ታሪክ ራሱን ሲደግም! የሌላውን ሰው ልጅ ደስታ አበላሽቶ በራስ ልጅ ሰርግ መደሰት…!
ከብስራት ወልደሚካኤል
በምርጫ 1997 ዓ.ም. ወቅት የኢህአዴግን መሸነፍ ተከትሎ ሟቹ አቶ መለስ ዜናዊ በሰጡት ቀጥተኛ ትዕዛዝ በአዲስ አበባ የ14 ዓመት ዕድሜ የነበራቸው ሴትና ወንድን በመንገድ ላይ እያሉ ገደሏቸው፡፡ በዛው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ሰኔ 1997 ዓ.ም. መጨረሻ ህፃናት ያስገደሉት አቶ መለስ፤ ልጃቸው ሰመሃል መለስ የ2ኛ ደረጃ ትምህርቷን በማጠናቀቋ በሸራተን አዲስ የእንኳን ደስ ያለሽ የእራት ግብዣ አድርገው ተደሰቱ፡፡ ከነበረው ተቃውሞ ጋ ምንም ንኪኪም ሆነ ግንኙነት ያልነበራቸው ሌሎችኢትዮጵያውያን ህፃናትን በአደባባይ አስገድለው የራሳቸውን ልጅ እንኳን ደስ ያለሽ ብለው ከተዝናኑ ባለፈው ሰኔ 10 ዓመታት አለፈው፡፡
ዛሬ ደግሞ ተረኛው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትናንት ወዲያ አርብ በኢሉባቦር መቱ ሌላ አሳዛኝና የማይረሳ ታሪክ ሰሩ፡፡ ይኸውም በመቱ ወረዳ መምህር ፍፁም አባተ መኮንን በነጋታው ትናንት ቅዳሜ ታህሣሥ 30 ቀን 2008ዓ.ም. ከፍቅረኛው ፍሬህይወት በለጠ ጋ የጋብቻ ስነስርዓታቸውን ለመፈፀም ወዳጅ ዘመድ ጠርተው በዋዜማው እንደ ሀገርኛው ባህል ቤተሰብና ጓደኛ ስራ ጨርሰው በቤታቸው እየተዝናኑና እየጨፈሩ ሳለ፤ ፌደራል ፖሊስ በር በርግዶ በመግባት ፊትለፊት የተገኘውን ጫጉላ/ሙሽራ መምህር ፍፁምን በጥይት ደበደቡት፡፡

በወቅቱ ከሙሽራው በተጨማሪ ሌሎችም የተጎዱ እንዳሉ ተሰምቷል፡፡ ሙሽራው በዕለተ ሰርጉ በነ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትዕዛዝ ንፁሃን ዜጎችን ለመግደል በታዘዙ የህወሓት ወታደሮች ክፉኛ በጥይት ተመቶ ሆስፒታል እያሳለፈ ይገኛል፡፡ የወዳጅ ዘመድና የአካባው ማኀበረሰብ የሰር ደስታም ወደ ሀዘን ተቀይሮ የተሰናዳው የሰር ዝግጅት ሁሉ አብሮ ከንቱ እንዲሆን ተፈርዶበታል፡፡
ዛሬ እሁድ ጥር 1 ቀን 2008 ዓ.ም. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የመምህር ፍፁም አባተን እና የወ/ት ፍሬህይወት በለጠን ሰርግና ህይወት አበላሽተው ልጃቸው በሞቀ ሰርግና ምላሽ በቤተመንግስት ድረዋል፡፡ መምህር ፍፁም እንዳቅሙ በቤቱና ባካባቢው ሰርጉን እንዳያሳልፍ የፈረዱበት አቶ ኃይለማርያምና ግብርአበሮቻቸው የመጀመሪያ ልጃቸውን ዶ/ር ሶስና ኃይለማርያምና የልጃቸውን እጮኛ አቶ አቤል አየለን በሞቀ ሰርግ በቤተ መንግሥት ተምነሽንሸዋል፡፡ ይሄ ነው የታሪክ ድግግሞሹ! በሰው ልጅ ስቃይ የራስ ደስታን ማጣጣም፡፡
እዚህ ላይ የልጃውን ማግባትና ሰርግ መሰረግ ላይ ተቃውሞ ባይኖረኝም፣ የሰውን ልጅ ህይወት፣ ሰርግና ደስታ አበላሽቶ ልጁን በመዳር መደሰት ምን ዓይነት አዕምሮ ያለው ወላጅ አስተሳሰብ ይሆን? እንደው ለነገሩ ለንፅፅር የወረዳ ዘንድ ሙሽራውን ጠቀስኩ እንጂ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሰላማዊ ተቃውሞ እያካሄዱ የነበሩ ከ7 ዓመት ህፃን እስከ 78 ዓመት አዛውንት፣ ከ7 ወር ነፍሰ ጡር አዛውንት እናትን ከነልጅ፣ ከመምህር እስከ ገበሬ፣ እንዲሁም የ4 ልጆች እናት ሱቅ ዕቃ ልትገዛ ስትሄድ በጥይት መንገድ ላይ የገደሏትን ጨምሮ ከ140 በላይ ሰላማዊ ዜጎችን ህይወት በግፍ ቀጥፎ ለራስ ልጅ ሰርግ ሽር ጉድ ብሎ ድሮ መደሰት ምን ዓይነት ስብዕና እና ሞራል ኖሮ ይሆን?
ይብላኝ ለልጆቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው፡፡ ነገ እነሱስ ምን ይደርስባቸው እንደሆን ማን ያውቃል?
ብቻ፤ መልካሙን ያምጣልን እንጂ…

No comments:
Post a Comment