ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ሆን ብሎ ባቀነባረው የሽህ ኑሩ ግድያ ላይ እጁ አለበት በማለት ተወንጅሎ ፍርዱን ሲጠባበቅ የነበረው ሙባረክ ይመር በቂሊንጦ እስርቤት ሕይወቱ አልፏል።
በእነ አሕመድ እንድሪስ መዝገብ 9ኛ ተከሳሽ የነበረው ሙባረክ ይመር ፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ በሰላም ደርሶ ከተመለሰ በኋላ በድንገት ታሞ ወደ ሕክምና ማእከል ቢወሰድም ሊተርፍ አልቻለም። ሙባረክ ይመርን ለሞት ያበቃው የጤና እክል እስካሁን አልታወቀም።
በነቀጀላ ገላና መዝገብ 4ኛ ተከሳሽ የነበረው አብደታ ኦላንሳ እስር ቤት በደረሰበት ድብደባና እንግልት ሕይወቱን ማጣቱ ይታወሳል።

No comments:
Post a Comment