የወያኔ መንግስት «ሕገ–መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመናድ…» በሚል ክስ በአምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ ላይ «በሕዝብ ላይ ሽብርተኝነት የሚነዙ ሽብርተኛ ናቸው!» ብሎ ከስ ማቅረቡ ይታወቃል ይህንንም ተከትሎ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፋክት መጽሔት ባልደረባ እንዲህ ይላል
«ይህ ክስ ‹የሕዳሴ አብዮቱን ለመቀልበስ የተደረገ ነው› ክሱን በሚመለከት የደረሰን ነገር የለም። ጉዳዩን ከመንግስት መገናኛ ብዙሐን ነው የሰማነው። ይህ ለምን እንደሆነ በራሱ ግራ የሚያጋባ ነው። ምክንያቱም በተለመደው አሰራር ክስ ሲመሰረት ተከሳሹ መጥሪያ ደርሶት ቃል እንዲሰጥ ይደረጋል። ፍትሕ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሰጠው መግለጫ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመበት ሁኔታ ነው መሆኑን ነው ያሳየን። ለምን ይሆን ተብሎ ለሚነሳው ጥያቄ መንግስት ጋዜጠኞችን ከሀገር ማባረር ስልት አድርጐት ስለያዘው ከተከሰሱት መጽሔቶችና ጋዜጦች መካከል የተባለውን የክስ መግለጫ ሰምተው ቀድመው ከሀገር እንዲሸሹ ስለተፈለገ ነው። የተነገረው የክስ መግለጫ በእኛ ሥራ ላይ በቀጣይ የሚያስከትለው ነገር የለም።
ዞሮ ዞሮ ከዚህ ክስ በስተጀርባ ያለው ፍርሀት እየተቃረበ የመጣውን በፋክት መጽሔት በተከታታይ እየቀረበ ያለውን «የሕዳሴው አብዮት»ን ነው። መግለጫውም ይህን የህዳሴውን አብዮት ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ ነው። የሕግ ክፍተት በመኖሩ የተፈፀመ ተደርጐ መወሰድ የለበትም። በፋክት ላይ የተዘገቡት የሐሰት ወሬዎች አይደሉም። እርምጃው ፖለቲካዊ ነው። ስርዓቱ በጣም ስለተደናገጠ እየተፈረካከሰ ስለሆነ መቃብሩ አፋፍ ላይ ስለቆመ የመጨረሻው ግብአት መሬቱን የሚያውጀውን የሕዳሴ አብዮትን ለመቀልበስ የተደረገ ሙከራ ነው። ይህ የአፈና ተግባር ነው።»
No comments:
Post a Comment