Friday, August 15, 2014

ጋዜጠኛና መምህርት ፌቨን ከፈለኝ በህክምና ላይ እያለች አረፈች

• የመኪና አደጋ ያጋጠማት ጋዜጠኛና መምህርት በህክምና ላይ እያለች አረፈች
• በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቢሮ በኩል ድንገት የመጣ ሚኒባስ ታክሲ ገጭቶ ጉዳት እንዳደረሰባት ምንጮች ተናግረዋል።
• ሥርዓተ ቀብራ ዛሬ በየካ ሚካኤል ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 8፡00 ይፈጸማል

ባሳለፍነው ሐሙስ ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በሚኒባስ ታክሲ የመገጨት አደጋ ደርሶባት ራሷን በመሳት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና ዕርዳታ እያገኘች ያለችው ጋዜጠኛና መምህርት ፌቨን ከፈለኝ ከኮማ ብትነቃም አስቸኳይ ህክምና እንደሚያስፈልጋት ቤተሰቦቿና ወዳጆቿ ቢስታውቁም ትናንት አረፈች።

በኤፍ ኤም 97.1 “ሃሎ ሌዲስ” ፕሮግራም መሪነትና በስኩል ኦፍ ቱሞሮ መምህርነቷ የምትታወቀው ይህቺ ወጣት ጋዜጠኛ “እፍርታም”ና “ፍቅርን ፈራሁ” በተሰኙ የፊልም ስራዎቿም የምትታወቅ ተዋናይ ነበረች። ወጣቷ ባለፈው ሐሙስ የ“ሃሎ ሌዲስ” ፕሮግራሟን ጨርሳ ከስቱዲዮ በመውጣት ላይ ሳለች በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ቢሮ በኩል ድንገት የመጣ ሚኒባስ ታክሲ ገጭቶ ጉዳት እንዳደረሰባት ምንጮቻች ተናገረዋል።

ለቀናት ራሷን ሳታውቅ የቆየችው ፌቨን፤ በጥቂቱም የነቃች መሆኗን ቤተሰቦቿና ጓደኞቿ አስታውቀው ነበር፡፡ ከዶክተሮቹ አገኘነው ባሉት መረጃ መሠረት በጭንቅላቷ ውስጥ ደም በመፍሰሱ ምክንያት አስቸኳይ የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚያስፈልጋት ተናግረው ነበር፡፡ በሆስፒታሉ የሰርጂካል ክፍል ውስጥ ህክምናዋን በመከታተል ላይ ለነበረው ፌቨን ለማገዝ እንቅስቃሴ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ጋዜጠኛ፣ ተዋናይትና መምህርት ፌቨን ከፈለኝ –  አርፋለች፡፡

ለመላው ቤተሰቦቻና አድናቂዎቻ መፅናናትን እንመኛለን ነብስ ይማር!


No comments:

Post a Comment