Monday, May 9, 2016

ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መረጃ በማቀበል ወንጀል ተከሰሱ


ሚያዚያ ፩(ግንቦት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ አቃቤ ህግ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት ምክትል አስር አለቃ አጃናው ታደሰና ምክትል አስር አለቃ ቻሌ ነጋ ላይ ለአርበኞች ግንቦት7 ወታደራዊ መረጃዎችን ሲያቀብሉ ነበር የሚል ክስ ተከፍቶባቸዋል።
ሁለቱ ተከሳሾች 6ኛ እና 25ኛ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ሬጅመንቶችን ብዛት እና መገኛ ቦታ በስልክና በቫይበር ማስተላለፋቸውን ሪፖርተር ዘግቧል።
ተከሳሾቹ የአገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የገቡትን ቃል ኪዳን ወደ ኋላ በመተውና የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅትን ተልዕኮ በመቀበል፣ የመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትና የሚገኝበትን አድራሻ መረጃ አሳልፈው በመስጠት፣ ከድርጅቱ ታጣቂዎች ጋር ለመቀላቀልና የድርጅቱ ተስፋ በመሆን በሽብር ወንጀል መከሰሳቸው ተዘግቧል። ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ለማዬት ግንቦት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

No comments:

Post a Comment