Wednesday, December 31, 2014

British security guard faces death penalty in Ethiopia after being found guilty of terrorism offences 

A British man who claims he was tortured in an Ethiopian prison is facing the death penalty after being found guilty of terrorism offences.

Ali Adorus, a security guard from east London, was subjected to electrocution, hooding and beatings during his 18-month imprisonment in the East African country, according to allegations made against Ethiopia and Britain to the United Nations High Commission.

Before leaving Britain to visit family in Ethiopia in 2012, Mr Adorus had complained that he had been targeted by MI5 and the Metropolitan Police over alleged links to Islamic extremism.

የደብረማርቆስ የመሰናዶ ተማሪዎች የመንግስትን ፖሊሲ ተቃወሙ

ተማሪዎች ኢህአዴግን እንዲመርጡ በሚል በግዳጅ በተዘጋጀው የፖለቲካ ስልጠና ላይ ተማሪዎች ፈታኝ የሆኑ ጥያቄዎችን አስተያየቶችን ሰጥተዋል ።
ኢህአዴግ እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን የመሰሉ ሰዎችን አሸባሪዎች ማለቱ ትክክል አለመሆኑን የሚገልጹት ተማሪዎች፣ ኢህአዴግን የሚበልጡት በመሉ አሸባሪ እያለ እንደሚፈርጃቸው ተናግረዋል
ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የሚኖርበት ቤት 400 ሺ ብር እንደሚከፈልበት የተናገሩት ተማሪዎች፣ አባይን መገደብ ያልቻለ መንግስት እንዴት ይህን ያክል ገንዘብ ይከፍላል ሲሉ ጠይቀዋል።
በኮምቦልቻ ደግሞ መድረኩን የሚመሩት ባለስልጣን በውጭ አገር የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ትክክለኛ መረጃ አያሰራጩም በማለት መናገራቸውን ተከትሎ ተማሪዎች በውጭ የሚገኙ ሚዲያዎች ከኢቲቪ ቀድመው መረጃ በመናገር ተአማኒነትን ማትረፋቸውን ለዚህም ደግሞ በየጊዜው የሚከዱ ባለስልጣናት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አቶ በረከት ስምኦን የሂትለር የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበረው ጆሴፍ ጎብልስ፣ ውሸት ሲደጋጋም እውነት ይሆናል ያሉትን በተደጋጋሚ እንደሚናገሩና፣ ይህንኑ በኢቲቪ ላይ ተግባራዊ እያደረጉት መሆኑን ተማሪዎች መናገራቸውን መዘገባችን ይታወቃል።
የመለስ ዜናዊን ማረፍ መጀመሪያ የሰማነው ከውጭ ሚዲያዎች ነው፣ ኢቲቪ ዜናውን የነገረን ከ2 ወር በሁዋላ ዘገይቶ በማለት በውጭ ሚዲያዎችን ላይ የቀረበውን ትችት ተከላክለዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በየጊዜው መክዳታቸው መረጃ ለማግኘት አስተዋጽኦ ማድረጉን የገለጹት ተማሪዎች፣ ኢሳት በጋዜጠኛ አበበ ቶላ ወይም አቤ ቶክቻው አማካኝነት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጋዜጠኞችን ህብረት ፕሬዚዳንትን ቃለ ምልልስ በማድረግ ያቀረበው ዘገባ፣ የመንግስት ባለስልጣናት እውነተኛ ፍላጎት የሚያሳይ ነው ሲሉ አክለዋል።
በጋምቤላ በመዠንገር አካባቢ የደረሱ ጭፍጨፋዎችንና ሌሎችንም በርካታ የአገራችን ችግሮች የሰማነው በውጭ ሚዲያው በመሆኑ፣ በሚዲያው ላይ የሚቀርበው ወቀሳ ትክክል አይደለም ብለዋል።
የብሄር ግጭትን በተመለከተ ዋናው ተጠያቂው መንግስት ነው ያሉት ተማሪዎች፣ በተለይ የትግራይን ህዝብ ከአማራውና ከኦሮሞው ጋር ለማጋጨት የሚያደርገው እንቅስቃሴ በሁዋላ ላይ አገሪቱን ይጎዳታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ተማሪዎች ካነሱዋቸው ቅሬታዎች መካከል አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በስልጤ ወራቢ ተገኝተው ስለተናገሩት እና በቀይ ባህር ላይ ስላለቁት ኢትዮጵያውያን ይገኝበታል። አንድ ጠ/ሚኒስትር እንዴት የገዛ ዜጎችን ገረድ ብሎ ይሳደባል ሲሉ የጠየቁት ተማሪዎች፣ እንዲህ አይነት ንግግር እንኳንስ አገር ከሚመራ ከተራ ዜጋም አይጠበቅም በማለት ተችተዋል። መንግስት ለመለስ ዜናዊ ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት በስርአት እንዲቀበሩ ማድረጉን ያስታወሱት ተማሪዎች፣ በቅርቡ ወደ የመን ሲሄዱ ላለቁ ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያን ሌላው ቢቀር ሰንደቃላማ እንኳን ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አለመደረጉ በዜጎች መካከል ያለውን ልዩነት የሚየሳይ ነው በማለት አክለዋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አያያዝ በአገራችን ፍትህ እንደሌለ የሚያሳይ ነው በማለት የፍትህ ስርአቱን የተቹት የመሰናዶ ተማሪዎች፣ አቶ አንዳርጋቸው ከስድስት ወራት የእስር ጊዜ በሁዋላ፣ በቤተሰብና በጠበቃ እንዳይጎበኙ፣ የታሰሩበትም እንዳይታወቅ መደረጉ የፍትህ ስርአቱ በአገራችን መቀበሩን ያሳያል ብለዋል።


