በመረጃና ደህንነት ኤጀንሲ ( ኢንሳ) ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ አንድ ከፍተኛ ባለሙያ ለኢሳት እንደገለጸው፣ የኢትዮጵያን የመሬት መረጃ የሚሰበስብ የኢትዮጵያ ካርታ ስራ ኤጀንሲ የተባለ መስሪያ ቤት ቢኖርም፣ መንግስት ፎቶ የማንሳቱ ስራ በኢንሳ ስራ ማድረጉ የተለያዩ አላማዎችን ለማስፈጸም ነው ይላል። የመረጃ ደህንነት ኤጀንሲ በአንድ ብሄር የተያዘ፣ ከመከላከያው ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው እንዲሁም ለወያኔ ድርጀቶችና ደጋፊዎች መሬት በመስጠት ፣ የወያኔን የፖለቲካ ኢኮኖሚ ደግፈው እንዲይዙ ለማድረግ ነው ይላል። እስካሁን 46 የፎቶ መቆጣጠሪያ ምልክቶች ተስርተው ያለቁ ሲሆን፣ የአየር ላይ ፎቶ የማንሳቱ ስራ እየተሰራ እያለ ለ2 ሳምንታት በአየር ጸባይ ምክንያት እንዲሁም በአካባቢው እየተነሳ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ የአየር መቆጣጠሪያ ምልክት ለማቆም ባለመቻሉ እንዲቆም ከተደረገ በሁዋላ፣ ፎቶ የማንሳቱ ስራ እንደገና ተጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር የሚካሄደው የፎቶ ማንሳት ስራ ከመተማ እስከ ቋራ ያለውን ወደ 365 ኪሜ እርዝመት ያለው መሬት የሚሸፍን ሲሆን ፣ በሂደትም በቤንሻንጉል ክልል አካባቢ ያለውን ፎቶ የማንሳቱ ስራ ይቀጥላል።
አሁን አንገብጋቢው ነገር ይላል ባለሙያው፣ በጎንደርና በሱዳን እንዲሁም በጎንደርና በምእራብ ትግራይ የሚሰሩ የአየር መቆጣጠሪያ ምልክቶች እንዳይሰሩ የአካባቢው ህዝብ በንቃት መጠበቅ እንዳለበት ባለሙያው ገልጿል
አሁን አንገብጋቢው ነገር ይላል ባለሙያው፣ በጎንደርና በሱዳን እንዲሁም በጎንደርና በምእራብ ትግራይ የሚሰሩ የአየር መቆጣጠሪያ ምልክቶች እንዳይሰሩ የአካባቢው ህዝብ በንቃት መጠበቅ እንዳለበት ባለሙያው ገልጿል
No comments:
Post a Comment