ጥር ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ተግዳሮቶችን ለመቀየር እያንዳንዱ ዜጋ ይህንን ዘረኛ ስርዓት ለመጣል በአንድነት በፅናት መታገል እንደሚገባው ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በአቋም መግለጫውን ጠቅሷል።
“መብታቸው ለተረገጠ፤ ለተገፉ፤ አድሎ ለተፈጸመባቸው፤ ስብዓዊ መብታቸው ለተገፈፉ ዜጎች መቆም ያለብን ወቅት ላይ ነን። መደራጀትና የትኩረት አቅጣጫችንን የጋራ በሆኑ እሴቶችና ግቦች ላይ ማተኮር ያለብን ጊዜ ቢኖር ዛሬ ነው። እያንዳንዳችን እንደ ተሰጥዖአችንና እንደችሎታችን የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ ከሆንን ጠባብና ዘረኛ አእምሮ የተቸራቸውንና ሃገራችንን በዘር ጥላቻ በመመረዝ ላይ ያሉትን የህወሃት ኢህአዴግ መሪዎችን ለመተካት የሚያስችል ሙያውም ፣እውቀቱም ፣ብቃቱም ያላቸው ዜጎች አሉን።” ብሎአል።
“ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሃዘንና በመለያየት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀን ተመልካች መሆን አይገባንም። ትኩረታችን ሁሉ ፊታችን በተደቀነው ግዙፍ እንቅፋት ላይ አድርገን በዘር መከፋፈላችንን ትተን ፣ በዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተን በጋራ ከቆምን ህወሃት እኛን ሊቋቋምበት የሚችልበት ምንም አቅም አይኖረውም” ሲል ንቅናቄው በመግለጫው ጠቅሷል።

No comments:
Post a Comment