ግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም.
በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይል ውስጥ በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው አንድ ቡድን ፋሽስታዊው የህወሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት የመከላከል እርምጃ ወስዷል።
የዚህ ቡድን አባላት የሆኑት አርበኛ ታጋዮች ከሚያዝያ 29 ቀን እስከ ግንቦት 1 ቀን ባደረጉት የመረረ ፍልሚያ ከሃያ በላይ የጠላት ወታደሮችን ገድለው ከሃምሳ ያላነሱትን አቁስለዋል፤ በዚህ ትንንቅ ውስጥ ከአርበኞች ግንቦት 7 ወገንም መስዋዕትነት ተከፍሏል። በወጣት አርበኞቻችን ጀግንነት፣ ጽናትና የጉሬላ ጦር ታክቲክ ክህሎት ኮርተናል። ያደረጉት ተጋድሎ ወደፊት ለሚጠብቃቸው ከዚህ የከፋ ትንንቅ ይበልጥ የሚያዘጋጃቸው ሲሆን የሕይወት ዋጋ የከፈሉት ሰማዕታት ጓዶቻችን ታሪክ ደግሞ ህያው ሆኖ ይኖራል። ህወሓት እና በየቦታው የመለመላቸው አድርባይ ምስለኔዎቹ የኢትዮጵያን ሕዝብ በዘፈቀደ የሚያስሩበት፣ የሚገርፉበትና የሚገድሉበት ጊዜ አብቅቷል። የአርበኞች ግንቦት 7 ደቡብ ግንባር አባላት በተግባር ያስተላለፉት መልዕክት “መሮናል፤ ዝም ብለን እንደ በግ እየተጎተትን አንታሰርም፤ የካድሬዎች የደም ጥም ማርኪያዎች አንሆንም፤ በአገራችንና በሕዝባችን ላይ የሚደርሰውን መከራ እያየን ዝም አንልም፤ ለነፃነታችን መሞት ካለብን፣ ገድለን እንሞታለን !!!” የሚል ነው። ይህ ከኮስታራ ሀሞት የወጣ ድምጽ በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ወገኖቻችን ድምጽ ሊሆን ይገባል።ከህወሓት ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ ጋር የሚደረገው ትግል በመላው የኢትዮጵያ ግዛት የሚደረግ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ከዚህ በፊት መግለጹ ይታወቃል። የህወሓት አገዛዝ እያመመውም ቢሆን ያመነው ይህ በደቡብ ኢትዮጵያ የተፈፀመው የመጀመሪያ ተጋድሎ የሚያረጋግጠው ይህንኑ ሀቅ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 ደጋግሞ እንደገለፀው ትግሉን በሰሜን ኢትዮጵያና በድንበር አካባቢ ተወስኖ የማይቀር መሆኑን ይህ የመጀመሪያ ምልክት ነው፤ በሌሎች ቦታዎች ተመሳሳይ ተጋድሎዎች የሚጀመሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። በመላው ኢትዮጵያ፤ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምስራቅና ምዕራብ፤ በዳርና በመሀል አገር እንዲሁም በከተሞችና በገጠሮች አርበኞች ግንቦት 7 ለነፃነት የሚደረገውን ፍልሚያ ያቀጣጥላል። ይህ የነፃነት ተጋድሎ አንዳንዴ ቦግ፣ ሌላ ጊዜ ደብዘዝ ይል ይሆናል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሥልጣን ባለቤት ሳይሆን ግን አይጠፋም።አርበኞች ግንቦት 7 በሁሉም አቅጣዎች ጠላትን ለመፋለም ዝግጁ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ወጣቶች ራሳቸውን ለመራር ትግል እንዲያዘጋጁ እና በየአካባቢያቸው ያለውን የጠላት ኃይል ፋታ እንዲነሱ አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያደርጋል።
አንድነት ኃይል ነው!
ክብር ለሰማዕታት ጓዶቻችን !
የሕዝብ ትግል አሸናፊ ነው !

No comments:
Post a Comment