ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመግዛት ተቸግረናል ሲሉ ፣ የነዳጅ ማደያ ባለሃብቶች በበኩላቸው መንግስት ያለንን ትንሽ መጠንም ቢሆን ከመንግስት ፈቃድ ውጭ እንዳትሸጡ ተብለናል እያሉ ነው፡፡ አንድ ሳምንት በዘለቀው ችግር የባጃጅ ባለንብረቶች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል።
የችግሩ መንስኤ በነዳጅ እጥረት ቢሳበብም በአለም ደረጃ በ12 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ዋጋ ከ30 ዶላር በታች በሚሸጥበት ወቅት በሃገር ውስጥም ሊቀነስ ሲገባው እንዴት እጥረት ይኖራል የሚል ጥያቄ ህዝቡ እየጠየቀ ነው።
በሰሞኑ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በተደረገውና የተማሪዎችን ህይወት በቀጠፈው የተማሪዎች ተቃውሞ፣ ብዛት ያላቸው ባጃጆች ተማሪዎችን ጭናችሁዋል ተብለው መቀጣታቸው ይታወቃል፡፡
በሰሞኑ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በተደረገውና የተማሪዎችን ህይወት በቀጠፈው የተማሪዎች ተቃውሞ፣ ብዛት ያላቸው ባጃጆች ተማሪዎችን ጭናችሁዋል ተብለው መቀጣታቸው ይታወቃል፡፡
No comments:
Post a Comment