ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን ለኢንቨስትመንት በሚል መሬት ከወሰዱት መካከል 98 በመቶ የሚሆኑት የህወሃት ደጋፊና አባላት መሆናቸው በኢሳት ከተጋለጠ በሁዋላ ህዝቡ በጸረ ሙስና ስብሰባዎች ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ቦዲ ለማስተባበል ሞክረዋል። አቶ አለማየሁ ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በልማቱ ገብቶ እንዲሳተፍ መሬት አዘጋጅተን ሰጥተናል ቢሉም፣ መሬቱ በአንድ አካባቢ ሰዎች ተይዟል ወይስ አልተያዘም የሚለውን ማስተባበል ሳይችሉ ቀርተዋል።
ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም ተደርጎ በነበረው ስብሰባው ላይ የተሳተፉ ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት ፣ በስብሰባው ላይ የተነሱት ጥያቄዎች የመንግስት ባለስልጣናቱን ሲያበሳጩ፣ ለቀረቡት ጥያቄዎች የመንግስት ባለስልጣናት የሰጡት መልስ ደግሞ በመልሱ ህዝቡን አበሳጭቷል።
ከአራት ቀናት በሁዋላ ለመምህራን በተደረገው ስብሰባ ላይም ተመሳሳይ ጥያቄ መቅረቡ፣ ባለስልጣኖችን ይበልጥ ማስቆጣቱን በስብሰባው ላይ የተገኙት መምህር እንድሪስ መናን ተናግረዋል። “ኢህአዴግ ጠንካራ አመራር የለውም፣ መከላከያ ሰራዊቱ የህወሃትን ስልጣን ለማስጠበቅ የቆመ ነው፣ በመሬት ዙሪያ ላይ በዞናችን ብዙ ቦታዎች በጥቂት ብሄሮች የተወሰደ ነው፣ ያ ተገቢ ነው ወይ?” የሚሉ እና ሌሎችም ጥያቄዎች ቀርበዋል።
በደቡብ አሪ ላይም እንደዚሁ መምህራን ተቃውሞ ማሰማታሻውን ለማወቅ ተሽሏል፡፡

No comments:
Post a Comment