(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 9/2010) የአዲስ አበባ መስተዳድር መሬት መስጠት ማቆሙን በይፋ አስታወቀ።
የተጀመሩ ግንባታዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ከኮንዲሚኒየምና መሰል የቤት ግንባታዎች ሙሉ በሙሉ እንደሚወጣም መስተዳድሩ ግልጽ አድርጓል።
በኢንደስትሪ ግንባታ ጭምር የሚቀርቡ የመሬት ጥያቄዎች ተቀባይነት እንደማይኖራቸው በተገለጸበት በዚህ መመሪያ ከበቂ ቅድመ ዝግጅት በኋላ ጉዳዮቹን መልሶ ማየት እንደሚቻልም ተመልቷል።
ከግል የኢንደስትሪ አልሚዎች ጥያቄ በተጨማሪ የሰነድ አልባና አግባብ ባለው እክል ሳይፈቀዱ የተያዙ ቦታዎችን በተመለከተም የከተማው አስተዳደር አገልግሎት እንደማይሰጥም በይፋ ተገልጿል።
መሬት ያልተረከቡ የመኖሪያ ቤት ማህበራትን በተመለከተም የቅድመ ማጣራት ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ አግልግሎት እንደማይሰጥም የከተማው አስተዳደር አስታውቋል።
No comments:
Post a Comment