(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከሁለት አመት በፊት “መስጂድ አይወክለንም” የሚል ቲሸርት በማድረግ ሙስሊሙን ይሰልሉ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ ከአንድ ሳምንት በፊት ታስሮ ነበር። የታሰረበት ምክንያት ደግሞ ይኸው አሮጌ ቲሸርት ባመጣበት ጣጣ ነው። ዘገባውን ያቀረበው ፍትህ ሬድዮ እንደገለጸው ከሆነ፤ የቀድሞ የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት አፈ ጉባኤ የነበረው አቶ ፈድሉ ሀሰን ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ በ1000 ብር ዋስ ተፈቷል። ዝርዝር ዘግርባው ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል።
አቶ ፈድሉ ሀሰን የታሰሩት ጁምዐ 18/11/2006 ሲሆን ቤታቸው ላይ ታጥቦ ከተሰጡ ልብሶች አንዱ “መጅሊስ አይወክለንም” የሚል ነበር :: ይህንን የተመለከተ የአካባቢው ካድሬ ወድያውኑ ፖሊስ በመጥራት ቲሸርቱ ፎቶ እንዲነሳ በማድረግ አቶ ፈድሉን ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዟቸው ይሄዳሉ፡፡
ማክሰኞ 22/11/2006 ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ አቃቢ ህጉ ለፍርድ ቤቱ ሲያስረዳ “አቶ ፈድሉ ሃስን ለአመፅና ለሽብር ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ተገኝቶባቸዋል” በማለት በአስረጂነት መጅሊስ አይወክለንም የሚለውን ቲሸርት ጠቀሶል::
ዳኛም አቶ ፈድሉን ምላሽ ሲጠይቁ አቶ ፈደሉም “ይህንን ቲሸርት የዛሬ ሁለት አመት መስጂድ ገብተን እንድንሰልልበት የሰጠን ኢህአዴግ ነው በአሁኑ ሰዐት እኔ በቲሸርትነት እጠቀምበታለው” ሲል መልስ ስጥቷል፡፡
ዳኛው ጉዳዩን በማየት የዋስትና መብታቸው የፈቀዱ ሲሆን አቃቢ ህጉ ያላጣራሁት ነገር አለ ለ14 ቀን ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ዳኛው ይህንን ያህል ግዜ አያስፈልግም በማለት ለ አርብ 25/11/2006 ቀጠሮ ሰጥተው ነበር። አርብ በዋለው ችሎትም በ1000 ዋስ መለቀቃቸውን ለማወቅ ችለናል ፡፡
አቶ ፈድሉ ሀሰን ከመታሰራቸው 5 ውር በፊት ባለመግባባት ስራ እንደለቀቁ ምንጫችን ገልጸዋል፡፡
Source: Fitih Radio
No comments:
Post a Comment