ታኀሳስ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ህዘባዊ ተቃውሞው እንደቀጠለ ሲሆን፣ ዜጎች በህወሃት ኩባንያዎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው። ትንናት በምስራቅ ሀረርጌ ቆቦ ከተማ የተጀመረው ተቃውሞ ወደ መሰላ ከተማም ተዛምቷል። የኢህአዴግ ወታደሮች በሚወስዱት ጭካኔ የተሞባለት እርምጃ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። የስርዓቱ ወታደሮች የሚወስዱት ጭካኔ የተሞላበት የሃይል እርምጃ ያሳሰባቸው የክልሉ ነዋሪዎች፣ የህወሃት ንብረት በሆነው ሰላም አውቶብስ ላለመሳፈር እንቅስቃሴ ጀምረዋል:፡ የክልሉ ወኪላችን እንዳለው ዜጎች በሰላም አውቶቡስ አንሳፈርም ማለታቸው ብቻ ሳይሆን፣ አውቶቡሱ በአካባቢው እንዳይንቀሳቀስ እየወሰዱት ያሉት እርምጃ ስጋት ላይ የጣለው ፣ ገዢው ፓርቲ፣ በእያንዳንዱ የሰላም ባስ ተሽከርካሪ ላይ ጠባቂ ወታደሮችን ለመመደብ ተገዷል።
ባለፉት 3 ቀናት በክልሉ የነበረው የሰላም አውቶቡስ እንቅስቃሴ የቀነሰ ሲሆን፣ ትናንት በአንዳንድ የኦሮምያ አካባቢዎች የተንቀሳቀሱ አውቶቡሶች በወታደሮች ታጅበው ታይተዋል። በኦሮምያ ክልል ውስጥ በሚሰሩ በሁሉም የሰላም አውቶቡሶች ውስጥ ጠባቂ ወታደሮች መመደባቸውን ዘጋቢያችን ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአጋዚ ወታደሮች በክልሉ ህዝብ ላይ የወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ መከፋፈል መፍጠሩን፣ አንዳንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላት እየገለጹ ነው። ከፍተኛ መፈራራትና ቅሬታ አለ የሚሉት ምንጮች፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች “የተወሰደው እርምጃ ተገቢ ነው” ብለው ሌላውን ሰራዊት ለማረጋጋት እየተሯሯጡ ነው። ቅሬታው የእሰፋ በመምጣቱ በመሃል አገር ውስጥ የሚገኙ ወታደሮችና አዛዥ መኮንኖች እርስ በርስ እንዲጠባበቁ እንዳደረጋቸው አክለው ገልጸዋል።
ገዢው ፓርቲ በሚወስደው እርምጃ የተጎዱ በርካታ ዜጎች ፎቶግራፎች በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን እየተሰራጩ ነው። እስካሁን ደድረስ ባለው መረጃ ከ100 በላይ ሰዎች በወታደሮች ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ታስረዋል።

No comments:
Post a Comment