Thursday, August 23, 2018

የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ተጨማሪ ጊዜ ተጠየቀባቸው

 ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 17 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓም በመስቀል አደባባይ ላይ በደረሰው ፍንዳታ በመምራትና በማስተባበር እጃቸው አለበት የተባሉት የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ አዛዥ ተስፋዬ ኡርጌ ላይ ተጨማሪ የምርምራ ጊዜ በተጠየቀባቸው መሰረት ፍርድ ቤት የ2 ሳምንታት የቀጠሮ ጊዜ ሰጥቷል። የተጠርጣሪው ጠበቆች ግለሰቡ ከተያዘ 43 ቀናት ያለፈው በመሆኑ የዋስ መብቱ ሊከበርለት እንደሚገባ ተከራክረዋል። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩ ከግድያ እና ሽብር ተግባር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ተጨማሪ የምርምራ ጊዜ እንደሚያስፈልግ
ወስኗል። በሰኔው የቦንብ ጥቃት እጃቸው አለበት በሚል ተይዘው በእስር ላይ የነበሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቀድሞው ምክትል ኮሚሽነር ግርማ ካሳ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አባል ኮማንደር ገብረ ኪዳን አሰግዶም፣ ኮማንደር ገብረ ሥላሴ ተፈራ፣ ኮማንደር ግርማይ በርሄ፣ ኮማንደር አንተነህ ዘነበ፣ ምክትል ኮማንደር አባቡ ዳምጤ፣ ምክትል ኮማንደር አብዲሳ ጋዲሳና ምክትል ኮማንደር ጫኔ ጠቋሬ ፣ ምክትል ኢንስፔክተር ሀገሬ ቀኔሳ፣ ዋና ሳጅን ድራር ታረቀኝና ዋና ሳጅን ከድር ዓሊ ከ15 እስከ 6 ሺ ብር በሚደርስ ዋስ መለቀቃቸው ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment