ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የታንዛኒያ ፖሊስ በሚቢያ ግዛት ማሂንቤ መንደር ውስጥ ሕገወጥ ስደተኞች ያላቸውን ተደብቀው የነበሩ ቁጥራቸው ከ83 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታውቋል።
የክልሉ የፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ፒተር ካካምባ ስደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ በከባድ መኪና በኮንትሮባንድ ተጭነው ወደ ማላዊ ለመሻገር ሲሞክሩ ተይዘዋል ብለዋል። ታንዛኒያዊ ሾፌርና ሕገወጥ ስደተኛ አዘዋዋሪ የሆነችው ሃና ሚካኖዮማ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥቆማ አብረው መያዛቸውን አዛዡ ገልፀዋል።
ስደተኞቹ በመንገድ ላይ በደረሰባቸው እርሃብና እንግልት ሳቢያ በመጎዳታቸው ምክንያት ሆስፒታል ውስጥ በማገገም ላይ መሆናቸውን ኦል አፍሪካ ዘግቧል።
ስደተኞቹ በመንገድ ላይ በደረሰባቸው እርሃብና እንግልት ሳቢያ በመጎዳታቸው ምክንያት ሆስፒታል ውስጥ በማገገም ላይ መሆናቸውን ኦል አፍሪካ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment