በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በነበረው ግጭት ተጠርጣሪ የሆኑ የሶማሌ ተወላጆችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የሶማሌ ክልል ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተገለጸ። በቁጥጥር ስር ለማዋል ተባባሪ ያልሆኑ የሶማሌ ክልል አመራሮች ርምጃ እንዲወሰድባቸው ተወስኗል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች ለወራት በዘለቀውና አሁንም መብረድ ባልቻለው ግጭት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑ የሶማሌ ክልል አመራሮች ርምጃ እንዲወሰድባቸው መወሰኑን የዘገበው በሀገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው። ውሳኔውን ያሳለፈው በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው ግብረ ሃይል እንደሆነም ዘገባው አመልክቷል። ግብረ ሃይሉ የፌደራል ፖሊስ ያቀረበውን ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ የተጠረጠሩትን በሕግ ጥላ ስር ለማዋል በተደረገ ጥረት ተባባሪ ያልነበሩ የክልሉ አመራሮች ተጠያቂ እንዲሆኑ መመሪያ አስተላልፏል። የፌደራል ፖሊስ በዚህ ሪፖርቱ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል ጥሩ ትብብር እንዳደረገለት አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ከተጠረጠሩት 98 ግለሰቦች ውስጥ 44 ያህሉ በፌደራል የጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመላክተዋል። በሶማሌ ክልል በፌደራል
Thursday, November 30, 2017
በምስራቅ ሀረርጌ በተለያዩ ከተሞች በተነሳ ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ።
በምስራቅ ሀረርጌ በተለያዩ ከተሞች በተነሳ ተቃውሞ 6 ሰዎች ተገደሉ። በአዳማ ናዝሬት ዛሬ በተቀሰቀሰው ግጭት 2 ነዋሪዎች በአጋዚ ሰራዊት መገደላቸው ታወቋል። በምስራቅ ሀረርጌ ጨለንቆ፣ ጉርሱም፣ በደኖና ባቢሌ ህዝባዊ አመጽ ተነስቶ ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ግጭት መፈጠሩንም የደረሰን ዜና ያመለክታል። በአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እየወጡ ነው። በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉም ታውቋል። የህወሃት ደህንነቶች በኦነግ ስም ወጣቶችን እየመለመሉ በማሰር ላይ መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። ዛሬ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች በትንሹ ስምንት ሰዎች ተገድለዋል። የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ግጭት ዳግም ባገረሸበት በዚህ ሰሞን ምስራቅ ሀረርጌ በህዝባዊ ተቃውሞ እየተናጠች ነው። በግጭቱ የተፈናቀሉትን ለመርዳት የተንቀሳቀሰው ህዝብ ላይ የመከላከያ ሰራዊትና የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ርምጃ በመውሰድ ከ6 በላይ ሰዎችን መግደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በጨለንቆ፣ በጉርሱም፣በበደኖ፣ በባቢሌ፣ በአወዳይና በሌሎች ከተሞች ህዝባዊ ንቅናቄ የተቀጣጠለ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊት በቀጥታ ተሳታፊ ሆኖ ርምጃ በመውሰድ ላይ ነው። ዛሬ በአዳማ
በአባይ ወልዱ ሲመራ የነበረው የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ራሱን ወደ ጥገኛ ገዢ መደብ የማሸጋገር አዝማሚያ ተጠናውቶት እንደነበር የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በአቋም መግለጫው አስታወቀ።
በአባይ ወልዱ ሲመራ የነበረው የህወሃት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ራሱን ወደ ጥገኛ ገዢ መደብ የማሸጋገር አዝማሚያ ተጠናውቶት እንደነበር የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ በአቋም መግለጫው አስታወቀ። ስራ አስፈጻሚው የውሸት ሪፖርት ሲያወጣ እንደነበርም ተመልክቷል። በትግራይ ማህበረሰብ ዘንድ የአድዋ ተወላጆች ስልጣኑን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጠሩት የሚል አስተያየት በሰፊው በመደመጥ ላይ ነው። ለተራዘሙ ቀናት በመቀሌ ግምገማ ተቀምጦ የነበረው የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ህዳር 21/2010 ድርጅታዊ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መግለጫው ማዕከላዊ ኮሚቴው ስር ነቀል ግምገማ በማካሄድ የእርምት ርምጃና የአመራር ሽግሽግ በማድረግ ማጠናቀቁን አስታውቋል። የአቋም መግለጫው ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ ስትራቴጂካዊ አመራሩ እየተዳከመ ተልዕኮውን ለመወጣት የሚያስችለው ቁመና፣አመለካከትና አደረጃጀት ተሸርሽሯል ይላል። ይህንን ቁመና ይዞ የሕወሃት መስመርንም ሆነ የመለስ ሌጋሲን ለማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ እንደሌለ በግልጽ ማየቱን ገልጿል። በአቶ አባይ ወልዱ ሊቀመንበርነት ሲመራ የነበረው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከገባበት የችግር አዙሪት ውስጥ መውጣት አቅቶት ሲዳክር መቆየቱን እንዳረጋገጠ ማዕከላዊ
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተካሄደ
በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተካሄደ። በምስራቅ ሀረርጌ ሰሞኑን የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን የህወሃት መንግስት ከስልጣን ይውረድ የሚለው ደግሞ ጥያቄያቸው ነው ። በወለጋ የተለያዩ ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው። በሌላ በኩል በአርባምንጭ ከተማ የሚገኘውን አየር ማረፊያ ሲጠብቁ የነበሩ ወታደሮች መጥፋታቸው ታወቋል። ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ እዝ አየር ምድብ አባላትም ለሁለት ቀናት አድማ አድርገዋል። ዳግም የተቀሰቀሰውንና ለበርካታ ሰዎች መገደል ምክንያት የሆነውን በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች አዋሳኝ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ የተነሳው ተቃውሞ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። በጉርሱም ሁለት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ ህዝቡ አደባባይ በመውጣት የህወሃትን መንግስት ያወገዘ ሲሆን በአስቸኳይ ከስልጣን እንዲወርድም መጠየቁ ተመልክቷል። ትናንት በጉርሱም በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ አንድ ፖሊስ፣ ሁለት የልዩ ሃይል አባላት ፣ ሁለት ሚሊሺያዎችና አንድ ሲቪል በአጋዚና ፌደራል ፖሊሶች መገደላቸው መዘገቡ ይታወሳል። ዛሬ ጉርሱም ላይ ህዝቡ ዳውን ዳውን ወያኔ እያለ ቁጣውን ሲገልጽ የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች በመኪና ጡሩምባ ድምጽ ሲያጅቡ
በአማራ ክልል ቻግኒ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች በፖሊስና በአካባቢው የሚሊሻ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአማራ ክልል ቻግኒ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቀ ሰዎች በፖሊስና በአካባቢው የሚሊሻ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በደቡብ ጎንደር ደጎማም ዛሬ ክፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። በሀዋሳና በአዲስ አበባ አንዳንድ ቦታዎች የትግል ጥሪ ወረቀቶች መበተናቸው ታውቋል። በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በፖሊስና በአካባቢው ሚሊሻ ታጣቂዎች ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ነው የታወቀው። ትናንት ልዩ ስሙ ፎረንቅ በተባለው ስፍራ ከምሽቱ 3 ፡20 ሲሆን በአካባቢው ሲዘዋወሩ በነበሩ የፖሊስና የሚሊሻ አባላት ላይ ጥቃት ተከፍቶ ሁለት ታጣቂዎች በቀስት የተመቱ ሲሆን አንደኛው በቻግኒ ሆስፒታል ህክምና ሲደረግለት ሌላኛው ታጣቂ ጉዳቱ ከባድ በመሆኑ ወደ ባህርዳር ፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዱ ታውቋል። ከጥቃቱ በኋላ በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደተሰማ የጠቀሱት የአይን እማኞች ተጨማሪ ሃይል በመግባት ጥቃት አድራሾቹን እያሰሰ እንደሆነም
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ እየተባባሰ መቀጠሉ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት የጋምቤላ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አለመቻሉን ገለጸ።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ቀውስ እየተባባሰ መቀጠሉ በሚነገርበት በአሁኑ ወቅት የጋምቤላ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል አለመቻሉን ገለጸ። በዚህም በክልሉ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ የጥቅምት ወር ደሞዛቸው እስከ ህዳር አጋማሽ እንዳልተከፈላቸው ታውቋል። የጋምቤላ ከተማ ከንቲባ ክልሉ ገንዘብ ለመክፈል ጊዜያዊ ችግር እንዳጋጠመው አረጋግጠዋል። የጋምቤላ ክልል በስሩ የሚያስተዳድራቸው የመንግስት ሰራተኞች በአጠቃላይ 1550 ያህል እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ። ታዲያ እነዚህ ሁሉ ሰራተኞች ናቸው የጥቅምት ወር ደሞዝ እስከ ሕዳር አጋማሽ ድረስ እንዳልተከፈላቸው የታወቀው። የመስከረም ወር ደሞዝም የተከፈላቸው ዘግይቶ መሆኑ ተመልክቷል። ደሞዛቸውን ካላገኙት 1ሺ 547 ሰራተኞች ውስጥ 513ቱ መምህራን መሆናቸውንም መረጃው አመልክቷል። እነዚህ መምህራን ደሞዝ ይከፈለን በማለት ባለፈው ሳምንት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውንና ከዚህም ጋር ተያይዞ የመማር ማስተማር ሂደቱ መስተጓጎሉን
በሔግ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ የነበሩት የቦስኒያ ክሮሺያ ጄኔራል በችሎቱ ፊት መርዝ ጠጥተው ሕይወታቸውን አጠፉ
በሔግ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ የነበሩት የቦስኒያ ክሮሺያ ጄኔራል በችሎቱ ፊት መርዝ ጠጥተው ሕይወታቸውን አጠፉ። በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ በተፈጸመ የጦር ወንጀል ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸውና በ20 አመት እስራት እንዲቀጡ የተፈረደባቸው ጄኔራል አሟሟት ጉዳይ በመጠራት ላይ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ የቀድሞ የቻይና ጄኔራል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው ባለበት ወቅት ሕይወታቸውን ማጥፋታቸው ታውቋል። አንድ የቀድሞው የቦስኒያ ክሮሺያ ጄኔራል በሔግ ፍርድ ቤት ውስጥ የፍርድ ውሳኔያቸውን በመስማት ላይ እያሉ መርዝ ጠጥተው መሞታቸው ታውቋል። የ72 አመቱ ጄኔራል ስሎቦዳን ፕራልጃክ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1992 እስከ 95 በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ በተፈጸመ የጦር ወንጀል በሔግ ኔዘርላንድ የሚገኘው ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቶ በ20 አመት እስራት እንዲቀጡ ከዚህ በፊት የወሰነውን ውሳኔ ይግባኝ ለማለት ነበር ትላንት ፍርድ ቤት የቀረቡት። ዋናው ዳኛ የ20
Tuesday, November 28, 2017
ዳኛ ዘርዐይ ወልደሰንበት ዛሬ ማሕሌት ፋንታሁንን በችሎት መሐል በወቀሳ አስጠነቀቋት
ጌታቸው ሽፈራው
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን “አክላቸው ወንድወሰን” በተባለ የፌስቡክ አድራሻ የዳኛ ስም ተጠቅሶ የተፃፈ የፍርድ ቤቱን ክብር የሚነካ ፅሁፍ አጋርተሻል በሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
አሚር በፌስቡክ የተፃፈ ፅሁፍ ስር አስተያየት እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም እኔ (ጌታቸው ሺፈራው) የምፈልገውን የፍርድ ቤት ውሎ ብቻ ቆርጬ እንደምዘግብ ይህም ምን “ሸንቆጥ” ለማድረግ እንደተፈለገ ፍርድ ቤቱ እንደሚረዳው፣ ለሌላ ሰውም መረጃ እንደምልክ ፍርድ ቤቱ ገልፆአል። ፍርድ ቤቱ ለሌላ ሰው መረጃ ትልካለህ ሲል የጠቀሰው ማስረጃም ሆነ የሰው ስም የለም።
ናትናኤል (የአባቱ ስም ያልተጠቀሰ)፣ አንገቱ ላይ “ሻርፕ” ያደርጋል የተባለና በችሎት ያልነበረ ግለሰብም ስሙ በችሎት ተጠቅሷል።
ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን በችሎት ቀርባ አጋርተሽዋል ስለተባለው ፅሁፍ የተጠየቀችው በጠዋቱ የፍርድ ቤት ጊዜ ሲሆን ለከሰዓት ተቀጥሮ ከአሁን ቀደም የምትፅፋቸው ፅሁፎች አጋራችው የተባለውን አይነት ይዘት እንደሌለው በመጥቀስ በተግሳፅ እንደታለፈች ፍርድ ቤቱ ገልፆአል።
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት በሆነው ሰላም ባስ ገራዥ ላት ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው።
በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ/ሕወሃት/ንብረት በሆነው ሰላም ባስ ገራዥ ላት ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ግለሰቦች ክስ ተመሰረተባቸው። አቃቢ ህግ ግለሰቦቹ ድርጊቱን የፈጸሙት በአርበኞች ግንቦት ሰባት ትዕዛዝ ነው ሲልም አመልክቷል። አርብ ሕዳር 15/2010 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች አንተነህ ፋንታሁን፣ኤርሚያስ አለባቸው፣አንድነት ፋንታሁን፣ፍስሃ እያዩና ብርሃኑ ሞገስ የተባሉ መሆናቸውም በክሱ ተመልክቷል። እኒዚህ በክሱ ላይ የተዘረዘሩት 5 ግለሰቦች ሐምሌ 13/2009 ከሌሊቱ 6 ሰአት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የሰላም ባስ ገራዥ ላይ ሁለት የእጅ ቦምብ በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸውን አቃቢ ህግ በክሱ ዘርዝሯል። ግለሰቦቹ ከዚህም በተጨማሪ በመስከረም ወር በኖክ ነዳጅ ማደያ ላይ የአምቦ ውሃ
የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ
ተማሪዎቹ ቀደም ብሎ የትምህርት ማቆም አድማ አድርገው በነበረበት ወቅት፣ ትምህርታቸውን እንዲጀምሩ ለማግባባት በአባ ገዳዎች ቃል የተገባላቸው ነገር ሳይፈጸም፣ የጊዜ ገደቡ በመድረሱ ትምህርት አቋርጠው ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። አድማው ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም የተጀመረ ሲሆን፣ ዛሬ ህዳር 19፣ ሁሉም የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።
ተማሪዎች በወቅቱ ከጠየቁዋቸው ጥያቄዎች መካከል ፣ የሶማሊ ልዩ ሃይሎች በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ይቁም፣ በምስራቅ እዝ
ተማሪዎች በወቅቱ ከጠየቁዋቸው ጥያቄዎች መካከል ፣ የሶማሊ ልዩ ሃይሎች በኦሮሞ ተወላጆች ላይ የሚፈጽሙት ጥቃት ይቁም፣ በምስራቅ እዝ
ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚዓብሄር ህወሃትን እንዲመሩ መመረጣቸው በስፋት እየተነገረ ነው
በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ስር ሆኖ ግምገማ እያደረገ የሚገኘው ህወሃት የድርጅቱን ሊቀመንበርና የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር አቶ አባይ ወልዱን ከስልጣን ካነሳ በሁዋላ፣ የድርጅቱን ሊቀመንበርነት ቦታ ለወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር የክልሉን መስተዳደርነት ቦታ ደግሞ ለአቶ አለም ገብረዋህድ እንደተሰጡ ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እየገለጹ ነው።
በትምህርት ጥራት ዙሪያ መምህራኑና ባለስልጣናቱ አልተግባቡም
በደቡብ ኦሞ ዞን ዋና ከተማ-ጂንካ ‹‹የአንጋፋና ጡረተኛ መምህራን የሜዳሊያ መስጠት›› ፕሮግራም ላይ በትምህርት ጥራት ዙሪያ በተደረገ ውይይት በደቡብ ክልል በአጠቃላይ ፣በተለይ ደግሞ በደቡብ ኦሞ ዞን የትምህርት ጥራት ጉዳይ በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የክልሉ መምህራን ማኅበር ተወካይና የዞኑ መምህራን ገልጸዋል፡፡ የዞኑ አስተዳዳሪ ይህንን የባለሙያዎቹን አስተያየት ሊቀበሉ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ህዳር9 ቀን 2010 ዓም በተካሄደው ስነስርዓት የክልሉን መምህራን-ማኅበር በመወከል የተገኙት መምህርት ጤናዬ ታደሰ የትምህርት ጥራቱ--“ከትምህርት ፖሊሲውና የትምህርት መዋቅሩ በመነጩ ችግሮች በአሁኑ ጊዜ ትናንት ‘የማያነቡ ተማሪዎች’ እያልን ከምንገልጽበት አደጋ ተሻግሮ ዛሬ ‹የማያነቡ› መምህራን ማፍራት ደረጃ-ተሸጋሯል” ብለዋል። “ ይህ ችግር ሥር እየሰደደ በመሆኑ እንደአገርም እንደክልላችንም አስደንጋጭና በእጅጉ አሳሳቢ ስለሆነ አስቸኳይ መፍትሄ ካልተበጀለት በአጠቃላይ የአገራችን ዕድገትና ልማት ቁልፍ በሆነው የሰብዓዊ ሃብት ልማት ላይ የሚያስከትለው አደጋ አገሪቱን በአጭር ጊዜ የከፋ አዘቅት ውስጥ ይከታታል፡፡›› በማለት የማኅበራቸውን ግምገማ ውጤት አስረድተዋል፡፡
ህዳር9 ቀን 2010 ዓም በተካሄደው ስነስርዓት የክልሉን መምህራን-ማኅበር በመወከል የተገኙት መምህርት ጤናዬ ታደሰ የትምህርት ጥራቱ--“ከትምህርት ፖሊሲውና የትምህርት መዋቅሩ በመነጩ ችግሮች በአሁኑ ጊዜ ትናንት ‘የማያነቡ ተማሪዎች’ እያልን ከምንገልጽበት አደጋ ተሻግሮ ዛሬ ‹የማያነቡ› መምህራን ማፍራት ደረጃ-ተሸጋሯል” ብለዋል። “ ይህ ችግር ሥር እየሰደደ በመሆኑ እንደአገርም እንደክልላችንም አስደንጋጭና በእጅጉ አሳሳቢ ስለሆነ አስቸኳይ መፍትሄ ካልተበጀለት በአጠቃላይ የአገራችን ዕድገትና ልማት ቁልፍ በሆነው የሰብዓዊ ሃብት ልማት ላይ የሚያስከትለው አደጋ አገሪቱን በአጭር ጊዜ የከፋ አዘቅት ውስጥ ይከታታል፡፡›› በማለት የማኅበራቸውን ግምገማ ውጤት አስረድተዋል፡፡
የሕወሃትን አገዛዝ የሚያወግዙ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተነገረ።
የሕወሃትን አገዛዝ የሚያወግዙ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተጠናክረው መቀጠላቸው ተነገረ። የሃሮማያና የጅማ ዩኒቨርስቲ ተመሪዎች በተቃውሞ ላይ ናቸው። 35ሺ የሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ሲወጡ የጅማዎቹ ደግሞ ከግቢያቸው እንዳይወጡ ታግተዋል። በጋሞጎፋ ዞን ሳውላ፣አወዳይ እንዲሁም በወለጋ ሕዝባዊ ተቃውሞው እንደገና ተቀጣጥሏል። በኢትዮጵያ የሕወሃትን የ26 አመታት አገዛዝ ለማክተም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚካሄደው ተቃውሞ እንደቀጠለ ይገኛል። በጋሞጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በግብር የተንገሸገሸው ነዋሪ የገቢዎችና ጉምሩክ ጽህፈት ቤትን ቅዳሜ ሕዳር 16/2010 ለሊቱን ሲያቃጥል አድሯል። የሳውላ ከተማ ነዋሪዎች የሕወሃት አገዛዝ ወገኖቻችንን ለሚገልበት ጥይት መግዣ ግብር አንከፍልም ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ነዋሪዎቹ ከኦሮሚያ ቄሮና ከአማራ ፋኖዎች ጋር እንቆማለን ሲሉም ድምጻቸውን አሰምተዋል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወገን ቀርቶ በጠላት ላይ የማይደረግ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል ሲል የቦረና አስተዳደር ቅሬታውን አቀረበ።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወገን ቀርቶ በጠላት ላይ የማይደረግ ኢ ሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል ሲል የቦረና አስተዳደር ቅሬታውን አቀረበ። ድርጊቱን የፈጸሙ የመከላከያ አባላት ተላልፈው እንዲሰጡና ለህግ እንዲቀርቡም ጠይቋል። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቦረና ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በሕዳር 14/2010 ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ለመከላከያ ሚኒስቴርና ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በጻፈው ደብዳቤ የመከላከያ ሰራዊት ያደረሰውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በዝርዝር አስፍሯል። ደብዳቤው በቦረና ዞን ድሬ ወረዳ ሶዶ ቀበሌ ግበሬ ማህበር ህብረተሰብ ላይ የደረሰውን ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ይመለክታል የሚል ርዕስን ይዟል። የመከላከያ ሰራዊቱ አባላት ጥቅምት 2/2010 የገበሬ ማህበሩ ነዋሪዎች የሆኑ 3 ሰዎችን ኢ-ሰብአዊና አሰቃቂ በሆነ መልኩ በጥይት ደብድበው ሲገድሉ 19 ያህል ነዋሪዎችን ደግሞ በከባድ ሁኔታ ማቁሰላቸውን በደብዳቤው ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ያመለክታል። ከባድ የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው ውስጥ ከ70 አመት በላይ የሚሆኑ አዛውንቶች፣ ሴቶችና ዕድሜያቸው ከ10
Monday, November 27, 2017
የአዜብ መስፍን ከህውሓት መታገድ፣ /ኤርምያስ ለገሰ/
አንደኛ: የመለስ ራዕይ ወደ ሥላሴ መቃብር ይወርዳል። HD ከዚህ በኋላ " ታላቁ መሪያችን" ብሎ እንዳይናገር ከአርከበ ትእዛዝ ይደርሰዋል።
ሁለተኛ: አዜብ መስፍን የስዬ አብርሃ እጣ ፈንታ ሊደርሳት ይችላል። እርግጥ ዘብጥያ ማውረዱ ዞሮ ዞሮ የኤፈርት ዝርፊያ እና ሌብነት ላይ ስለሚሽከረከር ለስብሃት በጣም ከባድ ይሆንበታል። አርከበም ቢሆን በሌብነት ከሴትየዋ የሚስተካከል በመሆኑ እስሩን ላይደግፈው ይችላል።
ሶስት: የሕውሓት ካድሬዎች ለሁለት ሊሰነጠቁ ይችላሉ። በተለይ ከሌብነቱ በላይ "የባድመ ጉዳይ" በልዩነት ጐልቶ መውጣት ከቻለ አባይ ወልዱ፣አዜብ እና ሳሞራ የኑስ በካድሬው ዘንድ ተቀባይነት ሊኖራቸው ይችላል ። ለስብሓት ነጋ የባድመ ጉዳይ ከባድ ፈተና ይሆንበታል።
በቦረና ዞን ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ።
(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ትናንት ህዳር 17 እና ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም በቦረና ዞን በዱቡልቅ እና በያቬሌ ከተሞች ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። የተቃውሞ ሰልፉ 28 የቦረና ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
ሰልፈኞቹ “ እኛን የሚገድለን የሶማሊ ልዩ ሃይል ሳይሆን የወያኔ ልዩ ሃይል ነው፣ ከእንግዲህ በወያኔ አንገዛም፣ ወያኔ እርስ በርስ ማጋጨቱን ያቁም” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል።
ሰሞኑን በአሬሮ ወረዳ 24፣ በሞያሌ ደግሞ 4 የቦረና ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ተገድለዋል። ከያቬሎ ወደ ሞያሌ በሚወስደው መስመር መሃል በ50 ኪ/ሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ዱቡሉቅ ከተማም ዛሬ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ሲካሄድ ውሎአል
ትናንት ህዳር 17 እና ዛሬ ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም በቦረና ዞን በዱቡልቅ እና በያቬሌ ከተሞች ከፍተኛ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። የተቃውሞ ሰልፉ 28 የቦረና ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
ሰልፈኞቹ “ እኛን የሚገድለን የሶማሊ ልዩ ሃይል ሳይሆን የወያኔ ልዩ ሃይል ነው፣ ከእንግዲህ በወያኔ አንገዛም፣ ወያኔ እርስ በርስ ማጋጨቱን ያቁም” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል።
ሰሞኑን በአሬሮ ወረዳ 24፣ በሞያሌ ደግሞ 4 የቦረና ተወላጆች በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ተገድለዋል። ከያቬሎ ወደ ሞያሌ በሚወስደው መስመር መሃል በ50 ኪ/ሜ ርቅት ላይ በምትገኘው ዱቡሉቅ ከተማም ዛሬ ከፍተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ሲካሄድ ውሎአል
የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ማስፈራሪያ ግቢውን ለቀው ወጡ
(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ለሳምንታት ሲደረግ የነበረው አድማ መቀጠሉን ተከትሎ ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ለመከፋፈል ያወጣው መመሪያ ተቀባይነት እንዳጣ፣ ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። እስካለፈው ቅዳሜ ሃሳባቸውን ይቀይራሉ ብሎ ተስፋ ሲያደርግ የቆየው ዩኒቨርስቲው፣ በተማሪዎች በኩል ምንም መልስ በማጣቱ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። ግቢውን ጥለው የወጡት ቂጦ ፉርዲሳ የምንድስህና ዲፓርትመንት ተማሪዎች ናቸው።
ለሳምንታት ሲደረግ የነበረው አድማ መቀጠሉን ተከትሎ ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ለመከፋፈል ያወጣው መመሪያ ተቀባይነት እንዳጣ፣ ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። እስካለፈው ቅዳሜ ሃሳባቸውን ይቀይራሉ ብሎ ተስፋ ሲያደርግ የቆየው ዩኒቨርስቲው፣ በተማሪዎች በኩል ምንም መልስ በማጣቱ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። ግቢውን ጥለው የወጡት ቂጦ ፉርዲሳ የምንድስህና ዲፓርትመንት ተማሪዎች ናቸው።
የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ማስፈራሪያ ግቢውን ለቀው ወጡ
(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ለሳምንታት ሲደረግ የነበረው አድማ መቀጠሉን ተከትሎ ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ለመከፋፈል ያወጣው መመሪያ ተቀባይነት እንዳጣ፣ ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። እስካለፈው ቅዳሜ ሃሳባቸውን ይቀይራሉ ብሎ ተስፋ ሲያደርግ የቆየው ዩኒቨርስቲው፣ በተማሪዎች በኩል ምንም መልስ በማጣቱ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። ግቢውን ጥለው የወጡት ቂጦ ፉርዲሳ የምንድስህና ዲፓርትመንት ተማሪዎች ናቸው።
ለሳምንታት ሲደረግ የነበረው አድማ መቀጠሉን ተከትሎ ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ለመከፋፈል ያወጣው መመሪያ ተቀባይነት እንዳጣ፣ ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲውን ለቀው እንዲወጡ አድርጓል። እስካለፈው ቅዳሜ ሃሳባቸውን ይቀይራሉ ብሎ ተስፋ ሲያደርግ የቆየው ዩኒቨርስቲው፣ በተማሪዎች በኩል ምንም መልስ በማጣቱ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተገደው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። ግቢውን ጥለው የወጡት ቂጦ ፉርዲሳ የምንድስህና ዲፓርትመንት ተማሪዎች ናቸው።
የኮካ ኮላ ፋብሪካ ንብረት የሆነ ስኳር ተወርሶ ከሶማሊ ክልል ለተፈናቀሉት እንዲውል ተወሰነ
(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ጠቅምት 29 ቀን 2010 ዓም ከአዳማ ተነስቶ ወደ ባህርዳር ይጓዝ የነበረ በ8 ተሽከርካሪዎች የተጫነ 720 ኩንታል ስኳር ጎሃ ጽዮን ከተማ ላይ በኦሮምያ ፖሊስ ከተያዘ በሁዋላ፣ የከተማው ፍርድ ቤት ስኳሩ ከሶማሊ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲከፋፈል ውሳኔ አሳልፏል። ከ8ቱ መኪኖች መካከል በአንደኛው መኪና ላይ የነበረው ስኳር በገበያ ቀን ለህዝቡ አከፋፍለውታል።
የኮካ ኮላ አምራች ኩባንያ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ስኳሩን በህጋዊ መንገድ እንደገዛው ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የአዳማ መጋዘን ክፍያ ፈጽሞ እንደተረከበ ገልጿል።
የኦሮምያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የግዢ ሰነዱን በማዬት ስኳሩ እንዲመለስ ለወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ ጽ/ቤት ደብዳቤ የጻፈ ቢሆንም፣ የ6 መኪኖች ጭነት ስኳር አስቀድሞ ለህዝቡ የተከፋፈለ በመሆኑ ኩባንያው ስኳሩን መልሶ የማግኘቱ እድል ተሟጧል
ጠቅምት 29 ቀን 2010 ዓም ከአዳማ ተነስቶ ወደ ባህርዳር ይጓዝ የነበረ በ8 ተሽከርካሪዎች የተጫነ 720 ኩንታል ስኳር ጎሃ ጽዮን ከተማ ላይ በኦሮምያ ፖሊስ ከተያዘ በሁዋላ፣ የከተማው ፍርድ ቤት ስኳሩ ከሶማሊ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች እንዲከፋፈል ውሳኔ አሳልፏል። ከ8ቱ መኪኖች መካከል በአንደኛው መኪና ላይ የነበረው ስኳር በገበያ ቀን ለህዝቡ አከፋፍለውታል።
የኮካ ኮላ አምራች ኩባንያ ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ስኳሩን በህጋዊ መንገድ እንደገዛው ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የአዳማ መጋዘን ክፍያ ፈጽሞ እንደተረከበ ገልጿል።
የኦሮምያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የግዢ ሰነዱን በማዬት ስኳሩ እንዲመለስ ለወረጃርሶ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ ጽ/ቤት ደብዳቤ የጻፈ ቢሆንም፣ የ6 መኪኖች ጭነት ስኳር አስቀድሞ ለህዝቡ የተከፋፈለ በመሆኑ ኩባንያው ስኳሩን መልሶ የማግኘቱ እድል ተሟጧል
የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው ዮናታን ተስፋዬ 3 አመት ከመንፈቅ ተፈረደበት
(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ወጣት ዮናታን ቀደም ብሎ በሽብር ወንጀል ተከሶ 6 ዓመት ከመንፈቅ ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የሽብር ወንጀል ክሱ ወደ መደበኛ ወንጀል ተለውጦ 3 ዓመት ከመንፈቅ እንዲታሰር ተፈርዶበታል።
ወጣት ዮናታን በፌስቡክ ገጹ ላይ በሚጽፋቸው ጽሁፎች የተነሳ መከሰሱ ይታወቃል። ዮናታን አመክሮ ከተሰጠው ከአምስት ወራት እስር በሁዋላ ሊፈታ ይችላል።
ወጣት ዮናታን ቀደም ብሎ በሽብር ወንጀል ተከሶ 6 ዓመት ከመንፈቅ ተፈርዶበት የነበረ ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የሽብር ወንጀል ክሱ ወደ መደበኛ ወንጀል ተለውጦ 3 ዓመት ከመንፈቅ እንዲታሰር ተፈርዶበታል።
ወጣት ዮናታን በፌስቡክ ገጹ ላይ በሚጽፋቸው ጽሁፎች የተነሳ መከሰሱ ይታወቃል። ዮናታን አመክሮ ከተሰጠው ከአምስት ወራት እስር በሁዋላ ሊፈታ ይችላል።
በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ እና የአርበኞች ግንቦት7 አባላት ናቸው የተባሉ ወጣቶች በእስር ቤት ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ነው
(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ከተለያዩ ከተሞች ተይዘው የመጡ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ እና የአርበኞች ግንቦት 7 አባል ናቸሁ የተባሉ ወጣቶች ባህር ዳር በሚገኘው የደህንነት የምርመራ ቢሮ ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል። በከተማዋ “ቦምብ ወርውራችሁዋል እንዲሁም የመንግስት ተቋም ላይ ቦንብ ለማፈንዳት አቅዳችሁዋል የተባሉ ወጣቶች በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብርተኝነት እና የልዩ ወንጀሎች የምርመራ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ጥበበ ሀይሌ እና በምዕራብ ጎጃም የደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ወንድማገኝ ትዕዛዝ ወጣቶቹ ድብደባ እና ሌሎች አካላዊ ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው ነው። ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸው ያሉበትን ቦታ እንኳን እንደማያዉቁ ምንጮች ገልጸዋል።
ከተለያዩ ከተሞች ተይዘው የመጡ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ እና የአርበኞች ግንቦት 7 አባል ናቸሁ የተባሉ ወጣቶች ባህር ዳር በሚገኘው የደህንነት የምርመራ ቢሮ ከፍተኛ የማሰቃየት ተግባር እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ምንጮች ገልጸዋል። በከተማዋ “ቦምብ ወርውራችሁዋል እንዲሁም የመንግስት ተቋም ላይ ቦንብ ለማፈንዳት አቅዳችሁዋል የተባሉ ወጣቶች በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሽብርተኝነት እና የልዩ ወንጀሎች የምርመራ ሃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ጥበበ ሀይሌ እና በምዕራብ ጎጃም የደህንነት ቢሮ ሃላፊ አቶ ግዛቸው ወንድማገኝ ትዕዛዝ ወጣቶቹ ድብደባ እና ሌሎች አካላዊ ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው ነው። ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸው ያሉበትን ቦታ እንኳን እንደማያዉቁ ምንጮች ገልጸዋል።
አንድ በቱርክ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሰራተኛ “በቱርክና ኢትዮጵያ መሃል” ጦርነት ይቀሰቀሳል በማለቱ የአገሪቱ ጋዜጦች መሳለቂያ ሆነ
(ኢሳት ዜና ህዳር 18 ቀን 2010 ዓም)
ቲ ኤች በሚል ቅጽል ስም የተጠራው የኢምባሲው ሰራተኛ አክራ ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሲያሽከረክር አንድ ታክሲ በመግጨት ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ፖሊሶች ግለሰቡ የአልኮል ምርመራ እንዲያደርግ ሲያዝዙት፣ “ እኔ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ነኝ፣ ምርመራ አላደረግም፣ በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል ጦርነት እንዲነሳ አደርጋለሁ” በማለቱ የቱርክ የመገናኝ ብዙሃን እየተቀባበሉ ተሳልቀውበታል።
ግለሰቡ ራሱን እንደአምባሳደር ቆጥሮ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ይናገር እንደነበር ጋዜጠኞች የዘገቡ ሲሆን በተለይ፣ ከነካችሁኝ “በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል ጦርነት ይነሳል የሚለው አነጋገሩ” እንዳስገረማቸው ጽፈዋል።
ቲ ኤች በሚል ቅጽል ስም የተጠራው የኢምባሲው ሰራተኛ አክራ ውስጥ በስካር መንፈስ ውስጥ ሲያሽከረክር አንድ ታክሲ በመግጨት ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ፖሊሶች ግለሰቡ የአልኮል ምርመራ እንዲያደርግ ሲያዝዙት፣ “ እኔ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ነኝ፣ ምርመራ አላደረግም፣ በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል ጦርነት እንዲነሳ አደርጋለሁ” በማለቱ የቱርክ የመገናኝ ብዙሃን እየተቀባበሉ ተሳልቀውበታል።
ግለሰቡ ራሱን እንደአምባሳደር ቆጥሮ በስካር መንፈስ ውስጥ ሆኖ ይናገር እንደነበር ጋዜጠኞች የዘገቡ ሲሆን በተለይ፣ ከነካችሁኝ “በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል ጦርነት ይነሳል የሚለው አነጋገሩ” እንዳስገረማቸው ጽፈዋል።
በመከላከያና በደህንነቱ ዋና መስሪያ ቤት መካከል ያለው አለመግባባት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ ተሰማ (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
በአቶ ጌታቸው አሰፋ የሚመራው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መስሪያቤት እና በጄነራል ሳሞራ የሚመራው መከላከያ መካከል የተፈጠረው ያለመግባባት በግልጽ የሚታይበት ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል። በመከላከያ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የጦር አዛዦች የደህንነቱ መስሪያ ቤት የሚያቀርበው መረጃ፤ ታእማኒነት የሌለው ነው በማለት በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይሰማል። አቶ ጌታቸው አሰፋ በመከላከያ ውስጥ ያለውን ተሰሚነት ለማስፋት በሚል የሚወስዳቸው እርማጃዎች ቀጥታ ከጄነራል ሳሞራ ጋር እንዳጋጨው መረጃዎች ያመለክታሉ።
Friday, November 24, 2017
Ethiopia: Search for deserters in Southern Ethiopia continues
ESAT News (November 24, 2017)
As search for soldiers who are said have deserted from the army in Southern Ethiopia continued, new reports indicate that one soldier was killed in a shootout between a commander and soldiers who were dispatched to search for the deserters.
Thirty-eight soldiers with the 10th division of the army in southern Ethiopia disappeared Monday along the country’s border with Kenya. It is now confirmed by ESAT sources that they had actually deserted the army.
Ethiopia: TPLF forces kill ethnic Somalis, Oromo in south
TPLF special forces that were deployed to Borbor, near Moyale, in the country’s southern border, have reportedly launched deadly attacks against locals killing at least 27 people.
The TPLF forces have been accused of pitting ethnic Somalis against Oromos who share common resources in Southern Ethiopia. The forces have reportedly used a dispute over land and grazing between the two communities as an excuse to intervene and carry out the deadly attack, according to
ስለ አርሲ ነገሌ የዛሬ ውሎ መረጃ
ዛሬ በአርሲ ነገሌ ከተማ ተቃውሞ ተካሂዷል። ተቃውሞው የብሄር መልክ እንዳለውና በኦሮሞና አማራ መካከል ግጭት እንደተፈጠረ ተደርጎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘገበ ይገኛል። ኢሳት ባደረገው ማጣራት የግጭቱን መነሻና የእለቱን ውሎ እንደሚከተለው ያቀርባል።
አቶ ደረጀ የተባሉ ግለሰብ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ አንድ የመጠጥ ግሮሰሪ ከፍተው ይሰራሉ። በግሮሰሪው ውስጥ የቂልጡ አንደኛና መልስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪዎች የሆኑ ሁለት መምህራን በመዝናናት ላይ እያሉ፣ ሰአቱ እየመሸ በመሄዱ የግሮሰሪው ባለቤት አቶ ደረጀ፣ “ግሮሰሪውን ልዘጋው ነው፣ በጊዜም ለልጆቼ ልድረስላቸው” በማለት መምህራኑ እንዲወጡላቸው ይጠይቁዋቸዋል። መምህራኑም በመጠጥ ሃይል ተገፋፍተው “ሰዓቱ ገና ነው ፣ መዝናናት እንፈልጋለን” በማለት አንወጣም ይላሉ። “ውጡ! አንወጣም!” በሚል ግብግብ የተፈጠረ ሲሆን፣ አቶ ደረጃ ሽጉጥ አውጥተው አንደኛውን መምህር ይመቱታል። የመምህሩ ህይወትም ወዲያውኑ ያልፋል። ይህ እንደተሰማ አቶ ደረጀ ተይዘው ይታሰራሉ።
አቶ ደረጀ የተባሉ ግለሰብ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ አንድ የመጠጥ ግሮሰሪ ከፍተው ይሰራሉ። በግሮሰሪው ውስጥ የቂልጡ አንደኛና መልስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪዎች የሆኑ ሁለት መምህራን በመዝናናት ላይ እያሉ፣ ሰአቱ እየመሸ በመሄዱ የግሮሰሪው ባለቤት አቶ ደረጀ፣ “ግሮሰሪውን ልዘጋው ነው፣ በጊዜም ለልጆቼ ልድረስላቸው” በማለት መምህራኑ እንዲወጡላቸው ይጠይቁዋቸዋል። መምህራኑም በመጠጥ ሃይል ተገፋፍተው “ሰዓቱ ገና ነው ፣ መዝናናት እንፈልጋለን” በማለት አንወጣም ይላሉ። “ውጡ! አንወጣም!” በሚል ግብግብ የተፈጠረ ሲሆን፣ አቶ ደረጃ ሽጉጥ አውጥተው አንደኛውን መምህር ይመቱታል። የመምህሩ ህይወትም ወዲያውኑ ያልፋል። ይህ እንደተሰማ አቶ ደረጀ ተይዘው ይታሰራሉ።
በሞያሌ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ የሚካሄደው ግጭት ቀጥሎአል
የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ በሶማሊ ልዩ ሃይሎች እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል የተጀመረው ግጭት ትናንትና ዛሬ ተባብሶ ቀጥሎአል። ሊበን ወረዳ፣ አሬሮ ወረዳና ሞያሌ ወረዳዎች ግጭቱ ተስፋፍቶ እስከ ሻቦ ድረስ ውጊያ መኖሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞያሌ ከተማ ባለው ግጭት ጣልቃ ገብተው ከ5 በላይ ሰዎችን ገድለዋል። በሌሎች ወረዳዎች በሚካሄደው የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የሚደርሰን መረጃ አመልክቷል።
ወደ ሞያሌ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ ተሽከርካሪዎች ማለፍ አልቻሉም።
በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል የሚካሄደው ግጭት ለወራት ቢቀጥልም፣ መከላከያ ሰራዊት ሊያስቆመው አልቻለም።
የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞያሌ ከተማ ባለው ግጭት ጣልቃ ገብተው ከ5 በላይ ሰዎችን ገድለዋል። በሌሎች ወረዳዎች በሚካሄደው የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የሚደርሰን መረጃ አመልክቷል።
ወደ ሞያሌ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ ተሽከርካሪዎች ማለፍ አልቻሉም።
በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት እና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል የሚካሄደው ግጭት ለወራት ቢቀጥልም፣ መከላከያ ሰራዊት ሊያስቆመው አልቻለም።
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ም/ል ፕሬዚዳንት ሊጠፉ ሲሉ ተያዙ
ምክትል ፕሬዚዳንቱ አቶ ምስጋናው አድማሱ አንድ የደህንነት ሰው አስከትለው ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ሊሰወሩ ሲሉ በደህንነት ሃይሎች ህዳር 13 ቀን 2010 ዓም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ቀደም ብለው በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ምስጋናው አድማሱ በአሁኑ ሰአት በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
የጉሙዝ ተወላጅ የሆኑት ም/ል ፕሬዚዳንቱ፣ እርሳቸው ዋና ፕሬዚዳንት ሆነው ለመሾም ተስፋ አድርገው በነበረበት ሰአት፣ ከእርሳቸው ስር የነበሩት የበርታው ተወላጅ አቶ አሻድሊ ሃሰን ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በመሾማቸው ሲበሳጩ ቆይተዋል ።
በክልሉ የስልጣን ድልድል መሰረት የፓርቲው ሊቀመንበር ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሲሆን፣ አዲሱ ተሿሚ ፕሬዚዳንት የፓርቲውንም የሊቀመንበርነት ቦታ ለመያዝ አጀንዳ ማቅረቡ ለሁለቱ የክልሉ ባላስልጣናት ጸበ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል።
ቀደም ብለው በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ምስጋናው አድማሱ በአሁኑ ሰአት በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
የጉሙዝ ተወላጅ የሆኑት ም/ል ፕሬዚዳንቱ፣ እርሳቸው ዋና ፕሬዚዳንት ሆነው ለመሾም ተስፋ አድርገው በነበረበት ሰአት፣ ከእርሳቸው ስር የነበሩት የበርታው ተወላጅ አቶ አሻድሊ ሃሰን ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በመሾማቸው ሲበሳጩ ቆይተዋል ።
በክልሉ የስልጣን ድልድል መሰረት የፓርቲው ሊቀመንበር ምክትል ፕሬዚዳንቱ ሲሆን፣ አዲሱ ተሿሚ ፕሬዚዳንት የፓርቲውንም የሊቀመንበርነት ቦታ ለመያዝ አጀንዳ ማቅረቡ ለሁለቱ የክልሉ ባላስልጣናት ጸበ ተጨማሪ ምክንያት ሆኗል።
ኦህዴድ በሃረሪ ክልል የነበሩ በርካታ ባለስልጣናትን ከስልጣን አነሳ
የአካባቢው ህዝብ ተደጋጋሚ ተቃውሞ ማድረጉን ተከትሎ ኦህዴድ በሃረሪ ክልል የሚገኙ ባለስልጣኖች አንስቷል። ከተነሱት ባለስልጣኖች መካከል የክልሉ የኦህዴድ ምክትል ሃላፊ አቶ ናስር መሃመድ፣ የሃረሪ ክልል ሲቪል ሰርቪስ ሃላፊ አቶ ሸሪፍ አህመድ ፣ የፖሊስ ም/ል አዛዡ ም/ል ኮሚሽነር ያሲን፣ ፣ የሸንኮር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሃይማኖት አሰፋ፣ የሸንኮር ወረዳ ጤና አስተባባሪ- አቶ ፈቃዱ ባቡሬ ፣ የሃኪም ወረዳ ፍትህና ጸጥታ ሃላፊ አቶ ከማል ፣ የሃኪም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ - አቶ አብዲ እና የአባድር ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ከድር ይገኙበታል። የሃረሪ ገቢዎች ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን ፉሪ፣ በ ወ/ሮ ሰሚራ ተተክተዋል።
የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ አባላት ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት ከችሎት እንዲነሱላቸው ለፍርድ ቤቱ በደብዳቤ ጠየቁ
በቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኙት አምስቱ የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ኮሚቴ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ መብራቱ ጌታሁን ዓለሙ፣ አቶ ጌታቸው አደመ ሰረጸ፣ አቶ አታላይ ዛፌ ገ/ማሪያም፣ አቶ አለነ ሻማ በላይ እና አቶ ነጋ ባንተይሁን በራ የ4ኛ ችሎት የግራ ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዲነሳ አቤቱታቸውን በፅሁፍ አስገብተዋል።
ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት በወልቃይት የአማራ ማንነት ላይ ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ አቋም ይዘው በሆርን አፍሪካ አፌር አማርኛ ድረገጽ ላይ አቋማቸውን አሳውቀዋል። ግለሰቡ የገዥው ፓርቲ ህወሃት አባልና የሆኑና በአመለካከታቸውም በሽብር ክስ ስም ከከሰሳቸው አቃቤ ሕግ የተለዩ ባለመሆናቸው ከእሳቸው ፍትሕ እንደማይጠብቁና ዳኛው ይቀየሩላቸው ዘንድ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት ላይ ተከሳሾች ችሎት ላይ አሰምተውት የነበረውን ተቃውሞ በጽሁፍ እንዲያቀርቡ ባዘዘው መሰረት በዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት የተጻፈውን 46 ገጽ ጽሁፍ አባሪ በማድረግ ከማመልከቻቸው ጋር ለፍርድ ቤቱ አስገብተዋል።
ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት በወልቃይት የአማራ ማንነት ላይ ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ አቋም ይዘው በሆርን አፍሪካ አፌር አማርኛ ድረገጽ ላይ አቋማቸውን አሳውቀዋል። ግለሰቡ የገዥው ፓርቲ ህወሃት አባልና የሆኑና በአመለካከታቸውም በሽብር ክስ ስም ከከሰሳቸው አቃቤ ሕግ የተለዩ ባለመሆናቸው ከእሳቸው ፍትሕ እንደማይጠብቁና ዳኛው ይቀየሩላቸው ዘንድ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ በዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት ላይ ተከሳሾች ችሎት ላይ አሰምተውት የነበረውን ተቃውሞ በጽሁፍ እንዲያቀርቡ ባዘዘው መሰረት በዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት የተጻፈውን 46 ገጽ ጽሁፍ አባሪ በማድረግ ከማመልከቻቸው ጋር ለፍርድ ቤቱ አስገብተዋል።
በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በመከላከያ አመራር ላይ ከፍተኛ ብወዛ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ
በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት ተከትሎ በመከላከያ አመራር ላይ ከፍተኛ ብወዛ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ። ብወዛው በተለይ የኦሮሞና አማራ ተወላጆች ላይ የተነጣጠረ መሆኑንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በጄኔራል መኮንኖች አካባቢ አመራሩ በሕወሃት ጄኔራሎች በመያዙ ብወዛው ከዚያ በመለስ ባለው የስልጣን መዋቅር ላይ ማተኮሩ ተመልክቷል። በመከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ በተጠናከረው ብወዛ በቅድሚያ የተሸጋሸጉ የ12 መኮንኖች ዝርዝር ለኢሳት ደርሶታል። በዚህም መሰረት ኮለኔል አበራ ለማ፣ኮለኔል ሙሉ ዘውዴ እንዲሁም ሻለቃ ደጀኔ ጉርሙ ከሰራዊቱ አመራርነት ተነስተው ወደ ሎጅስቲክ ተዛውረዋል። ሻለቃ ንጉሴ ኤጀርሳ፣ኮለኔል ደንቢ ገሪ፣እንዲሁም ኮለኔል ገረመው ሁንዴ ከሰራዊቱ አመራር ወደ ስልጠና ሲወሰዱ ኮለኔል ገዝሙ ደበላና ኮለኔል ሰለሞን ሁንዴ ወደ ምዕራብ እዝ አስተዳደር ክፍል ተሸኝተዋል። ኮለኔል አለሙ ቅጣቴ በኬንያ በኤምባሲው ስር ካለው ስውር የደህንነት መዋቅር ወደ አዲስ አበባ ወታደራዊ ደህንነት ሲዛወሩ ኮለኔል አለሙ ጨከነ ከሰሜን ዕዝ ተነስተው በተመሳሳይ ወደ ወታደራዊ ደህንነት ተልከዋል። ኮለኔል ስለሺ አሰፋና ኮለኔል አዱኛ ገርባ ከሰሜን ዕዝና ከማዕከላዊ ዕዝ የሰራዊቱ መደብ ተነስተው ወደ ትራንስፖርት ዘርፍ ተሸኝተዋል። በተመሳሳይ ኮለኔል ጀማል ሳህሌ ከወታደራዊ ደህንነት ተነስተው ወደ ትራንስፖርት ተዛውረዋል። ኮለኔል ቱሉ ኢርኮ ከወታደራዊ ዘመቻ መመሪያ ተነስተው ወደ ስታፍ ኮሌጅ ሲሔዱ ኮለኔል ቻሌ አየለም ከዘመቻ መምሪያ ወደ ሰላም ማስከበር
የኦሮሚያ ክልል ውሃ ሃብት ቢሮ ሜቴክ ከክልሉ የድንጋይ ከሰል በማውጣትና በመሸጥ ሲያከናውን የነበረውን ህገወጥ ድርጊት ማስቆሙን አስታወቀ
የኦሮሚያ ክልል ውሃ ሃብት ቢሮ ሜቴክ ከክልሉ የድንጋይ ከሰል በማውጣትና በመሸጥ ሲያከናውን የነበረውን ህገወጥ ድርጊት ማስቆሙን አስታወቀ። ቢሮው “ህገ ወጥ የሆነ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር በድብቅ ቢፈጸምም ከብዙሃኑ ህዝብ እይታ ግን ፈጽሞ ሊሰወር አይችልም” በሚል ባወጣው መግለጫ ሜቴክን ብቻ ሳይሆን የክልሉን ሃብት በመዝረፍ የተሰማሩ አካላት ላይ የምወስደውን ርምጃ እቀጥላለሁ ብሏል። የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/በሕግ ከተቋቋመበትና ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ከኦሮሚያ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ ነው ሲሉ በፓርላማ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንደገመገሙት ሰሞኑን መዘገባችን ይታወሳል። በምክረ ሃሳብ ነው የድንጋይ ከሰሉን ከክልሉ ማውጣት የጀመርኩት ያለው ሜቴክ ይህንን ምክረ ሃሳብ ያቀበሉት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚመክሯቸውና የሚያማክሯቸው ዶክተር አርከበ እቁባይ መሆናቸውን ገልጿል። ሜቴክ እየሰራው ያለው ስራ ህብረተሰቡን እያስቆጣ ነው በሚል ቋሚ ኮሚቴው ላነሳው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ላልፈለገው ሜቴክ ዛሬ ላይ ክልሉ ራሱ ንብረቴን መዝረፍ አትችልም ሲል ምላሽ ሰጥቶታል። ህገ-ወጥ የሆነ የኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር በድብቅ ቢፈጸምም፣ ከብዙሀኑ ህዝብ እይታ ግን ፈጽሞ ሊሰወር አይችልም በሚል የክልሉ ውሃ ሃብት ቢሮ ባወጣው መግለጫው አስታውቆታል።
ከሞያሌ በሳምንቱ መጀመሪያ የተሰወሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መክዳታቸውን ምንጮች ለኢሳት አረጋገጡ
ከሞያሌ በሳምንቱ መጀመሪያ የተሰወሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መክዳታቸውን ምንጮች ለኢሳት አረጋገጡ። የከዱት የሰራዊቱ አባላት ቁጥርም 38 እንደሆነ ምንጮቹ ገልጸዋል። እነሱን ለመፈለግ የወጣው ሃይልም አለመመለሱ ታውቋል። ሆኖም ለአሰሳ በወጣው ሃይል ውስጥ በተፈጠረ ውዝግብ አንድ ወታደር ሲገደል አንድ መቁሰሉን ምንጮቹ ተናግረዋል። ጥቃቱ የተፈጸመባቸው የኦሮሞ ተወላጅ ወታደሮች መሆናቸውም ተመልክቷል። በሳምንቱ መጀመሪያ ከሞያሌ ተነስተው ለአሰሳ የወጡት ወታደሮች ከ24 ሰአታት በላይ መሰወራቸውን ተከትሎ እነሱን የሚፈልግ አሳሽ ቡድን በቀጣዩ ቀን ተከትሎ ነበር። ይህ ሃይል የጠፉትን ወታደሮች ዱካ ሳያገኝ ሁለት ቀናት ያህል ከማሰነ በኋላ የቀደሙት ሆን ብለው
የሀዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ መምህራን ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተገለጸ።
የሀዋሳ ታቦር ሁለተኛ ደረጃ መምህራን ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ተገለጸ። መምህራንን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ በደቡብ ክልል መንግስት የወጣው መመሪያ ተፈጻሚ ሳይሆን ቤት እንዳገኘን ተደርጎ ሪፖርት መቅረቡና በመገናኛ ብዙሃን መነገሩ አስቆጥቶናል ያሉት መምህራን የአንድ ቀን ስራ በማቆም ወደክልሉ መስተዳድር በመሄድ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ተገልጿል። በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤት መምህራንም እንዲቀላለቀሉ ተጠይቋል። በሌላ በኩልም በዙር ሀዋሳ ለደረሰው የአባይ ዋንጫ መዋጮ መምህራን ገንዘብ አንሰጥም ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በግዴታ ከደመውዛቸው ለመቁረጥ መታቀዱንም ለማወቅ ተችሏል። ከአንድ ዓመት በፊት የደቡብ ክልል መንግስት አንድ አዋጅ ያወጣል። አዋጁ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ተብሎ የተቀረጸ ነበር። በአዋጁም መምህራን ሶስት አማራጮች ተሰጥቷቸው የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተባለ። ይሁንና አዋጁ ከወረቀት አልፎ መሬት ላይ መውረድ ሳይችል ከቆየ በኋላ የመንግስት ባለስልጣናት መምህራን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ሆነዋል የሚል ሪፖርት ማቅረባቸውንና ይህንንም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ማሰራጨታቸው በመምህራኑ ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል። በተለይ የሀዋሳ ታቦር ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ቤት እንዳገኙ ተደርጎ ሪፖርት
ጋብ ብሎ የነበረው በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር አካባቢ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ።
ጋብ ብሎ የነበረው በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድንበር አካባቢ ዳግም ግጭት ተቀሰቀሰ። በሞያሌ አቅራቢያ ቦርቦር በተባለው አካባቢ በተቀሰቀሰው በዚሁ ግጭት ከሁለቱ ወገኖች 27 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የህወሃት ልዩ ኮማንዶ በአካባቢው ከገባ በኋላ ግጭቱ እንደተቀሰቀሰ የጠቀሱት የኢሳት ምንጮች በግድያው ላይ የኮማንዶ ሃይሉ በቀጥታ መሳተፉንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል በአርሲ ነገሌ የመንግስት ካድሬዎች አቀናብረውታል በተባለ ጥቃት በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የኢሳት ምንጮች ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሏል። በአቅራቢያው የመከላከያ ሰራዊት የሚገኝ ቢሆንም ሊያስቆም እንዳልቻለ ተገልጿል። ከግማሽ ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉበት፣ በመቶዎች ለሚቆጠሩት መገደል ምክንያት የሆነው በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች መሀል የተፈጠረው ግጭት ያዝ ለቀቅ እያደረገው ቀጥሎ ሰሞኑን በሞያሌ አከባቢ መባባሱን ነው የኢሳት የመረጃ ምንጮች የገለጹት። በሞያሌ አቅራቢያ ቦር ቦር በተባለ ስፍራ ከሁለት ሳምንት በፊት የህውሃት ልዩ ሃይል መስፈሩን ተከትሎ በተቀሰቀሰው ግጭት ይህው የህወሃት ጦር ዋነኛ ተሳታፊ እንደሆነም ታውቋል። ልዩ የኮማንዶ ሃይሉ በካባቢው የሰፈረበት ምክንያት ባይታወቅም ወዲያኑ የወሰን ግጭት ተቀስቅሶ በርካታ ሰዎች መሞታቸውና የህወሃት ልዩ ወታደሮች ከገቡ በኋላ እንደአዲስ በተጀመረው ግጭት የ27 ሰዎች ህይወት ጠፍቷል። ኢሳት
Group claims responsibility for killing police commander
ESAT News (November 23, 2017)
An armed group took responsibility for the killing of a federal police commander for the north west region of Ethiopia in Bahir Dar on Tuesday.
Patriotic Ginbot 7, a group opposing the Ethiopian regime said in a statement that its forces had carried out the deadly attack on commander Desalegn Lijalem. The statement said the commander was stabbed to death by operatives of the group.
Trade Secretary fails British father on death row in Ethiopia
The International Trade Secretary, Liam Fox, has admitted he did not raise the case of a British father on death row in Ethiopia at an official meeting with the Ethiopian Prime Minister earlier this month, according to Reprieve, an international human rights organization that is following the case.
Asked directly about the case of
በኮማንደር ደሳለኝ ላይ ለተፈጸመው ግድያ አርበኞች ግንቦት7 ሃላፊነቱን ወሰደ
በባህርዳር ከተማ የፌደራል ፖሊስ አዛዥ በሆነው ኮማንደር ደሳለኝ ልጃለም ላይ ህዳር 12 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 4:45 በመኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ለተፈጸመው ግድያ ንቅናቄው ሃላፊነቱን ወስዷል። ግንባሩ ባወጣው መግለጫ የፖሊስ አዛዡ በከተማው ተካሂዶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ ከህወሀት የተሰጠውን መመሪያ በማስፈጸም ለበርካቶች ግድያና ስቃይ ተጠያቂ ነበር።
የኮማንደሩ አስከሬን ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ምርመራ ቢደረግለትም እጅግ ጥበብ በተሞላበት ድምፅ በሌለው መሳሪያ ጭንቅላቱ ላይ ሁለት ቦታ ተወግቶ ሊሞት ችሏል ። ኮማንደሩ በ ብአዴን 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ከልዩ እንግዶች ጋር የራት ግብዣ ላይ ተገኝቶ ካመሸ በሁዋላ የስንብት እርምጃ እንደተወሰደበት ግንባሩ ገልጿል።
የኮማንደሩ አስከሬን ከፈለገ ህይወት ሆስፒታል ምርመራ ቢደረግለትም እጅግ ጥበብ በተሞላበት ድምፅ በሌለው መሳሪያ ጭንቅላቱ ላይ ሁለት ቦታ ተወግቶ ሊሞት ችሏል ። ኮማንደሩ በ ብአዴን 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ከልዩ እንግዶች ጋር የራት ግብዣ ላይ ተገኝቶ ካመሸ በሁዋላ የስንብት እርምጃ እንደተወሰደበት ግንባሩ ገልጿል።
የአባይ ጉዳይ ለእኛም የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለጹ።
የአባይ ጉዳይ ለእኛም የሞትና የሽረት ጉዳይ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለጹ። ቃል አቀባዩ አቶ መለስ አለም የአባይ ግድብን በተመለከተ ከግብጽ ጋር ውጥረት መከሰቱን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ኢትዮጵያ በራሷ አቅም አባይን መገደቧን ትቀጥላለች። የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ በቅርቡ አንድ የአሳ ፋብሪካን ሲመርቁ አባይ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው ማለታቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ እየገነባች ባለችው የአባይ ግድብ የተነሳ ግብጽ ሰሞኑን ጠንካራና ጠጠር ያለ ቃላት በመወርወር ላይ ትገኛለች። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ፣ግብጽና ሱዳን መካከል የተጀመረው ውይይት እንከን ስለገጠመው መሆኑ ነው የተነገረው። ግብጽ በሶስትዮሹ ምክክር ከዚህ ቀደሞ የነበሩ የቅኝ ግዛት ውሎች ግምት ውስጥ ይግቡልኝ ስትል ኢትዮጵያና ሱዳን ሀሳቡን አልተቀበሉትም ነበር። እናም በዚሁ ሳቢያ እሰጣ ገባ የገቡት የሶስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በካይሮ ያካሄዱት ውይይት መቋረጡ ለሰጣ ገባው ምክንያት ሆኗል። የግብጹ ፕሬዝዳንት አልሲሲ ታዲያ የውይይቱን መቋረጥ ተከትሎ ማስጠንቀቂያ አዘል ሀሳብ ሰንዝረዋል። አልሲሲ በቅርቡ አንድ የአሳ ፋብሪካ በሀገራቸው ሲመርቁ እንዳሉት የአባይ ጉዳይ ለግብጽ የሞትና
የንግድ አጋሩን ለማስገደል ተንቀሳቅሷል በሚል የተወነጀለው ኢትዮጵያዊ በካናዳ ዊኒ ፔግ የ5 አመት አስራት ተፈረደበት
የንግድ አጋሩን ለማስገደል ተንቀሳቅሷል በሚል የተወነጀለው ኢትዮጵያዊ በካናዳ ዊኒ ፔግ የ5 አመት አስራት ተፈረደበት። በፖለቲካ ጥገኝነት በካናዳ የሚኖረው አቶ አማረ ገብሩ እስራቱን ሲጨርስ ከሀገር እንደሚባረርም ይፋ ሆኗል። ይህን ቤተሰቡን ያስደነገጠውን የማባረር ርምጃ ለማስቀረትም ጠበቆች እስራቱን በይግባኝ ለማስቀነስ በመሯሯጥ ላይ መሆናቸውን የካናዳው ሲ ቲ ቪ ኒውስና ዊኒ ፔግ ፍሪ ፕሬስ በዘገባቸው አመልክተዋል። አቶ አማረ ገብሩ ስሟ ካልተጠቀሰው የ31 አመት ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ጋር በጋራ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 የገዙት የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ በወራት ግዜ ውስጥ የውዝግብ መነሻ እንደሆናቸው ተመልክቷል። አማረ ገብሩ ውዝግቡን ተከትሎ ከአንድ የላውንደሪ ቤቱ ደንበኛ ጋር በመተባበር የንግድ አጋሩን ለማዘረፍ መንቀሳቀሱ በኋላም ይህንን ሀሳቡን በመለወጥ ለማስገደልና ለገዳዩም 10 ሺ ዶላር ለመክፈል ማሴሩን የፍርድ ሂደቱን
Wednesday, November 22, 2017
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዘርአይ አስገዶምን ዘረኛና ጎጠኛ ሲሉ የፓርላማ አባላት አወገዙ። አባላቱ ኢሕአዴግን ተጠልሎ ዘረኝነትን በኦፊሴላዊ ደረጃ ማራመድ፣ስልጣንን ማሳነስና የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈት ተጠያቂ ያደርጋል ብለዋል። የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤትም ሆነ በቃል አቀባዩ የሚወክሉት መንግስትን የሚያንጸባርቁትም የመንግስትን አቋም ነው ብለዋል አባላቱ። የመንግስት ኮሚኒኬሽኝ ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ህዳር 11/2010 ለፓርላማው የባህል፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሩብ አመት አፈጻጸማቸውን
መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶች በብቸኝነት ሲሚንቶ ማቅረብ የቻልኩት ልዩ ሲሚንቶዎችን በብቸኝነት የማመርት በመሆኔ ነው አለ።
መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለመንግስት ትላልቅ ፕሮጀክቶች በብቸኝነት ሲሚንቶ ማቅረብ የቻልኩት ልዩ ሲሚንቶዎችን በብቸኝነት የማመርት በመሆኔ ነው አለ። የኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው መሶቦ ሲሚንቶ ለግዙፍ ፕሮጀክቶቹ በብቸኝነት እንዲያቀርብ የተደረገው ግዙፉ የሙገር ሲሞንቶ ፋብሪካ በህወሃት ስርዓት በተለያየ መንገድ የማምረት አቅሙ እንዲዳከም ከተደረገ በኋላ መሆኑ ይታወቃል። በህወሃት ንብረትነት የሚተዳደረው ኤፈርት ኩባንያ አካል የሆነው የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ በ2009 ብቻ በኢትዮጵያ ለተከናወኑ የፕሮጀክት ግንባታዎች 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ቶን ሲሚንቶ ማቅረቡን አስታውቋል።
የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ክብረአብ ተወልደ ፋብሪካው ይህን ማድረግ በመቻሉ የኢትዮጵያን የሲሚንቶ ገበያ 23 በመቶ መቆጣጠር እንደቻለ ተናግረዋል። መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የሃገሪቱ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የሚፈልጉትን የሲሚንቶ አይነት በብቸኝነት ማቅረብ የቻለው የሚፈልጉትን የሲሚንቶ አይነት በብቸኝነት በማምረቱ እንደሆነ ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል። ለግልገል ጊቤ ቁጥር 3 የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ወደ 1
በሞያሌ ከትላንት በስቲያ የተሰወሩትን ወታደሮች ለመፈለግ የወጣው አሳሽ ቡዳን ዛሬም ፍለጋውን መቀጠሉ ተገለጸ
በሞያሌ ከትላንት በስቲያ የተሰወሩትን ወታደሮች ለመፈለግ የወጣው አሳሽ ቡዳን ዛሬም ፍለጋውን መቀጠሉ ተገለጸ። ከ30በላይ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ከተሰወሩ በኋላ በ10ኛው ክ/ጦር ባሉ ወታደሮች ዘንድ ውጥረት ነግሷል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የሬዲዮ መገናኛ ኦፕሬተር መታሰሩን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ወታደሮቹ ከተሰወሩ በኋላ በክ/ጦሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ በሆኑ የሰራዊቱ አባላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንንም ለማወቅ ተችሏል። ከትላንት በስቲያ ሰኞ ነው። በ10ኛ ክፍለጦር ውስጥ ከሚገኙ 3ሻለቃ መምሪያዎች በአንደኛው ያለ የጋንታ ሃይል ለመደበኛ ቅኝት ይወጣል። ከ30 በላይ የሚሆኑ አባላት ያሉት የጋንታ አመራር ሙሉ ትጥቁን እንደያዘ ከሞያሌ ምድብ ቦታው ተነስቶ አካባቢውን ሊያስስ ሲወጣ የሚመለስበት ሰዓት የሚታወቅ ነበር። ይሁንና በተባለው ሰዓት የጋንታው አመራር ወደ ካምፑ አልተመልሰም። ግንኙነቱ ከማዘዣው ኮማንድ ሃይል ጋር መቋረጡ የታወቀው ትላንት በዕለቱ እንደነበርም ከኢሳት የመረጃ ምንጮች ለማወቅ ተችሏል። ሌላ አሳሽ ግብረሃይል ተመድቦ ከትላንት ቀትር በኋላ ጀምሮ መላኩን የገለጹት የኢሳት ምንጮች እስከዛሬ ድረስ የጋንታው ሃይል እንዳልተገኘ ለማወቅ ተችሏል። ከነሙሉ ትጥቁ የተሰወረው የጋንታ ሃይል የት እንደገባ ሳይታወቅ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል። በመከላከያው የህወሃት አዛዦች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረው የወታደሮቹ መሰወር በ10ኛ ክፍለጦር ውስጥ ውጥረት ማንገሱ የተገለጸ ሲሆን ዛሬ የ10አለቃ ረጋሳ የተባሉ የመገናኛ ኦፕሬተር መታሰራቸውን
በባሌ ጎባ በህወሃት መንግስት አማካኝነት የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚደረገውን እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ እንዲያከሽፈው ተጠየቀ።
በባሌ ጎባ በህወሃት መንግስት አማካኝነት የእርስ በርስ ግጭት ለመፍጠር የሚደረገውን እንቅስቃሴ ህብረተሰቡ እንዲያከሽፈው ተጠየቀ። የጎባ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የህዝቡን ተቃውሞ በማሳነስ ያደረጉት ንግግር ቁጣን ቀስቅሷል። ምክትል አስተዳዳሪዋ ጥቃት እንዳይደርስባቸው በመንግስት ወታደሮች ጥበቃ እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል። ይህን የህዝብ ቁጣ ለማስቀየስ በህዝቡ መሀል ሃይማኖትንና ብሄርን መነሻ ያደረገ ግጭት ለመቀስቀስ በመንግስት በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ካለፈው ሰኞ ህዳር 11 ጀምሮ የባሌ ጎባ ነዋሪዎች በስጋት ውስጥ ናቸው።
በተለይም በከተማዋ ነባር የሆኑና ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ነዋሪ ሆነው ለዘመናት የቆዩ ኢትዮጵያውያን በመንግስት በተቀነባበረ ጥቃት የተነሳ ያለፉትን ሁለት ቀናት በፍርሃትና ጭንቀት እንዳሳለፉት ለኢሳት ገልጸዋል። የጥቃቱ መነሻ ደግሞ የጎባ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት ወ/ሮ
ከአገሪቱ ኢኮኖሚ መዳከም ጋር ተያይዞ የገንዘብ እጥረት እያጋጠመ መሆኑን መረጃዎች አመለከቱ
ካለፉት 2 ዓመታት ጀምሮ በተከታታይ የተደረገውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የአገሪቱ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ በመዳከሙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የበጀት እጥረት እያጋጠማቸው ነው።
ቀድም ብሎ በአገሪቱ ለታዬው አንጻራዊ የኢኮኖሚ እድገት ዋና መንስኤ ተድርጎ ይቆጠር የነበረው የግንባታ እንቅስቃሴው በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሟል። በርካታ ተቋራጮች በደረሰባቸው የኢኮኖሚ ኪሰራ ሰራተኞቻቸውን እየተበኑ ነው። የቱሪዝም ፍሰቱም እንዲሁ በእጅጉ ተዳክሟል። ከቡና በመቀጠል ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገቢ ያስገኝ የነበረው የጫት ሽያጭ በኦሮምያና ሶማሊ ክልሎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በመቋረጡ በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ተጽኖ አሳድሯል። በርካታ ባለሃብቶች በአገሪቱ የሚታየውን አለመረጋጋት ተከትሎ ሃብታቸውን ማሸሻቸው እንዲሁም በስልጣን ላይ ያሉት ባለስልጣናትና ወታደራዊ አዛዦች በከፍተኛ ሁኔታ በኮንትሮባንድ ንግድ ሃብት ለማፍራት የሚያደርጉት እሩጫ፣ ኢኮኖሚውን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድቶታል። በተለይ ነጋዴዎች ግብር አንከፍልም በማለት እያደረጉት ያለው አድማ፣ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዲፈጠር አድርጎታል።
Tuesday, November 21, 2017
Ethiopia: Protest continues in South against regime, mining deal
ESAT News (November 20, 2017)
People in Southern Ethiopia are protesting the regime for keeping them in poverty and political and economic marginalisation. They also reject a billionaire whom they said had extracted gold for over 20 years but did nothing for the community.
Residents of the town of Dima followed the footsteps of those in Shakiso and Adola and took to the streets in thousands to denounce the TPLF regime.
የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜቴክ/ የተጀመሩ የስኳር ፕሮጀክቶችን ያላጠናቀቁት የአቅም ችግር ስላለብኝ ነው አለ
የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜቴክ/ የተጀመሩ የስኳር ፕሮጀክቶችን ያላጠናቀቁት የአቅም ችግር ስላለብኝ ነው አለ። የተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በበኩሉ የሜቴክ ውጫዊ ምክንያቶች በዝተዋል እኔም በሜቴክ ጉዳይ ተሰላችቻለሁ ሲል ተናግሯል። የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜቴክ/ በየጊዜው በግዴታም ይሁን በማስገደድ አልፎ አልፎም በውይይት የሚወስዳቸው ፕሮጀክቶች ብዛት በርካታ ናቸው። ነገር ግን ሜቴክ እንደሚወራለትና እሱም እሰራቸዋለሁ ብሎ የተቋሙን ስም ከፍ አድርጎ እንደሚሰቅለው የሆነለት አይመስልም።
Monday, November 20, 2017
የሁሌ ቦራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጡ
ለሳምንታት ትምህርታቸውን አቋርጠው የቆዩ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ለጥያቄያቸው መልስ የሚሰጣቸው አካል ማጣታቸውን ተከትሎ ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2010 ዓም ዩኒቨርስቲውን ለቀው ወጥተዋል፡
ተማሪዎቹ አቶ ለማ መገርሳ መጥቶ እንዲያነጋግራቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የመከላከያ አባላት ወደ ግቢያቸው ገብተው ደብደብዋቸው ነበር። ይህን ተከትሎ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም ትምህርት በማቆም ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የተደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ ዛሬ ዩኒቨርስቲውን ለቀው ወጥተዋል።
ተማሪዎቹ አቶ ለማ መገርሳ መጥቶ እንዲያነጋግራቸው ጥያቄ አቅርበው ነበር። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የመከላከያ አባላት ወደ ግቢያቸው ገብተው ደብደብዋቸው ነበር። ይህን ተከትሎ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም ትምህርት በማቆም ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የተደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ ዛሬ ዩኒቨርስቲውን ለቀው ወጥተዋል።
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረቡት የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በግራ ዳኛው መዳኘት አንፈልግም ሲሉ ተቃውሞአቸውን አሰሙ
በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረቡት የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በግራ ዳኛው መዳኘት አንፈልግም ሲሉ ተቃውሞአቸውን አሰሙ። ሌሎች በችሎቱ የነበሩ ተከሳሾችም የመንግስትን አቋሚ በሚያንጸባርቁትና የሕወሃት የፖለቲካ አራማጅ በሆኑት ዘርአይ ወልደሰንበት አንዳኝም በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ከተከሳሾቹ የተነሳው ጥያቄ ትክክል መሆኑንና እንደዚህ አይነት አቋም ያለው ዳኛ ተከሳሾቹ ቅሬታ ከማቅረባቸው በፊት ራሱ ነበር ይህን ጉዳይ መዳኘት አልችልም ማለት ያለበት። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የዛሬ የፍርድ ቤት ውሎው ሰላማዊ አልነበርም ይላሉ በችሎቱ ላይ የተገኙት ታዛቢዎች። በተለይ የችሎቱ የግራ ዳኛ ዘርአይ ወልደሰንበት ተከሳሾችን የመዳኘት አቅምም ሆነ መብት የላቸውም በሚል የተነሳው ተቃውሞ ፍርድ ቤቱን ያንቀሳቀሰና የበርካቶችን ድምጽ ያሰማ ሆኗል። ጉዳዩ እንደዚህ ነበር ይላሉ ታዛቢዎቹ የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት አቶ አታላይ ዛፌን በማስቀደም ተቃውሞ አሰምተዋል። የተቃውሞአቸው ዋነኛ መነሻም በግራ በኩል የተሰየሙትና ዘርአይ ወልደሰንበት የሚባሉት ዳኛ በማህበራዊ ድረገጾችና በቴሌቪዥን ጭምር በመቅረብ ወልቃይት የትግራይ ነው የሚል አቋማቸውን የሚያንጸባርቁ ግለሰብ ናቸው። ይህንን አቋማቸን ይዘው ደግሞ እኛን ሊዳኙን አይገባም የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት ጥያቄ ነው።
ሜቴክ በአቶ አርከበ እቁባይ ትዕዛዝ ከኦሮሚያ ክልል በህገወጥ መንገድ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ እንደሆነ በፓርላማ ተገለጸ
ሜቴክ በአቶ አርከበ እቁባይ ትዕዛዝ ከኦሮሚያ ክልል በህገወጥ መንገድ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ እንደሆነ በፓርላማ ተገለጸ። ጥሬ ሐብቱ እየተበዘበዘበት ያለው ህዝብም ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ነው። በሕወሃቱ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/በሕግ ከተቋቋመበትና ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ከኦሮሚያ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ መሆኑ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የሜቴክን የ2010 በጀት አመት እቅድና አንደኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ሲገመግሙ ኮርፖሬሽኑ በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን ያዩ ወረዳ የድንጋይ ከሰል ከስልጣኑ ውጪ በማውጣት እየሸጠ መሆኑ ሕብረተሰቡን ቅሬታ ውስጥ እንደከተተው ተናግረዋል። የቋሚ ኮሚቴው አባላት ሜቴክ ከተቋቋመበት አላማ ውጪ የድንጋይ ከሰል እያመረተ በመሸጥ ላይ መሆኑ ከአካባቢው ህብረተብ ጋር ቅራኔ ውስጥ እያስገባው ነው። ይህንን ስራ ሜቴክ እንዲሰራ የተቋቋመበት ህግ የፈቅድለታል ወይ
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ታወቀ
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ታወቀ። ለአንድ ሳምንት ትምህርት አቁመው ጥያቄያቸው እስኪመለስ ቢጠብቁም ምላሽ ባለማግኘታቸው ግቢውን ሙሉ በሙሉ ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ የታጠቁ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ግቢው ዘልቀው በመግባት ተማሪዎችን እየደበደቡ መሆናቸውም ታውቋል። በመቱ ዩኒቨርሲቲ ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች አልተመለሱም። በግቢው የቀሩትም ትምህርት አለመጀመራቸው ታውቋል። ከአንድ ሳምንት በላይ ትምህርት አቋርጠው የቆዩ የቡሌ ሆራ (ሀገረማርያም) ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ መጥተው እንዲያናግሯቸው ጠይቀው ሲጠብቁ ነበር። ፕሬዝዳንቱ አልመጡም። የሚወክላቸውን ሰውም አላኩም። የአስተዳደር ጥያቄን ጨምሮ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል የሚያደርሰውን ጥቃት በመቃወም የቆዩት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለጥያቄያቸው መልስ የሚሰጣቸው አካል ማጣታቸውን ተከትሎ ዛሬ ህዳር 11/2010 ዩኒቨርስቲውን ለቀው መውጣታቸውን የኢሳት ምንጮች ከስፍራው ካደረሱን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከሌሊቱ 7 ሰዓት ላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ ዩኒቨርሲቲው ቅጥር ገብተው ተማሪዎችን መደብደባቸውን ተከትሎ በቡሌ ሆራ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም ትምህርት በማቆም ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ድጋፋቸውን መግለጻቸው የሚታወስ ነው። ተማሪዎች ትምህርት እንዲጀምሩ ለማድረግ የተደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ ዛሬ
የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ነባር ታጋዮች በንቅናቄው 37ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ተገለጸ
የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ነባር ታጋዮች በንቅናቄው 37ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ተገለጸ። በግብርና ስራ የተሰማሩና በኑሮ የተጎሳቆሉት የቀድሞ የንቅናቄው ታጋዮች ዛሬ የታወስንበት ምክንያት ሊገለጽልን ይገባል የማለት ተቃውሞ ማቅረባቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ብአዴን የተመሰረተበትን 37ኛ ዓመት ሲያከብር በመርሃግብር ከያዛቸው መርሃ ግብሮች አንዱ ለንቅናቄው ነባር ታጋዮች እውቅናና የምስክር ወረቀት መስጠት ነበር። ይሁንንና የትም ወድቀው የቀሩና ብዙዎች በድህነት ተሰቃይተው የሞቱ መሆናቸውን የገለጹ አንዳንድ ነባር ታጋዮች ለዘመናት ተዘንግተን ዘንድሮ የምንታወስበትን ምክንያት ስላላወቅን በበዓሉ ላይ አንገኝም በማለት መቅረታቸው ታውቋል። በተለይ በሰሜን ጎንደር በግብርና ስራ የተሰማሩ ነባር ታጋዮች አብዛኞቹ በዓሉን አንካፈልም በማለት ማደማቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ለኢሳት በደረሰው መረጃ መሰረት ነባር ታጋዮችን ለመሸለም በተያዘው መርሃግብር ምትክ የብአዴን የሊግና ፎረም አባላት የሆኑ ወጣቶች የምስክር ወረቀት
በጎንደር ከተማ በተካሄደው የአማራና የትግራይ ተወላጆች የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት አቶ በረከት ስምኦን ሁሉም ብሔረሰብ የራሱን ክልል እያስተዳደረ የሚገኝበት የእኩልነት ስርአት ገንብተናል ሲሉ ተነገሩ
በጎንደር ከተማ በተካሄደው የአማራና የትግራይ ተወላጆች የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት አቶ በረከት ስምኦን ሁሉም ብሔረሰብ የራሱን ክልል እያስተዳደረ የሚገኝበት የእኩልነት ስርአት ገንብተናል ሲሉ ተነገሩ። በዚሁ መድረክ ኢሳትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ተወግዘዋል። የአማራ ተወላጆች ልጆቻቸው ለተቃውሞ አደባባይ እንዳይወጡ ይሰበስቡ ዘንድም ጥሪ ቀርቦላቸዋል። “አብሮነታችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በጎንደር ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ በረከት ስምኦን በስርአቱ ላይ የተነሱ ተቃውሞዎች አዲስ አበባ ጫፍ መድረሳቸውን በማመን ችግሩ ግን የፌደራል ስርአቱ ያስከተለው ወይንም የውጭ እጅ የፈጠረው ሳይሆን ስልጣን ላይ ባለው አመራር የተከተለ እንደሆነ አመልክተዋል። በዚህም መንግስት በቅርቡ ይፋ ካደረገው የደህንነት ፖሊሲ ሰነድ ጋር የሚቃረን ሀሳብ አንጸባርቀዋል። በሰነዱ የችግሩ ዋና ምንጭ ተብለው የተጠቀሱት የግብጽና የኤርትራ መንግስት መሆናቸው ይታወቃል። አቶ በረከት በዚሁ መድረክ ሁሉም አካባቢውን ራሱ የሚያስተዳድርበት
Ethiopia: University students leave campus in protest
ESAT News (November 20, 2017)
University students in the east, south and south west of Ethiopia continue to leave their campuses en mass protesting the intervention of the regime in their academic as well as daily lives.
Students of Haromaya University in Eastern Ethiopia have reportedly left their campus today after their demands to the school administration fell on deaf ears. One of the demand by the students was to banish a so called “peace forum,” which they
ተከሳሾች ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዲነሱላቸው ጥያቄ አቀረቡ
“እሱ ተከራካሪ፣ እሱ መልዕክት አስተላላፉ፣ እሱ ዳኛ ሊሆን አይችልም” አቶ አታላይ ዛፌ
“የተከሰሳችሁት በወልቃይት አማራ ማንነት ነው ወይስ በሽብርተኝነት የሚለው የሚታይ ይሆናል” ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት
“እኚህ ዳኛ በማህበራዊ ሚዲያ ያቀረቡት የህወሓትን አቋም ነው” ዘመነ ጌቴ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የግራ ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት ሊዳኙን አይገባም ሲሉ ተከሳሾች ጥያቄ አቅርበዋል። ዛሬ ህዳር 11/2010 ዓም የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በአቶ አታላይ ዛፌ አማካኝነት በዳኛው ላይ ተቃውሟቸውን ሲያቀርቡ በግንቦት 7 እና ኦነግ ክስ የቀረበባቸው ሁሉም ችሎት ውስጥ የነበሩ ተከሳሾች ጥያቄው የሁላችን ነው በማለት ቆመው ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። ወልቃይት አማራ ነው ብለው በህገ መንግስቱ መሰረት ጥያቄያቸውን
Friday, November 17, 2017
የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ፣ በወታደሮች ታጅቦ ይጓዝ በነበረ መኪና ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገለጹ
ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 12 :48 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጓንግ ወንዝ ድልድይ ከመድረሱ በፊት 100 ሚትር ሲቀረው መታጠፊያ ቦታ ላይ በህወሓት ወታደሮች ከፊትና ከኃላ ታጅቦ ሲጓዝ በነበረ ነዳጅ በጫነ ቦቴ መኪና ላይ በተፈፀመ ጥቃት ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ አስከ ጫነው ነዳጅ ሲወድም በአሽከርካሪው እና በሚያጅቡት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡
Thursday, November 16, 2017
በንግስት ይርጋ ላይ የተፈፀመ ጭካኔ
(በጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው)
መስከረም 5/2009 ዓም ከምሽቱ 1:00 ሳንጃ ከተማ የተያዝኩ ሲሆን ወዲያውኑ እንደተያዝኩ በተፈፀመብኝ ድብደባ አእምሮዬን በመሳቴ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዴትና በምን እንደመጣሁ ሳላውቅ መስከረም 6/2009 ዓም ከጠዋቱ 4:00 ላይ የፌደራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በሰው ተደግፌ እና በጭቃ ተለውሼ ስቀርብ ማስታወስ ጀመርኩ። በጭካኔ በዱላ ተቀጥቅጬ መቁሰሌ እየታየ ወደ ሀኪም ቤት በመውሰድ ፋንታ ወዲያውኑ ወደፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተወስጄ እንደገና ለ3 ቀናት ራሴን ሳላውቅ ቆይቼ በ4ኛው ቀን ቁስሌ እና በጭቃ የተለወሰውን ገላዬን በምርመራ ቢሮው ውስጥ የነበሩ ሴት እስረኞች እንዲያጥቡልኝ ከተደረገ በኋላ እንደገና ሌላ ጭካኔ የተሞላበት ተግባር ተፈፅሞብኛል።
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ስለ ኮነሬል መንግስቱ ሀይለማርያም እና ዙምባብዌ!
የቢሮ ስልኬን አነሳሁ። ወደ ሀራሬ ደወልኩ። ከወዲያ ማዶ ትህትና የተሞላበት የእመቤት፡ ወይዘሮ፡ የእናትነት ግርማ ሞገስ የተላበሰ፡ ረጋ ያለ ድምጽ ተሰማኝ። ይሄን ድምጽ አውቀዋለሁ።
''ጤና ይስጥልኝ ማን ልበል?''
''ጤና ይስጥልኝ ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻው። መሳይ እባላለሁ። ከኢሳት ዋሽንግተን ቢሮ ነው የምደውለው።''
''እሺ የእኔ ጌታ። ደህና ናችሁ?''
