ከዛሬ አስርት አመታት በፊት እንደሚታወቀው በዲፕሎማ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚከታተሉት ተማሪዎች ከ3 እስከ 4 አመት የሚፈጅ ጊዜ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም በየጊዜ የሚወጡት መመሪያዎች ማሻሻያ እየተደረገ ዲፕሎማ የተሰኘውን ስም በመቀየር LEVEL የሚል መጠሪያ ስም አግኝቶ አንድ ሁለት ሶስት እየተባለ አራተኛ አመት ላይ የLEVEL 4 ምሩቅ ተብሎ ይመረቃል። ከዚያም የብቃት ማረጋገጫ መመዘኛውን (COC ) እስከ አራት LEVEL ድረስ ራሱን የቻለ ፈተና ማለፊያው ደግሞ ለእያንዳንዱ 100 % ውጤት ማስመዝገብ እየተጠየቀ ፈተናውን 99% እንኩዋን ወይም ጭራሽ ያልወሰደ ተመዛኝ ለስራ ብቁ እንዳልሆነ ተደርጎ በመስሪያ ቤት ደረጃ እንዳይቀጠር ህጉን አስቀምጠውታል። ይህም አላበቃም ከዛሬ ሶስት አመት በድጋሜ ሌላ መመሪያ ተላለፈ። አንደኛ አመት የLEVEL ተማሪ ለሁለትኛ አመት የሚያበቃው የCOC መመዘኛው ሲያልፍ ብቻ ለመቀጠል የሚያስችለው እንዲ እያለ ሁለትን ጨርሶ COC ሶስት አራት በየአመቱ መጨረሻ አራት ጊዜ እንዲመረቅ ተደርጉዋል። ማሻሻያው የለውጥ ግስጋሴውን ማን ይገታዋል ቅቅቅቅ ዘንድሮ ባለንበት ወር አዲስ ማሻሻያ ይዞ ብቅ አለ። አንድ ተማሪ የአንድ አመት የLEVEL ትምህርቱን ካጠናቀቀ በሓላ የሙያ መመዘኛ (COC) ይወስዳል ከዚያም ቢያልፍም ባያልፍም ሁለት አመት ስራ ላይ ውሎ ከነማስረጃው ለሁለተኛ አመት Level ይመዘገባል ይህ ስለሆነ ከጨረሰበት አመት ተቆጥሮ ሁለት አመት ሰርቶ ሲመለስ ብቻ ይሆናል ወደ ኮሌጁ ተመልሶ ትምህርቱን ሊቀጥል የሚችለው ከዚያም ሁለተኛ አመት Level2 ትምህርቱን ካጠናቀቀ በሃላ ለሁለት አመት ስራ ሰርቶ ለሶስተኛ አመት ትምህርት ይደርሳል ማለት ነው። እንዲህ እያለ LEVEL-4 የአራት አመት ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ የሚችለው በአስር አመት ጊዜ መሆኑ ታውቁዋል።
No comments:
Post a Comment