Tuesday, December 30, 2014

በኮምቦልቻ የገዢውን ፓርቲ ካድሬዎች በጥያቄ ያፋጣጡ ተማሪዎች ህዝብ ልታሳምጹ ነው የሚል ማስጠንቀቂያዎች ደረሳቸው

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው እሮብ ጀምሮ ለ3 ቀናት በተካሄደው የመሰናዶና የመምህራን የፖለቲካ ስልጠና ላይ የገዚውን ፓርቲ ካድሬዎች በጥያቄ ከማፋጠጥ ጀምሮ በአገሪቱ ውስጥ በሚታየው ዘረኝነት፣ የፍትህ እጦትና ሙስና ላይ አስተያየቶችን የሰጡ ተማሪዎች ከስብሰባው መጠናቀቅ በሁዋላ ተማሪውንና ህዝቡን ለአመጽ ለማነሳሳት አስባችሁዋል በሚል ማስጠንቀቂያና ባስፈራሪያ እንደደረሳቸው ዘጋቢያችን ገልጻለች።ለተማሪዎች በሚሊኒየም ትምህርት ቤት በፕላዝማ የተደገፈ የ3 ቀናት ስልጠና ሲሰጥ፣ ለመምህራን ደግሞ በቢራሮ አዳራሽ ለ4 ቀናት የቆየ ስልጠና ተሰጥቷል። መድረኩን የሚመሩት ባለስልጣን በውጭ አገር የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ትክክለኛ መረጃ አያሰራጩም በማለት መናገራቸውን ተከትሎ  ተማሪዎች በውጭ የሚገኙ ሚዲያዎች ከኢቲቪ ቀድመው መረጃ በመናገር ተአማኒነትን ማትረፋቸውን ለዚህም ደግሞ በየጊዜው የሚከዱ ባለስልጣናት አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። አቶ በረከት ስምኦን የሂትለር የማስታወቂያ ሚኒስትር የነበረው ጆሴፍ ጎብልስ፣ ውሸት ሲደጋጋም እውነት ይሆናል ያሉትን በተደጋጋሚ እንደሚናገሩና፣ ይህንኑ በኢቲቪ ላይ ተግባራዊ እያደረጉት መሆኑን ተማሪዎች ተናግረዋል።የመለስ ዜናዊን ማረፍ መጀመሪያ የሰማነው ከውጭ ሚዲያዎች ነው፣ ኢቲቪ ዜናውን የነገረን ከ2 ወር በሁዋላ ዘገይቶ በማለት በውጭ ሚዲያዎችን ላይ የቀረበውን ትችት ተከላክለዋል።

የባህር ዳር መስዋዕትነት የማይቀረዉ ድል ዋስትና ነዉ

ወያኔ በየአመቱ ህዳር ወር መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያን ብሄር ብረሰቦች ሰብስቦ ዘፈን የሚያስዘፍንበትን በዐል ሲያከብር በተደጋጋሚ ከሚያሳማቸዉ መፈክሮች አንዱ የብሄር ብሄረሰቦች መብትና እኩልነት በህገመንግስታችን ተከበረ የሚል እጅግ በጣም አሳሳች የሆነ መፈክር ነዉ። በእርግጥም ወያኔ ለይስሙላ ወረቀት ላይ ያሰፈረዉ ህገ መንግስት መግቢያዉ ላይ “እኛ የኢትዮጵያ ብሄሮች፤ ብህረሰቦች፤ ህዝቦች በነጻ ፍላጎታችን የህግ የበላይነትና በራሳችን ፍላጎት ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ በጋራ ለመገንባት ቆርጠን ተነስተናል” ይላል። መቼም ይህ ምንም በማያሻማ መልኩ ቁልጭ ብሎ የተቀመጠ ህገ መንግስታዊ አንቀጽ ሌላ ትርጉም ካልሰጡት በቀር የአማራንም ህዝብ ያጠቃልላል የሚል ሙሉ እምነት አለን። በዚህ ደግሞ የአማራን ክልል የማስተዳድረዉ እኔ ነኝ ባዩ ባዕዴንም የሚስማማ ይመስለናል። በተግባር ሲታይ ግን ይህ የወያኔ ህገ መንግስት ላይ ህዝብና መንግስት የሚተዳደሩበት ህግ ቀርቶ ህገ አራዊት እንኳን አይመስልም። ምክንያቱም በህገ አራዊት አሰራር ተመሳሳይ ዝሪያ ያላቸዉና በአ ያላቸዉ የዱር አራዊት ይከባበራሉ እንጂ አንዱ ሌላዉን አያጠፋም። ለምሳሌ አንበሳና አንበሳ ይረዳዳሉ ወይም አብረዉ አደን ይወጣሉ እንጂ እርስ በርስ አይተላለቁም፤ ነብርና አንበሳም ቢሆኑ በተገናኙ ቁጥር ተከባብረዉ ይተላለፋሉ እንጂ አንደ ወያኔ ብጤያቸዉን ባዩ ቁጥር አያጠቁም ወይም አይገድሉም።ወረቀት ላይ የሰፈረዉን የወያኔ ህገ መንግስት የተመለከተ ሰዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎች መብታቸዉና ነጻነታቸዉ ተከብሮ የሚኖሩ ሊመስለዉ ይችላል። በእርግጥም ይመስላል። ምክንያቱም የወያኔ ህገ መንግስት ችግሩ አጻጻፉ ላይ ወይም ይዘቱ ላይ ሳይሆን በተግባር አተራጓጎሙ ላይ ነዉ። በ1987 ዓም የፀደቀዉ የወያኔ ህገ መንግስት በተግባር ሲታይ ብሄሮች፤

በአማራ ክልል በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ጉንፋን መሳይ የኢንፍሎዌንዛ (Iinfluenza Virus) ቫይረስ እንዲሰራጭ ተደረገ

በአማራ ክልል በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች ጉንፋን መሳይ የኢንፍሎዌንዛ (Iinfluenza Virus) ቫይረስ እንዲሰራጭ ተደረገ በ ደብረ ብርሃን ፣ጋይንት ፣ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረታቦር ከከተሞች ላይ ብሄራዊ የንፁህ መጠጥ ውሀ ናሙና ሰርይ እናካሂዳለን በሚል ሽፋን አቶ መኮነን ግዳይ በተባል ኤክስፐርት የሚመራ የባለሙያወች ቡድን ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች በሚገኙ መጠጥ ውሃ ታንከሮች ላይ ለጊዜው አይነቱ (sub type ) በውል ያልታወቀ እና ከ ቻይና ሃገር ከሚገኝ አንድ ኩባንያ በቀጥታ ትእዛዝ በላብራቶሪ የተመረተ ጉንፋን መሳይ የኢንፍሎዊንዛ ቫይረስ መሰራጨቱ ተገለፀ ፡፡ ከአሁን በፊትም በፋሽስት ወያኔ ትእዛዝ በሰሜን ሽዋ የሚገኝ አንድ ሃይቅ (vibero cholera ) በሚባል ባክቴሪያ ተበክሎ የነበረ ሲሆን ብዛት ያላቸው የሽዋ አርሶ አደሮች ለህልፈት መዳረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡


ኢትዮጵያ ለወሲብ ንግድና ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር መነሻ አገር ሆናለች ሲል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታወቀ

የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው የ2014 ሪፖርት ኢትዮጵያ ለግዳጅ ሥራ፣ ለወሲብ ንግድና ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተዳረጉ ወንዶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት መነሻ፤ በተወሰነ ደረጃም መዳረሻ አገር ናት ብሎአል።
አዲስ አበባ የሚገኘው ዋና የገበያ ማዕከል ከአፍሪካ ቀዳሚው የወሲብ ንግድ ቤቶች መገኛ ነው የሚለው ሪፖርቱ፣ ዕድሜያቸው እስከ 8 ዓመት የሚሆኑ ልጃገረዶች በነዚህ ቤቶች በሴተኛ አዳሪነት ተሰማርተዋል ይላል።
ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶች ከኢትዮጵያ ውጪም በተለይ በጂቡቲ፣ደቡብ ሱዳን እና በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ውስጥ በቤት
ሠራተኝነት እና በሴተኛ አዳሪነት እንዲሰሩ እንደሚገደዱ፣ ኢትዮጵያውያን ወጣት ወንዶች ደግሞ ጂቡቲ ውስጥ በሱቅ ሰራተኝነት፣ በተላላኪነት፣ በቤት ሰራተኝነት፣ በስርቆት እና በጎዳና ላይ ልመና ለግዳጅ ሥራ ተዳርገዋል ብሎአል።
በርካታ ወጣቶች ሥራ ፍለጋ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሲሰደዱ ጂቡቲ፣ ግብጽ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን ወይም የመንን እንደመሸጋገሪያ ይጠቀማሉ የሚለው ሪፖርቱ፣ አንዳንዶቹ ሊሄዱ ካሰቡበት አገር ሳይደርሱ እንደመሸጋገሪያነት ባረፉበት አገር ተይዘው ለብዝበዛ፣ለእስራት፣ለግዳጅ ስራ እና ለመታገት ይዳረጋሉ ብሎአል።

Monday, December 29, 2014

የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ!!

ታኀሳስ ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክን በመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡

የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ መሆኑን ደንግጎአል፡፡

ወያኔው የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የተከሰተውን አለመተማመን ለመቆጣጠር በድጋሚ እንቅስቃሴ ተጀመረ::

የወያኔ ተባባሪ ባለስልጣናት በውሳኔ ሰጭነት ጉዳዮች ላይ አንሳተፍም ሲሉ አማረሩ ::(ምንሊክ ሳልሳዊ)
የደህንነት አባላት ለጸረ ሰላም ሃይሎች እና ለጠላቶቻችን መረጃ እየሸጡ ነው ሲሉ በሃላፊው ተወንጅለዋል::

የመከላከያ እና የፖሊስ ሰራዊቱ ከሃገሪቱ የተቃዋሚ ሃይሎች ጋር በማበር አደጋ ሊፈጥር ይችላል ሲል መፈራቱ እንዲሁም ሰራዊቱን እየከዱ የሚሄዱ መበራከታቸው አለመተማመኑን ከማስፋቱም በላይ በሕወሓት የጦር እና ደህንነት ክፍሎች ውስጥ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል ሲሉ ውስጥ አውቂዎች ይናገራሉ::ክዚህ ቀደም ተሞክሮ እንዳልተሳካ እና አሁንም ከባለፈው አካሄድ እና ግምገማ በተሻለ መልኩ በወያኔ መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ አዳዲስ የሆኑ ውስጣዊ እርምጃዎችን በመውሰድ በተጠናከረ መልኩ በሰራዊቱ መካከል እየተከሰተ ያለውን አለመተማመን ለመቆጣጠር የሚረዱ ግምግናዎች እና የማጣሪያ ስብሰባዎች በስፋት መካሄድ የጀመሩ ሲሆን በፖሊስ ክፍሉ ውስጥ በተለይ በቡድን የሚያሴሩ ሰዎች አሉ እየተባለ ስለሚነገር የወያኔ አንድ ብሄር ሰዎችን በስፋት በመመደብ እንዲሁም ከዚህ ቀደም እንደተደረገው የቢሮ ሰራተኛውን ከደህንነት ቢሮ በሚመደቡ የሕወሓት ደህንነቶች ለመተካት የታቀደ ሲሆን ቀሪውን ከቢሮ ውጭ የሚሰራውን የፖሊስ አካል ለመቆጣጠር አዲስ ሃይል እንደሚመደብ ታውቋል።

ከጀርመን ለውህደቱ የተወከሉት የአርበኞች ግንባር አመራር አቶ ካሳዬ መርሻ አስመራ እንዳይገቡ በሻእቢያ ታገዱ:: የኢሳያስ አፍወሪቂ ጋዜጣዊ መግለጫ እና ወያኔ ከውጪ የሚኖሩ ተቃዋሚዎች ጋር የድርድር ጥያቄ እንዲያዣንብብ እየሰራ መሆኑ ታውቋል::ተወካዩን አስመራ ለማስገባት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቀጥሏል::

ከአውሮፓ ወደ ኤርትራ ለውህደቱ ስብሰባ እንዲሄድ የተወከለው በጀርመን የሚኖረው አቶ ካሳዬ መርሻ ወደ አስመራ እንዳይገባ በሻእቢያ መከልከሉ ሲታወቅ ከፊል ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታወቀው እና ከአውስትራሊያ የተወከለው የወልቃይት ተወላጅ አቶ አለልኝ ከሻእቢያ ፈቃድ ማግኘቱ ታውቋል:: ነዋሪነት በጀርመን የሆነው እና ለአርበኞች ግንባር ትግል ታላቅ አስታውጾ እንዳበረከተ የሚነገርለት አቶ ካሳዬ መርሻ በግንባሩ አባላት አስፈላጊዉን ወጪ ተሸፍኖለት ለጉዞ ሲንደረደር በሻእቢያ መከልከሉ በውጪ የሚኖሩ የግንባሩ አባላትን ያሳሰበ ቢሆንም ሁኔታውን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::

በዚህ ምክንያት በውጪ የሚኖሩ የአርበኞች ግንባር አባላት እና ደጋፊዎች የተወከለው አቶ ካሳዬ እንዳይመጣ በሻእቢያ መከልከሉን በተመለከተ ያላቸውን ተቃውሞ በደብዳቤ መላካቸው ሲታወቅ በአስመራ የሚገኙ የግንባሩ አመራሮች ሁኔታውን እንዲፈቱ በደብዳቤያቸው ያሳውቁት አባላቱ በአግባቡ የተወከለው ሰው በውህደቱ ጉባዬ ላይ እንዲገኝ ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል::የወከሉት ሰው በመከልከሉ በውህደቱ ላይ ያላቸውን ጥርጣሬም አስምረውበታል::በቂ ሃይል እና ተንካራ መዋቅር እንዳለው የሚነገርለት አርበኞች ግንባት አባላቱ በኢትዮጵያ ለሚመጣው ለውጥ ተግተው እንደሚሰሩ እና ማንም እንደማያስቆማቸው ተናግረዋል::

Sunday, December 28, 2014

አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ከምርጫ ቦርድ ጋር ከገቡት አሰጥ አገባ ጋር ተያዞ በምርጫው የመቀጠላቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑ ታውቆአል

ታኀሳስ ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየምርጫ ክልሉ ጽሕፈት ቤቶች ከታህሳስ 16 እስከ ጥር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ የሚታወቅ ቢሆንም አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ከምርጫ ቦርድ ጋር ከገቡት አሰጥ አገባ ጋር ተያዞ በምርጫው የመቀጠላቸው ነገር አጠራጣሪ መሆኑ ታውቆአል፡፡
አንድነት እና መኢአድ በመጪው ምርጫ ለመወዳደር ወስነው የምርጫ ምልክት ለቦርዱ ካስገቡት ፓርቲዎች መካከል ሲሆኑ ቦርዱ ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን ምልክት ላይ ለመወሰን ያላሟሉት የሕግ ጉዳይ አለ በሚል ሰሞኑን መግለጫ ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ ሁለቱ ፓርቲዎች አላሟሉም ከተባሉት መካከል አንዱ በፓርቲዎቹ ውስጥ ከተፈጠረ ውዝግብ ጋር ተያይዞ ትክክለኛ አመራሮቻቸውን አላሳወቁም ፣ የምርጫ ሕጉንና ሕገደንባቸውን አላከበሩም የሚለው የምርጫ ቦርድ ክስ ይገኝበታል፡፡ ፓርቲዎቹ ይህንን ችግር በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አስተካክለው እንዲቀርቡ ቦርዱ ታህሰስ 4 ቀን 2007 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ወስኖአል፡

