(ዘ-ሐበሻ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከትናንት በስቲያ ቦምብ መፈንዳቱን ተከትሎ የተማሪዎች ሕይወት ማለፉን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው 3 ተማሪዎች መጸዳጃ ቤት ሞተው ተገኝተዋል::

ዘ-ሐበሻ እንዳነጋገረቻቸው ተማሪዎች ከሆነ በአሁኑ ወቅት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለው አለመረጋጋት እጅጉን ከቁጥጥር ውጭ ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው ቢወጡም ሌሎች ደግሞ በፌደራል ፖሊሶች እንዳይወጡ መደረጋቸው ተሰምቷል::
እጅጉን ቆሳስለው በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ሞተው የተገኙት ተማሪዎች በፌደራል ፖሊሶች መጨፍጨፋቸውን የገለጹት እነዚሁ ምንጮች በደም በመጨማለቃቸው በጥይት ብቻ ተመተው ሞቱ ለማለት ይከብዳል ይላሉ:: እንደምንጮቹ ገለጻ እነዚህ ሶስት ተማሪዎች ሳይወጉ አይቀሩም::
ከትናንት በስቲያ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፈነዳውን ቦምብ በተመለከተ መንግስታዊ ሚድያዎች ያልታወቁ ሰዎች ያፈነዱት ነው ቢሉም በአንጻሩ ሌሎች የመንግስት ወታደሮች በተማሪዎቹ ላይ ጥቃት ለማድረስ ሆን ብለው ያደረሱት ጥቃት ነው ሲሉ ይከሳሉ::

No comments:
Post a Comment