በገጠመው የኩላሊት ሕመም በ62 አመቱ ሕይወቱ ያለፈው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በሙያው ከፍተኛ አድናቆትና አክብሮት ያገኘ የመድረክ ፈርጥ ነበር።
ትላንት ማክሰኞ ሐምሌ 24/2010 ከዚህ አለም በሞት የተለየው የአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም አስከሬን ዛሬ ከቀትር በኋላ ከነበረበት የጸበል ቦታ አዲስ አበባ ገብቷል።
በ1948 አመተ ምህረት በአዲስ አበባ ከተማ የተወልደው የኪነጥበብ ባለሙያው ፍቃዱ ተክለማርያም ላለፉት 42 አመታት በኪነጥበቡ መስክ ጉልህ አስተዋጽኦ ያደረገ ባለሙያ መሆኑ ይታወሳል።
ቴዎድሮስ፣ኦቴሎ፣ኤዲፐስ ንጉስ፣መልዕክተ ወዛደርን ጨምሮ በርካታ የመድረክ ተውኔቶችን የተጫወተውና በበርካታ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ የተሳተፈው አንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያ ፍቃዱ ተክለማርያም “ሞገደኛው ነውጤ”፣ጥቁር ደም”፣ “ሳቤላ”፣የተባሉና ሌሎች መጽሃፍትን በኢትዮጵያ ሬዲዮ በመተረክ ሁለገብ አርቲስትነቱን ያሳየ ባለሙያ ነበር።
በተወለደ በ62 አመቱ ትላንት ከዚህ አለም በሞት የተለየው የአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም አስከሬን ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።
የቀብር ስነስርአቱን የሚያስፈጽም ኮሚቴ ተቋቁሞ በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑም ተመልከቷል።
No comments:
Post a Comment