ከታሃሳስ 24 ጀምሮ እስከ ታሃሳስ 28/2008 ዓ.ም በደቡብ ጎንደር ዞን የሚገኙትን የ48 የቀበሌ አስተዳደሮችንና የቀበሌ ሊቀመንበሮች የክልሉ ባለስልጣናት በወረታ ከተማ፣ለአምስት ተከታታይ ቀናት በስብሰባ ጠምደዋቸው ሰነበቱ፡፡ ‹‹የስብሰባው ዋና አጀንዳም አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት ከፍቶብናልና በየቀበሊያቹህ ያሉትን የሚሊሻ አባላት ለጦርነት እንዴት ዝግጁ እናድርጋቸው›› የሚል እንደነበር ከቦታው የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡
ምንም እንኳን ስብሰባው አምስት ተከታታይ ቀናት የፈጀ ቢሆንም የቀበሌ ሊቀመንበሮቹና አስተዳዳሪዎቹ በተነሳው አጀንዳ ዙሪያ ፈቃደኛ አለመሆናቸውንና በግልፅ ቅዋሜያቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ይህን ተከትሎ የአገዛዙ ባለስልጣናት ለቀበሌ አመራሮቹ በዛቻ የታጀበ ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም፣የቀበሌ አስተዳደሮቹና ሊቀመንበሮቹ የመጣ ይምጣ ሲሉ መደመጣቸው ታውቋል፡፡በዚህም ለአምስት ተከታታይ ቀናት የተደከመበት ስብሰባ ያለፍሬ ተጠናቋል፡፡
ህዝባዊ ዓላማ ታጥቆ የተነሳው አርበኞች ግንቦት 7 በፀረ-ህዝብ የወያኔ ሰራዊት ላይ እያደረሰ ያለውን ጠንካራ ምት ተከትሎ የአገዘዙ ሹማሙንቶች በግልፅ የፍርሃት ማዕበል ውስጥ መዘፈቃቸውን ያሳያል ሲሉ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል፡፡

No comments:
Post a Comment