ታኀሳስ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቅዳሜ እለት የኢትዮጵያ የደኅንነት ኃይሎች በኢትዮ ኬንያ ድንበር ቦሪ አቅራቢያ ተሻግረው ሁለት ኬንያዊንና ሁለት የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን አግተው መውሰዳቸውን የቀጠናው ፖሊስ አስታውቋል።
የመርሳቤት ግዛት የፓሊስ አዛዥ የሆኑት ሞፋት ካንጋ እንዳሉት ግለሰቦቹ ምን እንዳደረጉ ያወቅነው ነገር የለም። በእርግጥ በኦሮሞ ሕዝብና በኢትዮጵያ መንግስት መሃከል ችግር እንዳለ እናውቃለን። የታገቱትን ዜጎቻችንን እንደሚለቁና የወሰዱብንን መሳሪያዎች እንደሚመልሱልን ተስፋ አደርጋለሁ በማለት መግለጫ ሰጥተዋል።
የኬኒያ የደህነት ባለስልጣናት ሁኔታውን እያጣሩ ሲሆን ባለፈው ወር በኢትዮጵያ የፀጽታ ኃይሎች ሶስት ፖሊሶች መገደላቸው ይታወሳል ሲል ስታንዳርድ ዲጅታል አክሎ ዘግቧል።

No comments:
Post a Comment