ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው ነጻ የተባሉትና እንደገና ይግባኝ የተጠየቀባቸው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሽ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ አብርሃም ሰለሞን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም እንደገና ሌላ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ፣ አቃቤ ህግ በስር ፍርድ ቤት አልተመረመረልኝም ያለው ከብሄራዊ ደህንነትና መረጃ ማዕከል የተገኘው ማስረጃ፣ ማስረጃ ሳይሆን የመረጃ ትንተና የተሰጠበት ስለሆነ ‹ኦርጅናሉ› መረጃ ቀርቦ እንዲመረመር መስጠቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል።
ፍ/ቤቱ አቃቤ ህግ የታዘዘውን ማስረጃ ይዞ እንዲቀርብ ለጥር 24/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

No comments:
Post a Comment