''ጤና ይስጥልኝ ማን ልበል?''
''ጤና ይስጥልኝ ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻው። መሳይ እባላለሁ። ከኢሳት ዋሽንግተን ቢሮ ነው የምደውለው።''
''እሺ የእኔ ጌታ። ደህና ናችሁ?''
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ስለምደውል አልረሱኝም። ትህትናቸው ይገድላል። ለጠብ የመጣን በፍቅር ማርኮ ይመልሳል። የቀድሞዋ ቀዳማይ እመቤትን ዘመን አልቀየራቸውም። ርቀት አለወጣቸውም። ደርበብ ያሉ ኢትዮጵያዊ እመቤት። ወ/ሮ አዜብ መስፍን ትዝ አሉኝ። ማወዳደር ይከብዳል።
Ethiopia: TPLF central committee in deadlock, some members walk out of marathon crisis meeting
by Engidu Woldie
ESAT News (November 16, 2017)
ESAT News (November 16, 2017)
Reports reaching ESAT say a marathon meeting by the central and executive committees of the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) continues in Mekelle despite a deadlock.
Increasing number of members of the central committee are also walking out of the crisis meeting, according to ESAT sources. Azeb Mesfin, the widow of Meles Zenawi, who had controlled the party with iron fist, has reportedly walked out of the meeting yesterday and never returned.
One of the the focus of the meeting, that began early October, was a discussion on a 59 page document presented by the leadership which
በአማራና በትግራይ አስተዳደሮች በሕዝብ ስም የተጠራው የግንኙነት መድረክ የሕወሃትን ስልጣን ለማራዘም የታቀደ በመሆኑ እናወግዛለን ሲል የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ልሳነ ግፉአን ማህበር ገለጸ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 7/2010)በአማራና በትግራይ አስተዳደሮች በሕዝብ ስም የተጠራው የግንኙነት መድረክ የሕወሃትን ስልጣን ለማራዘም የታቀደ በመሆኑ እናወግዛለን ሲል የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ልሳነ ግፉአን ማህበር ገለጸ። የማህበሩ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት የአማራን ሕዝብ በጠላትነት የፈረጀው ሕወሃት ሳይወገድ ከትግራይ ሕዝብ ጋር ድርድር ማድረግ ከጠላት ጋር እንደመተባበር ይቆጠራል። እናም የአማራ ሕዝብ ወልቃይትን ጨምሮ በሕወሃት የተወሰደበት መሬት እስኪመለስና በአገዛዙ የደረሰበት በደል እስኪወገድ ድረስ ትግሉን እንዲቀጥል ልሳነ ግፉአን ጥሪ አቅርቧል። በትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የተመራ የልኡካን ቡድን ነገ አርብ ይጀመራል ተብሎ በሚጠበቀው መድረክ ለመገኘት ጎንደር ይገባል። የትግራይና የአማራ ክልሎች አስተዳደሮች ባዛጋጁት መድረክ ላይም ከ1 ሺ በላይ ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለውጥ የሚጠይቁ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች ቁጥር እየጨመረ ነው
ከመከላከያ ሰራዊት የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በመከላከያ ውስጥም ሆነ አጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ ለውጥ የሚጠይቁ የመከላከያ አዛዦች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው። በቅርቡ በተካሄዱ የመከላከያ ግምገማዎች ላይ በርካታ መኮንኖች አገዛዙ የሚከተለው ፖሊሲ አገሪቱን አደጋ ውስጥ የሚጥልና ግጭቶችንም የሚያበብስ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ ለውጥ ሊመጣ ይገባዋል ብለዋል።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተካሄዱት ተቃውሞዎች ወታደሮች ግራ መጋባታቸውን የገለጹት አዛዦች፣ ህዝባዊ ድጋፍ አለኝ የሚል መንግስት እንዴት ይህን ያክል ተቃውሞ ሊገጥመው ቻለ የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል። የመከላከያው ሚና ምን መሆን አለበት የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል። መከላከያው ድንበር መጠበቁን ትቶ በየጎጡ መሰማራቱ ከአገራዊ ተልእኮው ጋር የሚጋጭ
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተካሄዱት ተቃውሞዎች ወታደሮች ግራ መጋባታቸውን የገለጹት አዛዦች፣ ህዝባዊ ድጋፍ አለኝ የሚል መንግስት እንዴት ይህን ያክል ተቃውሞ ሊገጥመው ቻለ የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል። የመከላከያው ሚና ምን መሆን አለበት የሚሉ ጥያቄዎችም ተነስተዋል። መከላከያው ድንበር መጠበቁን ትቶ በየጎጡ መሰማራቱ ከአገራዊ ተልእኮው ጋር የሚጋጭ
በደቡብ ክልል ለአባይ ግድብ መዋጮ እንዳይሰበሰብ የሚቀሰቅሱት የአማራ ተወላጆች ናቸው በሚል ጥቃት ይፈጸምብናል ብለው እንደሚሰጉ መምህራን ገለጹ
(ኢሳት ዜና ህዳር 6 ቀን 2017 ዓም)
በሲዳማ ዞን ይርጋዓለም ከተማ ለአባይ ግድብ መዋጮ አንከፍልም ያሉ መመህራን ስጋት ላይ መውደቃቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። መምህራን በብሄራቸው ሰበብ ጥቃት
የይርጋአለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት መምህራን ከኑሮዋቸው ጋር በማማያዝ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለመክፈል እንደማይችሉ አቋማቸውን ግልጽ ካደረጉ በሁዋላ፣ የአካባቢው ካድሬዎች ወደ ሌሎች ክልል ተወላጆች መመህራን በመሄድ፣ “ ለግድቡ መዋጮ እንዲከፈል የማይፈልጉ እንዲሁም በክልሉ አመጽ እንዲቀሰቀስ የሚፈልጉ አማሮች በመሆናቸው ተጠንቀቁ” እያሉ በመናገር ላይ መሆናቸውን መምህራኑ ገልጸዋል።
በሲዳማ ዞን ይርጋዓለም ከተማ ለአባይ ግድብ መዋጮ አንከፍልም ያሉ መመህራን ስጋት ላይ መውደቃቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። መምህራን በብሄራቸው ሰበብ ጥቃት
የይርጋአለም ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤት መምህራን ከኑሮዋቸው ጋር በማማያዝ ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለመክፈል እንደማይችሉ አቋማቸውን ግልጽ ካደረጉ በሁዋላ፣ የአካባቢው ካድሬዎች ወደ ሌሎች ክልል ተወላጆች መመህራን በመሄድ፣ “ ለግድቡ መዋጮ እንዲከፈል የማይፈልጉ እንዲሁም በክልሉ አመጽ እንዲቀሰቀስ የሚፈልጉ አማሮች በመሆናቸው ተጠንቀቁ” እያሉ በመናገር ላይ መሆናቸውን መምህራኑ ገልጸዋል።
የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ምደባ አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር እየተጠቀመበት ያለውን አሰራር እንደማይቀበሉት አስታወቁ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 7/2010)የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ምደባ አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴር እየተጠቀመበት ያለውን አሰራር እንደማይቀበሉት አስታወቁ። የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው መመሪያ የአንድ ሀገር ህዝቦችን የሚነጣጥልና የፌደራሊዝም ስርአቱን የሚያበላሽ ነው ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተነሳ ግጭት በርካቶች ሕይወታቸውን አጥተዋል።በሺዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። አሁን ላይ በሁለቱ ህዝቦች መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትና ከቀያቸው የተፈናቀሉትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት የትምህርት ሚኒስቴር ያወጣው አዲስ መመሪያ ሌላ የመነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል። መመሪያው የኦሮሞ ክልል ተወላጆች በሶማሌ ክልል፣የሶማሌ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ደግሞ በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች እንዳይመደቡ የሚያዝ ነው። ይህንን መመሪያ ደግሞ የሶማሌ ክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በፍጹም እንደማይቀበሉትና መመሪያውንም እንደማያምኑበት ነው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት። እሳቸው እንደሚሉት ከሆነ የኦሮሞ ተማሪ ጅግጅጋ
የአርባምንጭ ደን እየተመናመነ ነው ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ
(ኢሳት ዜና ህዳር 6 ቀን 2017 ዓም)
የከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የተለያዩ የእጽዋትዝርያና የዱር እንስሳት የሚገኙበት የአርባ ምንጭ ደን እየወደመ በመገኘቱ የከተማዋ ነዋሪዎች ስጋት ላይ ወድቀዋል። በቀን ውስጥ እስከ 2 ሺ የሚጠጉ ዛፍ ቆራጮች በጫካው ተሰማርተው በዘፈቀደ እንደሚቆርጡ የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ እነዚህ ግለሰቦች የሚቆርጡትን ዛፍ በከተማዋ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ እስር ቤቶችና ሌሎችም ድርጅቶች በመግዛት እየተጠቀሙበት ነው። በዚህም የተነሳ የደኑ መጠን እየተመናመነ በአካባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ መዛባት እያስከተለ ነው።
የከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት የተለያዩ የእጽዋትዝርያና የዱር እንስሳት የሚገኙበት የአርባ ምንጭ ደን እየወደመ በመገኘቱ የከተማዋ ነዋሪዎች ስጋት ላይ ወድቀዋል። በቀን ውስጥ እስከ 2 ሺ የሚጠጉ ዛፍ ቆራጮች በጫካው ተሰማርተው በዘፈቀደ እንደሚቆርጡ የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ እነዚህ ግለሰቦች የሚቆርጡትን ዛፍ በከተማዋ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ እስር ቤቶችና ሌሎችም ድርጅቶች በመግዛት እየተጠቀሙበት ነው። በዚህም የተነሳ የደኑ መጠን እየተመናመነ በአካባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ የተፈጥሮ መዛባት እያስከተለ ነው።
በቃሊቲ እስር ላይ የሚገኘው ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል የጤና ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተነገረ።
(ኢሳት ዜና ህዳር 6 ቀን 2017 ዓም) ከዓመታት በፊት የሙስሊሞችን መብት ለማስከር በሕዝብ ምርጫ ከተቋቋመው የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት አንዱ ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ነው።የኮሚቴው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመሆን ሲያገለግል የነበረው አንደበተ ርቱኡ አህመዲን ጀበል በህወኃት አገዛዝ የሀሰት የሽብርተኝነት ክስ ከተመሰረተባቸው የኮሚቴው አባላት መካከል አንዱ ሲሆን፣ የ18 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ወደ ወህኒ ከተጋዘ አምስት ዓመታት ተቆጥረዋል።ባለፉት አምስት ዓመታት የእስር ቤት ቆይታው ሦስት መጻህፍትን ጽፎ ያሳተመው ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፤ የጤንነቱ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ አሣሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ታውቋል፡፡
በእስር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል አህመዲን ጀቢል የገጠመው የጤና ችግር አስጊ በመሆኑ አፋጣኝ ህክምና እንዲያገኝ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ጫና እንዲፈጥሩ ፈረስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ጥሪ አቀረበ።
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 7/2010) በእስር ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል አህመዲን ጀቢል የገጠመው የጤና ችግር አስጊ በመሆኑ አፋጣኝ ህክምና እንዲያገኝ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ጫና እንዲፈጥሩ ፈረስት ሂጅራ ፋውንዴሽን ጥሪ አቀረበ። አህመዲን ጀቢል በከፍተኛ የኩላሊት ህመም በመሰቃየት ላይ መሆኑን የተለያዩ የመረጃ ምንጮች በመግለጽ ላይ ናቸው። የህወሃት መንግስት የደህንነት ሃይሎች በእስር ቤት ውስጥ ከባድ ድብደባና ማሰቃየት ይፈጽሙበት እንደነበርም ታውቋል። በተደጋጋሚ ህክምና በመከልከሉ ህመሙ ወደ ከፋ ደረጃ መድረሱን ያስታወቀው ፈርስት ሂጅራ ጉዳዩን ለአፍሪካ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለማሳወቅ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በመንግስት ጣልቃ ገብነት የእምነት ነጻነታቸው መገፈፉን ተከትሎ ያስነሱትን ተቃውሞ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል አንዱ ነው። የህወሃት መንግስት ከስድስት ዓመት በፊት የኮሚቴውን አብዛኛውን አባላት ወደ እስር ቤት ሲያስገባ እሱም አንዱ ነበር። ፖለቲካዊ ውሳኔ በፍርድ ቤት ሲተላለፍ የ22ዓመት እስር ተበይኖበታል። ከአንድ ዓመት
በዚምባቡዌ የሀገሪቱን ስልጣን የተቆጣጠሩት ወታደራዊ አዛዦች ከሚኒስትሮችና በቁም እስር ላይ ከሚገኙት ሮበርት ሙጋቤ ጋር በድርድር ላይ መሆናቸው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር7/2010) ድርድሩን በዋናነት የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ ሳድክ እየመራው መሆኑ ታውቋል። የአፍሪካ ሕብረት በበኩሉ የወታደራዊው ሃይል ስልጣኑን በሃይል መቆጣጠሩን እንደማይቀበለው አስታውቋል። በዚምባቡዌ ወታደራዊ አዛዦች የሀገሪቱን መንበረ ስልጣን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ዛሬ ወታደራዊ አዛዦቹ ከሚኒስትሮች እንዲሁም በቁም እስር ላይ ከሚገኙትና ሀገሪቱን ለ37 አመታት ከመሩት ሮበርት ሙጋቤ ጋር በድርድር ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ቢቢሲ ከሐራሬ እንደዘገበው ድርድሩ እየተመራ ያለው ሳድክ በመባል በሚታወቀው የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ አማካኝነት ነው። የዚምባቡዌ የተቃዋሚ መሪ የሆኑት ሞርጋን ቫንጊራይ ሙጋቤ ስልጣኝቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ጠይቀዋል ተብሏል። ቢቢሲ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የ93 አመቱ ሮበርት ሙጋቤ ሕጋዊ ፕሬዝዳንት ነኝ በማለት ስልጣናቸውን ላለመልቀቅ እያንገራገሩ መሆኑ ተሰምቷል። የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር የጊኒው አልፋ ኮንዴ ሕብረቱ የወታደራዊው ሃይል ስልጣኑን በሃይል
Wednesday, November 15, 2017
Ethiopia: Group says leaked security doc shows regime on brink of collapse
ESAT News (November 14, 2017)
Patriotic Ginbot 7, an armed opposition to the Ethiopian regime, said a security plan of action document leaked yesterday to the media shows the regime in Ethiopia is teetering on the brink.
