Wednesday, May 4, 2016

የደቡብ ሱዳን መንግስት ከ100 በላይ የተጠለፉ ህጻናት ያሉበትን ቦታ ማወቁን ገለጸ

ሚያዚያ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር ከጋምቤላ በሙርሌ ጎሳ አባላት የተወሰዱት ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ፣ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የኢትዮጵያ ጦርም ወደ ደቡብ ሱዳን ድንበር ዘልቆ መግባቱን ብሉምበርግ ተርሚናል የፕሬዚዳንቱን ቃል አቀባይ በመጥቀስ ዘግቧል። ቢቢሲ እንደዘገበው ደግሞ እስካሁን የተገኙት 41 ህጻናት ናቸው።

የኢትዮጵያ ጦር በደቡብ ሱዳን መንግስት ፈቃድ ወደ አገሪቱ መግባቱንና ፍለጋም እያካሄደ መሆኑን ቃል አቀባዩ ገልጿል።
ሰዎቹን በድርድር ለማስለቀቅ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን ለአለማቀፍ ዲፕሎማቶች ሲናገር የነበረው መንግስት፣ አሁን ለምን ሰራዊቱን ወደ ውስጥ ለማስገባት እንደፈለገ የገለጸው ነገር የለም። የኢትዮጵያውያን ህጻናት መጠለፍ በአገር ውስጥ ከፍተኛ የህዝብ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል።

No comments:

Post a Comment