ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በሁለት የአኝዋክና ንዌር የመንግስት ባለስልጣናት መካከል የተነሳው ጸብ ወደ ብሄረሰብ ግጭት በማምራቱ የከተማዋና አካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በከተማዋ ውስጥ እንደልብ መንቀሳቀስ አለመቻሉን የገለጹት ነዋሪዎች፣ እስካሁን ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ አለመቻሉን ገልጸዋል።
በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያቤቶች ተዘግተዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማዋ ቢሰማሩም ግጭቱን ሊያስቆሙት አለመቻላቸውንም ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።
የአኝዋ ሰርቫይቫል ዳይሬክተር አቶ ኒይካው ኦቻላ በአንድ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ አንድ ሰው መቁሰሉን፣ ኦሜንጋ በተባለ አካባቢ የሚገኙ አኙዋኮች መፈናቀላቸውንና አንድ ፖሊስን ጨምሮ 4 ሰዎችም መሞታቸውን ገልጸዋል።

No comments:
Post a Comment