Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ከኬንያ ናይሮቢ ታፍነው ከሶስት ኣመት በፊት ወደ ኣዲስ ኣበባ ኣሮጌው ኣይሮፕላን ማረፊያ የጨለማ የግዞት እስር ቤት የታሰሩት የጎጃም ብቸና ተወላጅ የሆነው አና የደቡብ ምስራቅ እዝ ባልደረባ የመቶኣለቃ ኣበባው ነጮ እና ለኦብነግ የስለላና ሰራዊት ምልመላ ያደርጋሉ በሚል ጥርጣሬ ተይዘው የነበሩት ኣብዱ ኑር፣ ኢብራሂም ኣብዱላዚዝ እና ሁሴን ኣብዱልሙኒም የተባሉ ከ፳ ቀን በፊት ወደ ከደብረዘይት ኣየር ሃይል ጀርባ በሚገኘው ምስጢራዊ የግድያ ማእከል ተወስደው ከተገደሉ በኋላ መቀበራቸውን የደሕንነት ቢሮ መረጃዎች የጠቆሙ ሲሆን እንደ ምንጮቹ ገለጻ ይህ ለሕወሓት የተለመደ ስራ መሆኑን ገልጸው በተለያዩ የደህንነት ምስጢራዊ እስር ቤቶች ከስምንት ሺህ አስከ ኣስር ሺህ የሚደርሱ አስረኞች በጨለማ ክፍል ውስጥ አንደተቆለፈባቸው ኣስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ሕዝባዊ ንቅናቄ ለማብረድ እየከበደ እንደመጣ የሕወሓት የደህንነት ሃላፊዎች የተወያዩበት ሲሆን በፍጹም የሕዋሱን ማእከል ሊያገኙት አንዳልቻሉ አና የዖሕዴድ ባለስልጣናት አና ካድሬዎች ላይ አንደለመዱት የተጠቋቆሙ ሲሆን የዖሕዴድ ባለስልጣናት ከሃገር ውጪ አንዳይወጡ ቢወጡም ሁነኛ የደህንነት ሰዎች ኣብረዋቸው አንዲሄዱ አንደሚደረግ እንዲሁም የኦሮሚያ ወጣቶችን ለማባበል ኣስፈላጊ ወጪ በማድረግ በገንዘብ አና በተለያዩ ሽልማቶች ማታለል አምቢ ያሉትን በሂደት ለማጥፋት አንደታቀደ ታውቋል፤ በተጨማሪም በዘመድ ኣዝማድ ስሞች በሕወሓት ባለስልጣናት የተሰሩ አና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ንብረቶች ጠባቂ በሆኑ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ለማድረስ እንደታሰበ ታውቋል፤በትግራይ ተወላጆች ላይ የሚደርስ የንብረት ጥፋት ማንንም ሊያሳስብ ስላልቻለ ከማሳዘን ይልቅ እያስደሰተ ስለሆነ ወደ ትግራይ ተወላጅ ኢንቨስተሮች እና እምባ ጠባቂዎች ላይ ግድያ ሳይሆን የተለያዩ የኣካል ጉዳቶች በማድረስ ድንጋጤን ለመፍጠር አና ለንቅናቄ የሚወጣውን ሕዝብ ለመምታት ታልሟል፤ሕዝቡ ከኣዲስ ኣበባ ማስተር ፕላን ተነስቶ የመብት እና የነጻነት የኣስተዳደር አና የእኩልነት መብቶቹን በቆራጥነት መጠየቅ መቀጠሉ ሲታወቅ የሕወሓት የዘረኛ ቡድን ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ መቀጠሉ አንዲሁም ግድያው አና መቁሰሉ ሕዝቡ ብርታት አና ጥንካሬን አንደሰጠው ታውቋል።ወሓት ኣሁንም በፍራቻ ውስጥ ያለ ሲሆን ሰራዊቱ ላይ ያለው እምነት ባዶ ስለሆነ ሰራዊቱ ምንም መረጃ እንዳያገኝ በወታደራዊ ደህንነቶች በኩል በጥብቅ አየተከታተለ ይገኛል:: #ምንሊክሳልሳዊ
No comments:
Post a Comment