚገኙ ባለስልጣኖች አንስቷል። ከተነሱት ባለስልጣኖች መካከል የክልሉ የኦህዴድ ምክትል ሃላፊ አቶ ናስር መሃመድ፣ የሃረሪ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ አቶ ሸሪፍ አህመድ ፣ የፖሊስ ም/ል አዛዡ ም/ል ኮሚሽነር ያሲን፣ ፣ የሸንኮር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሃይማኖት አሰፋ፣ የሸንኮር ወረዳ ጤና አስተባባሪ- አቶ ፈቃዱ ባቡሬ ፣ የሃኪም ወረዳ ፍትህና ጸጥታ ሃላፊ አቶ ከማል ፣ የሃኪም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ - አቶ አብዲ እና የአባድር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ከድር ይገኙበታል። የሃረሪ ገቢዎች ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን ፉሪ፣ በ ወ/ሮ ሰሚራ ተተክተዋል።
ከስልጣን የተነሱት የክልሉ ም/ል አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ሃምዛ መሃመድ እስካሁን ድረስ በ ሌላ የሃላፊነት ቦታ አልተመደቡም። ምንም እንኳ ኦህዴድ እነዚህን የህዝብ ማረጋጊያ ያላቸውን እርምጃዎች ቢወስድም፣ በሙስና የተዘፈቁት የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ መሪዎች ከስልጣን ሳይነሱ መቅረታቸውን ህዝቡን ይበልጥ አስቆጥቷል። ዋናውን ስልጣን ይዘው ክልሉን የሚበድሉት የሃብሊ ባለስልጣናት ሆነው እያለና የህዝቡም ዋና ጥያቄ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ሆነ እያለ ኦህዴድ የአንድ ወገን እርምጃ በመውሰድ የህዝቡን ጥያቄ መልሻለሁ ሊል አይችልም በማለት፣ ተጨማሪ ተቃውሞዎች ሳይነሱ የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ከፍተኛ አመራሮች እንዲነሱ እንዲሁም ሌሎች ያነሱዋቸው ጥያቄዎች እንዲመለሱ አሳስበዋል።
x
No comments:
Post a Comment