( ኢሳት ዜና ነሐሴ 23 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኮሬና በአጎራባቹ የጉጂ ብሔረሰቦች መሃከል ከ15 ወራት በላይ ያስቆጠረዉን ግጭት ለማስቆም እርምጃ በመወሰድ ላይ መሆኑን ተከትሎ፣ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርቧል። ሰልፈኞች ብሄርን መሰረት ያደረገ ጭፍጨፋ ይቁም፣ ለ 15 ወራት የተዘጋው ከዲላ አማሮ አዲስ አበባ መንገድ ይከፈትል፣ እየሞትንም ቢሆን ሃገራዊ ለዉጡን በመደገፍ ተደምረናል፣ያለ ሕዝብ ፍላጎት በቀድሞ አመራሮች አስገዳጅነት የተቋቋመዉ የሰገን አካባቢ ሕዝቦች
ዞን አይወክለንም፣ የጉጂና የኮሬ ሕዝቦች የማይነጣጠሉና የተሳሰሩ ስለሆነ ግጭቱን የሚያባብሱ ግለሰቦች ሁለቱንም ብሔሮች አይወክሉም፣ የኮሬ ሕዝብን በመከፋፈል በህዝብና ቤት ቆጠራ ላይ በሁለት ኮድ መቆጠራችን ይስተካከልልን እንዲሁም በግጭቱ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በፍጥነት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ መንግስት ተግቶ ይስራ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። በወረዳዉ ዋና ከተማ ኬሌ ከ50 ሺ በላይ የሚሆኑ ከሁሉም የወረዳ ቀበሊያት መገኘታቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አምልክቷል። በኮሪና በጉጂ መካከል ከአመት በላይ የዘለቀው ግጭት ቢቆምም፣ ተፈናቃዮች እስከሁን ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ አልተመሰሉም።

No comments:
Post a Comment