ጭማሪው በኪሎ ግራም 3 ብር ከ40 ሳንቲም ሲሆን ከፍተኛ ነው በሚል እየተተቸ ነው፡፡
ሚኒስቴሩ ለዚህ ጭማሪ የሰጠው ምክንያት የማምረቻ ዋጋ ጭማሪ አሳይቶአል የሚል ቢሆንም ለስኳር ኮርፖሬሽን ቅርበት
ያላቸው ምንጮች ግን መንግስት ከድርቁ ችግር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ በመግባቱና
ስኳር መሠረታዊ ፍላጎት አይደለም በሚል እንዲጨመር መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
የስኳር የማምረቻ ዋጋ በኪሎግራም ከ 7 ብር እንደማይበልጥ የጠቀሱት ውስጥ አዋቂዎች፣ ነገር ግን ዋጋ እንዲያረጋጉ በተቋቋሙ
ሸማች ማህበራት በኩል ለአዲስአበባ ነዋሪዎች አንድ ኪሎ በ15 ብር እንዲሸጥላቸው ሲደረግ ቆይቶአል፡፡ ካለፈው ሳምንት
ጀምሮ በድንገት የአንድ ኪሎ ስኳር ዋጋ 18 ብር ከ40 ሳንቲም እንዲሆን ተደርጎአል፡፡ ጭማሪውን
ተከትሎ በመደበኛ ሱቆች የአንድ ኪሎ ግራም ስኳር የችርቻሮ ዋጋ እስከ ብር 25 አሻቅቦአል፡፡
ይህ ያልተጠበቀ የዋጋ ጭማሪ በተለያዩ የምግብ ውጤቶች ላይ ሊንጸባረቅ ስለሚችል በቀጣይ በምግብ ነክ ውጤቶች
ላይ የማይናቅ የዋጋ ንረት ያስከለትላል የሚል ስጋት አሳድሮአል፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ የነዳጅ ምርትም በኣለም አቀፉ ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምርም፣ አሁንም መንግስት የተለያዩ
ምክንያቶችን በመደርደር የዓለም ገበያን ተከትሎ ዋጋ ለመቀነስ እምቢታ ማሳየቱ የሚታወስ ነው፡፡
የመንግስት ሰራተኞች የኑሮ ውድነቱን መቋቋም እንደተሳናቸው በተለያዩ ጊዜዎች ሲገልጹ ቆይተዋል።

No comments:
Post a Comment