(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ከተለያዩ ከተሞች ተይዘው የመጡ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ እና የአርበኞች ግንቦት 7 አባል ናቸሁ የተባሉ ወጣቶች ባህር ዳር በሚገኘው የደህንነት የምርመራ ቢሮ ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል። በከተማዋ “ቦምብ ወርውራችሁዋል እንዲሁም የመንግስት ተቋም ላይ ቦንብ ለማፈንዳት አቅዳችሁዋል የተባሉ ወጣቶች በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብርተኝነት እና የልዩ ወንጀሎች የምርመራ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ጥበበ ሀይሌ እና በምዕራብ ጎጃም የደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ወንድማገኝ ትዕዛዝ ወጣቶቹ ድብደባ እና ሌሎች አካላዊ ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው ነው። ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸው ያሉበትን ቦታ እንኳን እንደማያዉቁ ምንጮች ገልጸዋል።

ድባንቄ መድሀኒአለም ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሚገኘው የክልሉ የምርመራ ቢሮ ከተለያዩ የአማራ ክልል ቦታዎች በሽብርተኝነት ተይዘው የመጡ ከ18 በላይ ወጣቶች ግርፋት እየተፈጸመባቸው በመሆኑ የከተማው ነዋሪዎች እንዲታደጉዋቸው ምንጮች ጥሪ አቅርበዋል።
No comments:
Post a Comment