A leaked security document first published by the Addis Standard on Monday blames Patriotic Ginbot 7 and OLF for the unrest in the country. The document accused that the groups are supported by Egypt and Eritrea; and are bent on to disrupt the peace and dismantle the constitutional system through violence.
ESAT’s attempt to reach OLF representatives for a response has failed but a member of the leadership for PG7, Neamin Zeleke, responded saying the document was another evidence that the regime is gasping for the last breath.
በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ
በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው ለኢሳት እንደገለጸው በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉት ሁለገብ ትግሎችን ለማፋፋም ተዘጋጅቷል። የህወሀት መንግስት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና ደህንነት የገጠሙ አደጋዎች ህዝቡን ተስፋ እንዳስቆረጡት የገለጸበት ዕቅድ ግብጽንና ኤርትራን ድጋፍ በመስጠት የሚከስ ነው። አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄንና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን በሀገሪቱ ለተፈጠሩት ቀውሶች ዋነና ተጠያቂ ያደርጋል።የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እያደረገ ያለውን ትግል አጠናክሮ እንደሚቀጥልና የኢትዮጵያ ህዝብ በውድቀት አፋፍ ላይ ያለውን ስርዓት ነቅሎ ለመጣል እንዲዘጋጅም ጥሪ አቅርቧል።
Ethiopia suffers dramatic decline of internet freedom
ESAT News (November 15, 2017)
Ethiopia has suffered a dramatic decline of internet freedom over the past year, according to an annual report by Freedom House.
The report said Internet and mobile phone networks were deliberately disrupted during anti government protests and student exams; social media and communications platforms were periodically blocked throughout the year.
ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ሰዓት መቀሌና ሀራሬ ሁነኛ የፖለቲካ ክስተት ተፈጥሯል። የመቀሌው ይፋ የወጣ አይደለም። በህወሀት አፍቃሪያን ድረገጾች የተተነፈሰ ወሬ ነው። ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመቀሌውን ህንፍሽፍሽ ረግጠው ወጡ የሚለው ከውስጥ አዋቂ ያፈተለከው ዜና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በትክክል ከሆነ የሀራሬው ዓይነት መፈንቅለ መንግስት ልናይ የምንችልበት እድል ሰፊ ነው። የጄነራል/ፕሮፌሰር ሳሞራ የኑስ ቡድን በመቀሌው ስብሰባ ከተሸነፈ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ አይሆንም። በአቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባው ህወሀት በአንዳች ተአምር መከላከያውን ከሳሞራ የኑስ እጅ ፈልቅቆ ካልወሰደ በቀር የወ/ሮ አዜብ መስፍን ኩርፊያና ረግጦ መውጣት የሚያስከትለው መዘዝ ለህወሀት ፍጻሜው ሊሆን ይችላል።
አህመዲን ጀበል በህክምና እጦት ከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆኑ ታወቀ
ሰበር ዜና፦
ቢቢኤን ህዳር 06/2010
የህዝብን ዉክልና ተቀብሎ የህዝብን ድምጽ በሰላማዊ መንገድ በማሰማቱ ለእስር የተዳረገው አህመዲን ጀበል ማረሚያ ቤት ዉስጥ እየተሰቃየ መሆኑ ታወቀ።በማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ ከፍተኛ ድብደባንና ግርፋት (ቶርቸር) የደረሰበት አህመዲን ጀበል አሁንም የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በሚያደርስበት ስነ-ልቦናዊና አካላዊ ስቃይ ጤናው እየተቃወሰ እንደሚገኝ ታውቋል።አህመዲን ጀበል አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ካላገኘ ለከፋ ችግር እንደሚዳረግም ህክምና ባገኘበት የቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ዉስጥ ያሉ የቢቢኤን ምንጮች አሳውቀዋል።
ወጣቱ የህሊና እስረኛ በህዝብ የተመረጠው የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ሐላፊ ሆኖ ያገለገለ ሲሆን፤ በግፍ ተይዞና በሐስት ተመስክሮበት የ22 አመት ጽኑ እስራት እንደተፈረድበት ይታወቃል። በቅሊንጦና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዉስጥ ስቃይና መከራን በየቀኑ የሚጋፈጠው አህመዲን ጀበል
ቀደም ሲል በማእከላዊ የማሰቃያና የማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ በደረሰበት ዘግናኝ የስቃይ አያያዝ (ቶርቸር) ለጤና ቀዉስ መዳረጉ አይዘነጋም።
ቀደም ሲል በማእከላዊ የማሰቃያና የማጎሪያ ካምፕ ዉስጥ በደረሰበት ዘግናኝ የስቃይ አያያዝ (ቶርቸር) ለጤና ቀዉስ መዳረጉ አይዘነጋም።
በኩላሊት በሽታና በሽንት ፊኛ ትቦ ህመም የሚሰቃየው አህመዲን የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር በተገቢው ሰዓት የህክምና ፍቃድ ሊሰጠው ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሳቢያ የጤናው ችግር እየከፋ መሆኑ ታዉቋል። ከብዙ ልፋትና ድካም በሗላ ተመላላሽ ታካሚ እንዲሆን የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ቢፈቀድለትም የሆስፒታል ቀጠሮዎቹን በተገቢው መልኩ
Tuesday, November 14, 2017
በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ
በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው ለኢሳት እንደገለጸው በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉት ሁለገብ ትግሎችን ለማፋፋም ተዘጋጅቷል። የህወሃት መንግስት በዕቅዱ ላይ በአሸባሪነት ከወነጀላቸውና ስርዓቱን በማስጨነቅ ብርቱ ፈተና እንደደቀኑ ከተጠቀሱት ድርጅቶች አንዱ አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መሆኑ ይታወቃል። ሾልኮ የወጣውና በመንግስት የቀረበው ወቅታዊ ሁኔታን የሚዘረዝረው ዕቅድ ሀገሪቱ ያለችበትን አደጋ በጥልቀት የሚያሳይ ነው። የህወሀት መንግስት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና ደህንነት የገጠሙ አደጋዎች ህዝቡን ተስፋ እንዳስቆረጡት የገለጸበት ዕቅድ ግብጽንና ኤርትራን ድጋፍ በመስጠት የሚከስ ነው። አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄንና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን በሀገሪቱ ለተፈጠሩት ቀውሶች ዋነና ተጠያቂ ያደርጋል። ዕቅዱ ላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ድርጅቶች በሀገሪቱ ውስጥ እንደፈለጉ እየፈነጩ በመሆኑ የህዝብ ደህንነት ስጋት ላይ ወድቋል ይላል የህወሀት መንግስት። ኢሳት በዕቅዱ ላይ ክስ የቀረበባቸውን
Saturday, November 11, 2017
አጭር መልዕክት ለብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ባልደረቦች በሙሉ! (ዶክተር ታደሰ ብሩ)
የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ሥራቸውና ስማቸው ለየቅል ከሆኑባቸው ተቋማት አንዱ ነው። ይህ ተቋም እንደ ስሙ የሚሠራ ቢሆን ኖሮ ለብሄራዊ ደህንነት የሚጠቅሙ መረጃዎችን የሚሰበስብ በሆነ ነበር፤ ግን አልሆነም።
አሁን ባለሁ ሀቅ መሠረት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት፣ ህወሓትን የሚቃወሙ ዜጎችን ሁሉ በጠላትነት ፈርጆ ለማጥፋት “ህጋዊ ፈቃድ” የተሰጠው ተቋም ነው። የዚህ ተቋም አባላት በአገር ደህንነት ስም የዜጎችን የግል መኖሪያ ቤት፣ ቢሮ፣ የስልክና የኢሜል ግኑኝነቶች ይበረብራሉ። “የዓይኖቻቸው ቀለም” ያላማሩዋቸውን“ ዜጎች ያዋክባሉ፣ ይገርፋሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይገላሉ። ከፍተኛ መጠን ያለው የሀገር ሀብት የህወሓት ሽማምንትን ደህንነት ለመጠበቅ ያባክናሉ። ውሎና አዳራቸው ዜጎችን ማሳደድ ነው። ከዚህም አልፎ ሕዝብ ከሕዝብ፤ የአንድ እምነት ተከታዮች ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋር የሚያጋጩ አሻጥሮችን ይሠራሉ። ዘወትር ወንጀሎችን እየሠሩ በሌሎች ላይ ይደፈድፋሉ። ፍርድ ቤቶች ፍርደገምል ውሳኔ እንዲሰጡ ያደርጋሉ። ... ብዙ እጅግ ብዙ ለዓይንና ጆሮ የሚቀፉ ተግባራትን ይፈጽማሉ።
Friday, November 10, 2017
በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተካተቱበት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ይፈታል የተባለ አዲስ እቅድ አወጣ
በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተካተቱበት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ይፈታል የተባለ አዲስ እቅድ አወጣ። የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ያወጣውን አዲስ እቅድ በተመለከተ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የጸጥታ ሃይሎች ከእንግዲህ የሚካሄዱ ህገ ወጥ ሰልፎችን ለማስቆም እንዲችሉ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። እስካሁን ለጠፋ ህይወትና ንብረት የሚጠየቁና ለሕግ የሚቀርቡ አካላት እንደሚኖሩም አቶ ሲራጅ ገልጸዋል። ዜጎች በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚያካሂዱት አመጽ እንዲቆም ይደረጋልም ብለዋል። በኢትዮጵያ የተከሰተውን ሕዝባዊ አመጽ አንዴ በሀይል ሌላ ጊዜ ደግሞ ያልተፈጠረ በማስመሰል ለመከላከል ሲማስን የነበረውና በሕወሃት የሚመራው አገዛዝ ብዙ ሙከራዎችን ሲያደርግ ቆይቷል። በአስቸኳይ አዋጁ ጭምር የሕዝብን ጥያቄ ለማፈን ያልቻለው አገዛዝ ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር ውሏል፣የሀገሪቱ ሰላምም አስተማማኝ ነው ሲልም ነበር። አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የሕዝብ ቁጣ ለማፈን አዲስ እቅድ ነድፌያለሁ እያለ ነው። አዲስ እቅድ ደግሞ ተነደፈ የተባለው በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት መሆኑን የመንግስት
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች ለራሳቸው አካባቢ የማድላትና ሁሉንም ሕዝብ እኩል ያለማየት ችግር አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች ለራሳቸው አካባቢ የማድላትና ሁሉንም ሕዝብ እኩል ያለማየት ችግር አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ይህንኑ ችግር ለማስወገድ በኦሮሚያና አማራ ክልል መካከል የተካሄደው ሕዝባዊ የምክክር መድረክ በሌሎች ክልሎችም በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል። የኢህአዴግ ማዕከላዊ አሰራር ተዳክሞ አባል ድርጅቶች መርህ እየጣሱ ነው መባሉም ትክክል አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። አቶ አባዱላ ገመዳ በቴሌቪዥን ወጥተው ከአፈጉባኤነት ለመልቀቅ ጥያቄ ስለማቅረባቸው መግለጻቸውም ልክ አይደልም ብለዋል። በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች መካከል ልዩነት እየተፈጠረ መሆኑን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያሉ ክስተቶች ያመላክታሉ የሚሉ አስተያየቶች ሲደመጡ ቆይተዋል። ይህም የኢሕአዴግ ማዕከላዊነት መርህ እየተጣሰ ሕወሃት ተዳክሟል የሚሉት ብዙዎች ነበሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም በሰጡት መግለጫ ግን ኢሕአዴግ መርሁ ተጥሶ አያውቅም ሲሉ ነው
የጣሊያን ፍርድ ቤት ከ5 ዓመት በፊት የተገነባውን የግራዚያኒ ሀውልት እንዲፈርስ ውሳኔ ሰጠ
የጣሊያን ፍርድ ቤት ከ5 ዓመት በፊት የተገነባውን የግራዚያኒ ሀውልት እንዲፈርስ ውሳኔ ሰጠ። በላዚዮ ክፍለ ግዛት አፊሌ ከተማ የፋሺስቱ ሮዶልፍ ግራዚያኒ መታሰቢያ ሀውልትን በገነቡት የከተማዋ አመራሮች ላይ የእስርና የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉምም ታወቀ። ዓለም ዓቀፍ ህብረት ለፍትህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ለኢሳት እንዳስታወቀው ይህ የጣሊያን ፍርድ ቤት ውሳኔ ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው። ሀውልቱን የገነቡትና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበር ክስ የተመሰረተባቸው የአፊሌ ከተማ ከንቲባና ሌሎች አመራሮች ከ6 እስከ 8 ወራት እስራት የተፈረደባቸው ሲሆን የገንዘብ ቅጣትም ተጥሎባቸዋል። ከ1928 እስከ 1933 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ባለው የ5ዓመቱ የፋሺስት ወረራ 1 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። 2ሺህ አብያተክርስቲያናት ተቃጥለዋል። ከግማሽ ሚሊየን በላይ ቤቶች ወድመዋል። 14ሚሊየን የቤት እንስሳት አልቀዋል። በገንዘብ ለመተመን የሚያስቸግሩ የሀገር ቅርሶች ተዘርፈው ተወስደዋል። ፋሺስት ጣሊያን በኢትዮጵያና ህዝቧ ላይ የሰራው ግፍ በታሪክ ሲታወስ የሚኖር
የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ እንደገና ማገርሸቱ ተሰማ
የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ እንደገና ማገርሸቱ ተሰማ። ቀውሱ እንደገና ያገረሸው ባለፈው ቅዳሜ የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣኔን ለቅቄያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ነው። በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት ሁቲዎች ባለፈው ቅዳሜ ወደ ሳውዲ ያስወነጨፉት የረጅም ርቀት ሚሳኤል ጉዳይም ሌላኛው የውጥረቱ ምክንያት ሆኗል። የሳውዲ ዜግነትን ደርበው የያዙት የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳአድ ሐሪሪ ባለፈው ቅዳሜ ከሳውዲ ሪያድ ሆነው የግድያ ሙከራ ሊደረግብኝ እየተጠነሰሰ ነው በሚል ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ካሳወቁ በኋላ ሌባኖስን ትልቅ ቀውስ ውስጥ ከቷታል። ሐሪሪ የግድያ ሙከራው በማን ሊደረግ እንደታቀደ በግልጽ ባያስቀምጡም ኢራን በሀገራቸውም ሆነ በአካባቢው አረብ ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን አውግዘዋል። የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሳውዲ ሆነው ከስልጣን መልቀቃቸውን ባሳወቁበት በዛው እለት የሳውዲው አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን በዝርፊያ ጠርጥሬያቸዋልሁ ያሏቸውን የሳውዲ ልኡላንና ሚኒስትሮችን እንዲሁም ነጋዴዎችን ጠራርገው በቁጥጥር ስር
Subscribe to:
Posts (Atom)