ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሞክሩ በድንበር ጠባቂዎች ባለፈው ወር በፖሊስ ተይዘው በእስር ሲንገላቱ የነበሩ 40 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ጨምሮ በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ካለ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩና ይሰሩ ነበሩ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያ ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው ለመለስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ሚንስቴር አስታወቁ።
የአገር ውስጥ ሚንስቴሩ ቻርለስ ኪታዋንጋ እንዳሉት ”ካለ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ በአገራችን ውስጥ የሚኖሩ ብዙ የውጭ አገር ዜጎች አሉ። ካለ ምንም ጥርጥር ሁሉንም አስረን ወደ አገራቸው እንመልሳቸዋለን።”
ስደተኞቹ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በአማካኝ ከ1 ሽህ እስከ 2 ሽህ የአሜሪካ ዶላር ለሕገወጥ ደላሎች እንደሚከፍሉ የአገሪቱ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።በ2012 እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር 45 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ሲሞክሩ በኮንቴነር ውስጥ ታፍነው ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ባለ ሁለት አሃዝ የምጣኔ ሃብት እድገት አምጥታለች እየተባለ በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ቢለፈፍም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ግን አሁንም የትውልድ ቀዬያቸውን በመተው መፍለሳቸውን አላቋረጡም።

No comments:
Post a Comment