Monday, May 2, 2016

በኢትዮጵያ ውስት የትራፊክ አደጋ በ 11% መጨመሩ ተነገረ

(ሚያዚያ 24 ፥ 2008)

ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች በትራፊክ አደጋ የደረሰ የሞት አደጋ ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር በ11 በመቶ መጨመሩንና ወደ 5ሺ የሚጠጉ ሰዎችም ከባድ የአካል ጉዳት እንደ ደረሰባቸው በባለስልጣኑ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ሃላፊ የሆኑት አቶ ስሜ በላይ አስታውቀዋል።
በሰው ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪም ከ 569 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረትም በዘጠኝ ወራቶች ውስጥ መውደሙን የተናገሩት ሃላፊው የሃገሪቱ የትራፊክ አደጋ እጅግ አስደንጋጭ እየሆነ መምጣቱንም ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ያሉ የተሽከርካሪዎች ቁጥር ከህዝብ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ቢሆንም እየደረሰ ያለው ጉዳት ግን በአለም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት ይገልጻል።
የትራፊክ አደጋው በዚሁ መልኩ ከቀጠለም በየአመቱ ወደ አምስት ሺ የሚጠጉ ሰዎች ህይወታቸውን እንደሚያጡ የትራንስፖርት ባለስልጣን ሪፖርት ዋቢ በማድረግ በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

No comments:

Post a Comment