Friday, December 26, 2014

ገዥው ፓርቲ ባህርዳር ላይ የተደረገውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ ነው

በሰልፉ የማይገኝ ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል
ገዥው ፓርቲ በአማራ ክልል አስተዳደር ባህር ዳር ከተማ የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ለመንገድና ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በባህር ዳር ቀደም ሲል የተካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ሊጠራ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡
መንግስት ታህሳስ 9/2007 ዓ.ም የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የ‹‹ፀረ ሰላም ኃይሎች እጅ እንዳለበት›› በመግለጽ ‹‹ህገ-ወጥ ሰልፍ›› ማለቱ የሚታወስ ሲሆን ባህር ዳር ከተማ የሚገኙት የቀበሌ ካድሬዎች የተደረገውን ህዝባዊ ተቃውሞ የሚቃወም የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ እያስተባበሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የቀበሌ ካድሬዎች በየ ቤቱ እየሄዱ የነዋሪዎችን ስም በመመዝገብ በሰልፉ የማይሳተፍ ሰው ቅጣት እንደሚጠብቀው እያስጠነቀቁ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ የድጋፍ ሰልፉ ታህሳስ 21 ወይንም 22 ቀን 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡



በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ሰዓት ሰልፎች ይደረጋሉ፣ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ይፋ አደረገ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ያወጣውን ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩን ዛሬ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ይፋ አድርጓል፡፡ ትብብሩ የመጀመሪያ ዙር መርሃ ግብሩን በህዳር ወር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ማከናወኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዙር መርሃ ግብሩ ደግሞ ለ2 ወራት የሚቆይ እንደሚሆን ተገልጹዋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች በሰማያዊ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት በሁለተኛ ዙር የትብብሩ መርሃ ግብር መሰረት የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 የሀገሪቱ ትላልቅ ከተሞች ላይ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች ይደረጋሉ፤ በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳርና በአዳማ ደግሞ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚደረጉ የትብብሩና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ይልቃል ጌትነት (ኢ/ር) በመግለጫው ወቅት ተናግረዋል፡፡

ከድንበር ጋር በተያያዘ በአማራና በትግራይ ክልል ከፍተኛ ውጥረት ነግሶአል

ታኀሳስ ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ታህሳስ 16 ቀን 2007 ዓም በሶረቃ ከተማ ከ70 ያላነሱ ከትግራይ ክልል የመጡ ታጣቂዎች፣ ከምስላል ወደ ስላንዴ በረሃ የሚሰራውን መንገድ ለማስቆም ተኩስ በመክፈታቸው 2 አርሶ አደሮች ሲቆስሉ፣ በአብራጅራ ወረዳ የሚገኙ ጸረ ሽምቅ እየተባሉ የሚጠሩ ሃይሎች ከህዝቡ ጋር በመሆን የአጸፋ ተኩስ በመክፈታቸው ታጣቂዎች ከአካባቢው ተሰውረዋል።
ፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው በመሄድ ህዝቡን ለማነጋገር ሙከራ በማድረግ ላይ ሲሆን፣ በአማራ ክልል በኩል ያሉ የአራት ወረዳ ህዝብ እስከ ታህሳስ 30 ድንበራችን ካልተከለለ እና የታሰሩ ሰዎች ካልተፈቱ እርምጃ እንወስዳለን በማለት ማስጠንቀቃቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል .
ሌሎች ወገኖች እንደሚሉት ደግሞ የትግራይ ክልል እያስታጠቀ የሚልካቸው ታጣቂዎች በአማራ ክልል ያሉ ብአዴኖችን እያስቆጣ ነው። ግጭቱንም የሁለቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ግጭት አድርገው የሚወስዱት ወገኖች አሉ። ሁለቱም ክልሎች የድንበር ችግሩን እስካሁን ለመፍታት አለመቻላቸው በአካባቢው ለሚነሳው ተደጋጋሚ ግጭትና ለሚጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ህወሃት ስልጣን በያዘባቸው የመጀመሪያዎቹ አመታት ከአማራ ክልል መሬት በመውሰድና ወደ ትግራይ በማካለል የቀድሞ የህወሃት ታጋዮችን አስፍሮበታል በሚል በተደጋጋሚ እንደሚተች ይታወቃል።


ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ከደቡብ ሱዳን መንግስት በቀረበባቸው ክስ ከሃላፊነት መነሳታቸው ታወቀ።

በደቡብ ሱዳን ለተሰማራው የተመድ የሰላም አስከባሪ ጦር አዛዥ የነበሩት ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ከደቡብ ሱዳን መንግስት በቀረበባቸው ክስ ከሃላፊነት መነሳታቸው ታወቀ።

ህዳር 11 ቀን 2007 ዓም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ ሱዳን በአቤይ ግዛት ተሰማርቶ የነበረው የሰላም አስካባሪ ቡድን አዛዥ ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም በእ/ኤ/አ ጁን 19፣ 2014 ተልእኮዋቸውን ጨርሰው በሜ/ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ገላልቻ መተካታቸውን ቢገልጽም፣ ኢሳት በዜና እወጃው አዛዡ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ መሰናበታቸውን ጠቅሶ ዘግቧል። የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደገለጹት ሌ/ጄኔራል ዮሃንስ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የተደረገው የደቡብ ሱዳን መንግስት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደብዳቤ መጻፉን ተከትሎ ነው።

የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት የተቀነባበረ ግድያ ድንጋጤ ፈጥሯል::

ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ካሳንቺስ ከቀድሞ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ከሚገኘው ድብቅ የደህንነት እስር ቤት ውስጥ በመገኘት በከፍተኛ የሴኩሪቲ ጥበቃ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር Greg Dorey እንዳነጋገሩ ሲታወቅ ከአንዳርጋቸው ጋር ያደረጉትን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ባይገኝም በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሲገልጹ የኤምባሲው ምንጮች እንዳሉት ስለ አንዳርጋቸው መረጃ ያላቸው ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ክፍተኛ የደህንነት አባላት እና የአንድ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል::እንዲሁም አመነስቲ ኢንተርናሽናል አንዳርጋቸውን በተመለከተ ከታፍነ 6 ወር መሆኑን ገልጾ ሁኔታው አሳሳቢ ነው ሲል ለእንግሊዝ መንግስት አቤት ያለበተን መግለጫ ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ አውጥቶ ነበር::

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ አንድ አርሶ አድር ታጣቂ ሚሊሻ በሚመስል ጸጉረ ልውጥ ሰው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ቱሪስት መገደሉ ታውቋል::የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት መገደል ድንጋጤ ፈጥሯል::ገዳዩ ለግድያው እንደተዘጋጀበት በሚያስታውቅ መልኩ በአከባቢው አድብቶ ሲጠባበቅ የነበረ እና ወዲያው እንግሊዛዊውን እንደገደለው ለፖሊስ ያለምንም ጥያቄ እጁን ሰቷል::በአከባቢዉም የታተቁ ፖሊሶች የነበሩ ሲሆን ግድያው ሲፈጸም ምንም ያደረጉት መከላከል አልነበረም::ግድያው የተቀነባበረ ነው ሲል የባህር ዳር ህዝብ እየተናገረ ነው::

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

Thursday, December 25, 2014

ኤርትራዊው አቶ በረከት በሕወሓት 40ኛ ዓመት ላይ “እኛ ብአዴኖች ወያኔዎች ነን” አሉ

ኤርትራዊው በረከት ስምዖን በሕወሓት የምስረታ በዓል ላይ እኛ ብአዴኖች (የአማራውን ድርጅት ማለታቸው ከሆነ) ወያኔዎች ነን አሉት:: ሙሉ ንግግራቸውን አስቀምጠናል ያንብቡትና ትዝብትዎን ይስጡ::
ኤርትራዊው በረከት ስምዖን በቅርቡ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ ከተከለከው ፍልፍሉ ጋር:: ኢሳት ራድዮ ፍልፍሉን ቃለምልልስ አድርጎ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ እንዳተለከለ እንዲያስተባብል ዕድል ቢሰጠውም; ተስፋ የቆረጠው ፍልፍሉ ከበረከት ጋር በሕወሓት በዓል ላይ ፎቶውን እየተነሳ ስለዲያስፖራው መስማት የሚፈልጉትን እየነገራቸው ሲያስቃቸውም አምሽቷል::ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የለውጥ ፍላጎቶች ዘመናትን ያስቆጠሩ ናቸው

Wednesday, December 24, 2014

ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት አብራሪዎች ቤታቸው ተፈተሸ

ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል ደህንነቶች ወደ ጠፉት አብራሪዎች ቤት በድንገት በመሄድ ፍተሻዎችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በቤቶች ውስጥ የተገኙ ሰነዶችን፣ የበረራ ማኑዋሎችን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ ትጥቆችንና ሌሎችም ቁሳቁሶች ወስደዋል።
ከደህንነቶች ጋር ምንም አይነት ፖሊስ ያልነበረ ሲሆን፣ ደህንነቶች ፍተሻውን ለማካሄድም የፍርድ ቤት ማዘዣ አላሳዩም። የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ አብራሪዎች በዋናው አብራሪ ተገደው መጥፋታቸውን ቢገልጽም፣ ከዋና አብራሪው ውጭ ያሉት ረደት አብራሪውና ቴክኒሻኑ ቤታቸው እንዲፈተሽ መደረጉ፣ ሚኒስቴሩ የሰጠው መግለጫ የተሳሳተ መሆኑን እንደሚያመለክት ምንጮች ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህና በመጪው ሳምንታት በድሬዳዋ ምድብ ሊደረጉ የታሰቡ የበረራ ልምምዶች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጡ ተደርጓል። ግምገማው እስኪጠናቀቅና መመሪያ እስከሚወርድ ማንኛውም የበረራ ልምምድ እንዳይደረግ የተላለፈውን ትእዛዝ ተከትሎ፣ የአየር ሃይል የደህንነት ሰዎች የተለያዩ ሰልጣኝ አብራሪዎችንና ነባሮችን እያስጠሩ በመጠየቅ መረጃ እየሰበሰቡ ነው።
የኢሳት ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ከፍተኛ የበረራ ልምድ ያላቸው ሻምበል ሳሙኤል የህወሃት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ አየር ሃይል ላይ የሚያደርሱትን ጥፋት ከሚቃወሙት የትግራይ ተወላጆች መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደግሞ በአየር ሃይል ውስጥ የተስፋፋውን ዘረኝነት ከሚኮንኑ አብራሪዎች መካከል መሆናቸው ታውቋል። ሻምበል ሳሙኤል ለ12 አመታት መቶ አለቃ ቢልልኝ ደግሞ ለ7 አመታት አየር ሃይልን አገልግለዋል።
በሌላ በኩል መንግስት አብራሪዎቹ ሄሊኮፕተሩን ኤርትራ አሳርፈውታል የሚል መግለጫ ቢሰጥም፣ የኤርትራ መንግስት እስካሁን ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠም። ኢሳት ሄሊኮፕተሩ የት እንዳረፈ ለማወቅ ያደረገው ሙከራም እስካሁን አልተሳካለትም።
ባለፉት 6 ወራት ብቻ አየር ሃይል 11 ልምድ ያካበቱ አብራሪዎችን አጥቷል። ሁሉም አብራሪዎች ከአየር ሃይል በሚጠፉበት ወቅት የሚሰጡት ምክንያት ዘረኝነት፣ የፍትህ እጦትና የአስተዳደር መበላሸት የሚል ነው።


በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ

በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ::በባህር ዳር ከተማ አንድ ኢንግሊዛዊ ቱሪስት ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አለፈ።ድርጊቱ የተፈፀመው ዛሬ ረፋድ 4 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ነው።በግድያው የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ የወንጀል ድርጊቱ እየተጣራ ነው ። የሟቹም አስክሬን በሆስፒታል እንደሚገኝ ተመልክቷል። – ምንሊክ ሳልሳዊ


አቶ መላኩ ፈንታ ጠበቆቻቸውን አሰናብተው ውሳኔ በማረሚያ ቤት እንዲነገራቸው ጠየቁ

-ሁለት ጠበቆች የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ ተላለፈባቸው

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በሚኒስትር ማዕረግ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ፣ ጥብቅና የቆሙላቸውን ጠበቆች እንዲሰናበቱና የሚያርፍባቸውን ውሳኔ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲሰሙ፣ ክሱን እየመረመረው የሚገኘውን ፍርድ ቤት ትናንትና ጠየቁ፡፡

አቶ መላኩ ፈንታ ጥያቄውን ያቀረቡት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ልደታ ምድብ ችሎት ነው፡፡ አቶ መላኩ ጠበቆቻቸውን አሰናብተው ውሳኔ ለመስማት ጥያቄ ለማቅረብ ያስገደዳቸው፣ አቶ ተሻገር ደሳለኝ የተባሉት ጠበቃቸው የምስክርንና የችሎቱን ክብር የሚነካ ንግግር እንዳደረጉ ፍርድ ቤቱ ገልጾ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በመስጠቱ ነው፡፡

በነ ሀብታሙ አያሌው የክስ ጉዳይ የተሰየመው ችሎት ‹አስገራሚ› ውሎ

ተከሳሾቹ ‹‹ዘረፋ›› ተፈጽሞብናል ብለዋል∙‹‹ለማን አቤት ይባላል?›› ሀብታሙ አያሌውበላይ ማናዬዛሬ ታህሳስ 15 ቀን 2007 ዓ.ም በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ጨምሮ ስድስት ተከሳሾች ተሟልተው ፍርድ ቤት ተገኝተዋል፡፡ችሎቱ የተሰየመው ታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ወቅት ተከሳሾች በቀረበባቸው የሽብር ክስ ላይ የሰጡትን መልስ በተመለከተ 7ኛ ተከሳሽ መልስ በዕለቱ ባለማቅረባቸው አሟልተው እንዲቀርቡ ነበር፡፡ በተጨማሪም ተከሳሾች በእስር ላይ ባሉበት ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሊጎበኟቸው የሚሄዱ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ወደ እስር ቤቱ ሲገቡ በተለየ መዝገብ እንዲመዘገቡ እየተደረጉ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበው ስለነበር ይህን በተመለከተ ማረሚያ ቤቱ ማብራሪያ እንዲሰጥ በታዘዘው መሰረት ማብራሪያውን ለመስማት ነበር፡፡የተከሳሾች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በጥየቃ ወቅት በተለየ መዝገብ ይመዘገባሉ የተባለውን አቤቱታ በተመለከተ፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በደብዳቤ መልስ መስጠቱ የተገለጸ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ‹‹ማረሚያ ቤቱ በሰጠው መልስ እስረኞች ከሌሎች በተለየ የደረሰባቸው ችግር የለም›› ማለቱን ገልጾ ይህንኑ መልስ ሙሉ ለሙሉ መቀበሉን አስታውቋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በዛሬው የችሎቱ ውሎ ላይ ተከሳሾች ለየት

