Friday, August 22, 2014
ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ሲታፈሱ አመሹ
ለዘ-ሐበሻ የዘገበው ኢትዮጵያ ሃገሬ ጅዳ በዋዲየሳውዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ህገወጥ ውጭ ሃገር ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚገልጸውን መመሪያ ተግባርዊ ለማድረግ የፀጥታ ሃይሉ በወሰዱት እርምጃ ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ እትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሳውዲን ምድረ ለቀው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ ከስደት ተመላሽ ወገኖችን መልሷ የማቋቋም ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በወቅቱ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ እስኪረጋጋ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኗም ከስደተኛው ጋር ፎቶ በመነሳት በኢቲቪ ሲሰራጭ ከነበረው ሰፊ የዜና ሽፋን ባሻገር ስደተኛው ምንም አይነት ማቋቋሚያም ሆነ ድጋፍ እንዳላደረጉላቸው ይነገራል። በተለይ የስደት አለም ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው ለሃገር የበቁ እናቶች ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉበት አስዛኝ ታሪክ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሆድ አላውሷል ። መንግስት በወቅቱ አዲስ አበባ በስደተኞቹ እንዳትጨናነቅ የስደተኞቹ ጉዳይ በየክልሉ ባለስልጣናት የታያል በሚል ሽፋን በመቶሺህ የሚቆጠረውን ስደተኛ በየጉራጉሩ ወሽቆ ነገሮቹን ለማድበስበስ ቢሞክረም አብዛኛው ወገኖች በቋፍ ላይ ያለቸውን ህይወታቸውን ለመታደግ አቀም ያለው አይቀሬውን ሞት በመጋፈጥ፡ በህይወቱ ቆርጦ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት ቀይ ባሀርን በጀልባ አቋርጧ ለዳገም ስደት ተዳርጓል።በአንጻሩ በሰው ሃገር ወልዶ ከብዶ በወቅቱ ያገኛት በነበረች የዕለት ገቢው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ የስደት አለም ጎጆውን አሞቆ ያለጥሪት ይኖር የነበረው አባወራ ያቺን ቀውጢ ውቅት መቋቋም ተስኖት የቤተሰቦቹን ህይወት ከወረበሎች ለማዳን ወደ ሃገሩ እግሬ አውጪኝ ቢልም ያለጠበቀው ገጥሞት የሞቀ የስደት ዓለም ትዳሩን መቅኔ ያሳጣውን የመንፉሃው ሁከት እየረገመ በገዛ ሃገሩ ሰማይ ተድፍቶበት ለልጆቹ የዕለት ጉርስ ዳቦ መግዣ አጥቶ የህጻናቱን ስቃይ እና መከራ ላለማየት እግር ወዳ መራው ሲኳተን በረሃ በልቶት እደወጣ የቀረውን ከሳውዲ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ቤት ይቁጠረው ። ይህ ባለበት ሁኔታ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በዛሬው ዕለት ባደረጉት የተጠናከረ የቤት ለቤት ፍተሻ ከ1 ሺሕ በላይ ህገ ወጥ ሰዎች በቁጥጠር ስር መዋላቸውን የሚናገሩ ምንጮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጉዳዩን የበለጠ አሰደንጋጭ ያደረገዋል ። የፀጥታ ሃይሉ ከህብረትሰቡ በሚቀርብላቸው መረጃ መስረት ዘመቻውን በቀጣይነት በሪያድ ከተማ በተለምዶ ነሲም አል ሃማም እና ጉቤራ እይተባሉ የሚጠሩ መንደሮችን በማማከል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።። ከአንድ ወር በፊት በሪያ ድ ከተማ የአንድ ወህኒ ቤት ግርግዳ ደምርሰው ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ቁጥሩ በወል የማይታወቅ እስረኞች ማምለጣቸው ይታወሳል ።በዛሬው ዕለት መንፉሃ ውስጥ በተካሄደው የቤት ለበቤት ፍተሻ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለደርሰ እንግለት ወደ ሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ባደረኩት ጥረት አንድ ስሜ እንዳይገለጽ ያሉ ዲፕሎማት የቤት ለቤት ፍተሻው በኢትዮጵያውያኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ገልጸው በዘመቻው ወቀት ከፍተኛ የሳውዲ ፀጥታ ሃይል መኮንኖች እና የመዲናይቱ ባለስልጣናት የቀርብ ክትትል እና ቁጥጠር ያደርጉ እንደነበር በማውሳት እርምጃው በባህር የመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በሌላቸው ህገወጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና በየትኛውም ዜጋ ላይ ምንም አይነት እንግለት ያለተፈፀመ ጥናቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደነበር አረጋግጠናል ብለዋል ።በማስከተል ትላንት የሻኞቸውን ኢትዮጵያውያን ደግማችሁ ዛሬ ስትሸኙ ምን ይሰማችሃል ላልኳቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡኝ ተሰናብተውኛል። ዛሬ ማለዳ መንፉሃ ውስጥ በሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ተካሄደ በተባለው የቤት ለበቤት አፈሳ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ወህኒ ከሚገኙ ወገኖች መረጃ በማሰባሰብ በሰፊው ለመዘገብ የማደርገው ጥረት ይቀጥላል ።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment