ሐምሌ 11 ቀን 2006 ዓ.ም በአናዋር መስጊድ በተነሳው ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የሚገኙት፤ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል አቶ ኢብራሂም አብዱልሰላም እና ወ/ሪ ወይንሸት ሞላ እንዲሁም የአዲስ ጉዳይ መፅሔት ፎቶ ግራፈር አዚዛ መሐመድ ከህግ አግባብ ውጪ ለተጨማሪ 48 ሰዓት በእሰር ቤት እንዲቆዩ ተደረገ፡፡
ሚክሲኮ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባቀረበው የክስ አቤቱታ መሠረት በተለያየ ቀናት ከሳሽን እና ተከሳሽ መካከል ክርክር ሲደረግ ቆይቶ ሐምሌ 29 እና 30 ተከሳሾች (እነ ወይንሸት) እያንዳንዳቸው 5000 ሺህ ብር የሚገመት የንብረት ዋስ አሲዘው እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር፡፡ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ ይግባኝ በመጠየቅ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲሻር በማድረግ 30 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድለት አስደርጓአል፡፡ይህን የህግድ ውሳኔ የሰጠው የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ነው፡፡ይሁን እንጂ የዚህን ትህዛዝ በክስ መዝግብ ውስጥ ፖሊስ ሳያካት ወይም ቀድሞ ውሳኔ ለሰጠው ፍርድ ቤት ሳያሳውቅ እነ ወይንሸትን ፖሊስ በራሱ ፍቃድ ብቻ እስር ቤት ሊያቆያቸው ችሎአል፡፡
በመሆኑም በተሰጠው የህግድ ትህዛዝ መሠረት በ07/12/06 ይግባኝ ባይ ፖሊስ በተሠጠው የጊዜ ቀጠሮ ለፍርድ ቤት ቀርቦ “የሚቀረን ተጨማሪ የሰው ማስረጃ ማሰባሰብ ፣ያልተያዙ አባሪዎችን መያዝ ነው፡፡ሆስፒታል ተኝቶ የነበረው ፖሊሲ የጤናው ሁኔታ ከነበረበት የተሸለ ስለሆነ የህክምና ማስረጃዎችን ጨርሰን ለአቃቢ ሕግ አስታየት ማሰጠት ነው” በማለት ለፍርድ ቤት ያስረዳ ሲሆን ፡፡ፍርድ ቤቱ “ ይግባኝ ባይ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ይሁን እንጂ ቀደም ሲል በተሰጠው የህግድ ትህዛዝ መሠረት የተጎጂዎች የህክምና ማስረጃ በማቅረብ ወይም የምርመራ መዝገቡን በመያዝ በአግባቡ አላስረዳም በመሆኑ የህግድ ትህዛዙን አንስተናል” በማለት በትላንትናው ዕለት ውሳኔ አስተላልፏአል፡፡ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ ከተላለፈ በኋላ ቀደም ብሎ ትዕዛዝ ወደተሰጠበት ፍርድ ቤት ታሳራዎችን በዋስ ለማስለቀቅ የተደረገው ጥረት ዳኞች እና የፍርድ ቤት እረዳት ሰራተኞች ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ይህ በሆነ በማግስቱ ማለትም በዛሬው ዕለት በ8/12/06 ጠዋት 2፡30 ሚክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቂርቆስ ምድብ ችሎት በመቅረብ ቀድሞ የተወሰነው ውሳኔ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት አፅድቆታል በመሆኑም የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ታሳሪዎች እንዲለቀቁ ዋስ በማዘጋጀት ፍ/ቤቱ የማስፈቻ ትህዛዝ እንዲሰጥ ቢጠየቅም ፡፡ጉዳዩን የተመለከቱት ዳኛ በሰበር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ግልብጭ ያስፈልጋል ይህም በመሆኑ ግልባጭ አምጡ በማለት ትህዛዝ ሰጡ፡፡ ህንዲህ አይነቱ ትህዛዝ በወቅቱ አስፈላጊ ባይሆንም ምን አይነት አማራጭ ባለመኖሩ ወደተጠቀሰው ፍርድ ቤት በመሄድ የውሳኔ ግልባጭ የተጠየቀ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት “እንዲ አይነት ትህዛዝ ከዚህ ቀደም ተሰጥቶ አያቅም በአሰራር ሂደትም ገጥሞን አያውቅም ” በማለት ለተጠየቁት የውሳኔ ግልባጭ ምላሽ ለመስጠት እጅግ በጣም መቸገራቸውን በመግለፅ የሁኔታው አሳሳቢነት ተረድተናል በማለት የተጠየቀውን የውሳኔ ግልባጭ ለመስጠት ችሎአል፡፡
ይውሳኔ ግልባጭ የጠየቀው የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን ትህዛዝ የቀረበለት ሲሆን ቀድሞ ትህዛዙን የሰጡት ዳኛ ምክንያቱ ባልታወቅ ሁኔታ የስራ ገበታቸው ላይ ሊገኙ አልቻሉም፡፡ይህ በመሆኑ የትህዛዝ ችሎት ዳኛ ለሆኑት ለተለዋጭ ዳኛ ጉዳዩን እንዳዲስ በማስረዳት የታሳሪዎች የዋስትና መብታቸው ተከብረሮ ከእስር ቤት እንዲወጡ የማስፈቻ ትህዛዝ እንዲሰጡ የተጠየቁ ሲሆን እሳቸውም በተራቸው “ እኔ ውሳኔ መስጠት የምችለው የሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሠረት ብቻ ሳይሆን ቀድም ብሎ ሰበር ሰሚ ፍ/ቤት የእኛን ውሳኔ ያገደበት የህግድ ትዛዝ ግልባጭ ሲደርሰን ነው፡፡በመሆኑም ከሰበር ሰሚ ፍ/ቤት የህግድ ትህዛዙን ማምጣት አለባችሁ በማለት ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ይህ ሲሆን ጉዳዩን በፍርድ ቤት በመገኘት በቅርበት ስንከታተል ለነበርነው የሰማያዊ ፓርቲ የምክ/ቤት ዋና ሰብሳቢ አቶ ሰኢድ ኢብራሂም፣የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ እንዲሁም የወይንሸት ሞላ እህት ወ/ሪ መልካም ሞላ እና አቶ አፍወርቅ በደዊ፡፡በተጨማሪም እያንዳንዱን ጉዳይ ፍጥነት በተሞላበት መልኩ በስልክ ልውውጥ ሲከታተሉ ለነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንብር ኢ/ር ይልቀል ጌትነት እና የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ እጅግ በጣም ከማስገረሙም አልፎ ቁጭት እና በስጭት እንዲሰማን አድርጓአል፡፡ሆኖም ግን ልክ እንደቅድሙ አሁንም ምንም ማድረግ ስለማይቻል ወደተጠቀሰው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማመልከት ግድ ሆኖአል፡፡
በመሆኑም የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን ትእዛዝ ለመጠየቅ የአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመቅረብ ከስር ፍርድ ቤት የተጠየቅነውን አስረድተን ሳንጨርስ “ የዛሬው ምን ጉድ ነው ? ምን አይነት ዳኞች ናቸው ፣እንዲ አይነት ትእዛዞችን እየጠየቁ የሚያጉሏሏችሁ ! የቅድሙ ሲገርመን ይሄን ይጠይቃሉ” በማለት በታችኛው ፍ/ቤት ሲገረሙ እና ሲሣሣቁ ለመታዘብ የተቻለ ሲሆን፡፡በሆነው ነገር አብዛኛው የመዝገብ ቤት ሰራተኞች እና የዳኞች ፃፊዎች በማዘና እና በመገረም የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቀውን የህግድ ትህዛዝ በማዘጋጀት በሚደንቅ ትብብር ሊሰጡ ችለዋል፡፡በዚህም መሠረት የታችኛው ፍርድ ቤት የጠየቅውን የህግድ ትህዛዝ በመያዝ የህግድ ትህዛዙ እንዲቀርብላቸው ለጠየቁት ዳኛ በዲጋሚ ለመቅረብ የተቻለ ሲሆን ጉዳይ የተመለከቱት ዳኛ “አሁን ሁሉም ነገር ተሟልቷአል በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት የሚችለው ጉዳዩን በመጀመሪያ ሲያየው የነበረ ዳኛ ነው፤አሁን እሱ ስለሌለ ነገ ጠዋት መጥታችሁ ጉዳያችሁ ማቅረብ ትችላለችሁ” በማለት ምንም እንዳልተፈጠረ አድርገው ውሳኔ አስተላለፉ፡፡
የአገራችን የዳኝነት ስርአት በተለያየ ወቅት እና በተለያየ ተበዳዮች እውነተኛ ፍትህ ሳያገኙ እየቀሩ በእንዲ መልኩ ከስር ከስሩ እየታጨደ ሌጣ ሜዳ ሆኖ መቅረቱ ያስቆጫል፡፡እኔ በሆነው ነገር እጅግ በጣም ነው ያዘንኩት፤ በእንዲህ አይነቱ ግዴለሽነት እና በእጅ አዙር መንግስትን የሚጠቅም ውሳኔ የሚያስተላልፍ ፍርድ ቤት እና የዳኝነት ስርአት መታየቱ የገዥውን የአምባገነን መንግስት ስርአት አደገንኘቱን ከማመላከት ባለፈም ስርአቱ በህዝብ ተሳትፎ ከወደቀም በኋላ ወደፊት ዜጎች በፍትህ ስርአት ላይ አመኔታ እንዲያጡ ሆን ተብሎ የሚቀበር ፈንጂ ስለመሆኑ አርቆ አሳቢነትን አብዝቶ የሚጠይቅ አይደለም፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !!! በይድነቃቸው ከበደ
No comments:
Post a Comment