የፀጋዬ በርሔ ቪላ ተሸጠ – ከኢየሩሳሌም አረአያ

የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በኋላ የፌዴራል ደህንነት ዋና ባለስልጣን የሆኑት የሕወሐት ፖሊት ቢሮ ባል አቶ ፀጋዬ በርሄ በመቀሌ ልዩ ስሙ “አፕርታይድ መንደር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ያስገነቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አረጋገጠዋል። 10 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደፈጀ የሚነገርለት የአቶ ፀጋዬ ቪላ ለአንድ ባለሃብት 25ሚሊዮን ብር እንደተሸጠ ቢነገረም በትክክል የተሸጠበትን ዋጋ ማወቅ እንዳልተቻለ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ፀጋዬ በርሄ የቅዱሳን ነጋ ባለቤት ሲሆኑ ቅዱሳን የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ናቸው።የመቀሌ ነዋሪ “አፓርታይድ መንደር” የሚል ስያሜ በሰጠው በዚህ ቦታ ከአቶ ፀጋዬ በርሄ በተጨማሪ አቦይ ስብሃት ነጋ በራሳቸውና በመጀመሪያ ልጃቸው ስም ሁለት ቪላዎችን ሲያስገነቡ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጎበዛይ ወ/አረጋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ ዘመናዊ ቪላዎችን ካስገነቡ የሕወሐት ባለስልጣናት ሲጠቀሱ ኪሮስ ቢተው በሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ በዚሁ ስፍራ ያስገነቡትን ቪላ ከ9 ወራት በፊት መሸጣቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል። በሌላም በኩል የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበሩት የሕወሐት አባል ጄ/ል አበበ ተ/ሃይማኖት (በቅፅል ስማቸው ጆቤ) በቦሌ ያስገነቡትን ቪላ በ24 ሚሊዮን ብር መሸጣቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

በባህር ዳሩ የመስቀል አደባባይ ተቃውሞ ዙሪያ አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች ህዝቡ ያቀረበውን ተቃውሞ ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ ለገዢው መንግስት ሚዲያ ተቋማት በሰጡት መግለጫ ቅር መሰኘታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታህሳስ 10 /2007 ዓ.ም ለአምስት ሰዎች ሞትና ለበርካቶች አካል መጉደል ምክንያት በሆነው የተቃውሞ ሰልፍ ዙሪያ የገዢው መንግስት አስቸኳይ  መግለጫ እንዲሰጡ ያስገደዳቸው የኃይማኖት አባቶች በመስቀል አደባባይ ዙሪያ ላይ የቀረበውን ጥያቄ በደስታ እንደተቀበሉት በመግለጫቸው መስጠታቸው እና ምዕመኑን እንደ ጥፋተኛ በመቁጠር ማግለላችው እንዳበሳጫቸው በትላንትናው ዕለት በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ በሚስጥር የተሰባሰቡት የእምነቱ ተከታዮች ተናግረዋል፡፡ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና ድምጻቸው እንዳይሰማ የፈለጉት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ የእምነቱ ተቆርቋሪዎች የቅዱስ ሚካኤልን በአል ለማክበር በተሰባሰቡበት ጊዜ ባደረጉት ውይይት ” እኛን የሚወክሉ የሃይማኖት አባቶች ለህዝቡ ይቆረቆራሉ እንጅ በህዝብ አይፈርዱም፡፡ ” በማለት ከምዕመናኑ ጎን በመቆም ድርጊቱን ያወገዙ ቢኖሩም አንዳንድ አባቶች ግን ምዕመኑን እንደ ጥፋተኛ መቁጠራቸው በከፍተኛ ሁኔታ ስሜታችውን እንደጎዳው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡የተቃውሞ ሰልፉ በተካሄደ እለት ከሰዓት በኋላ መግለጫ ከሰጡት መካከል ስብሰባውን የመሩት አባት ” የተሰጠንን የቤት ስራ አከናውነናል፡፡” በማለት ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት ለማሳወቅ

Tuesday, December 23, 2014

አስመራ የገቡት ፓይለቶች ከቤተ መንግስቱ ወደ ሆቴል ተዘዋወሩ

አስመራ የገቡት ፓይለቶች ከቤተ መንግስቱ ወደ ሆቴል ተዘዋወሩ::
‪- የድሬደዋ አየር ሃይል መምሪያ በግምገማ ታመሰ::
– መጭውን ውህደት የሚያሳፈጽሙ የአርበኞች ግንባር አባላት ከአውሮፓ እና አውስትራሊያ ተወከሉ::
Minilik Salsawi:- አርብ እለት ከድሬዳዋ ተነስተው በደቡባዊ ኤርትራ አሰብ ዘልቀው የገቡት የወያኔው አየር ሃይል አብራሪዎች እና ቴክኒሺያኖች በደህና ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ በኤርትራ የአየር ክልል የተቀበላቸው እና በ1987 አመተምህረት በወያኔ እና የደርግ መኮንኖች የሰለጠነው የሻእቢያ ኮማንዶ ጦር አጅቧቸው ወደ አስመራ ቤተመንግስት ከገቡ በኋላ በቤተ መንግስቱ ውስጥ ለሁለት ቀን በእንግዳ ማረፊያ ክፍል ውስጥ ቆይተው ወደ ሆቴል መዘዋወራቸውን ከአስመራ የተገኙ ምንጮች ጠቁመዋል::

በቤተ መንግስት ቆይታቸው አስፈላጊ ጥያቄዎች እና ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ከደምህት ጦር ጋር በመቀላቀል እየተገነባ ባለው ዘመናዊ አየር ሃይል ውስጥ አገልግሎት እንዲሰጡ የተጠየቁ መሆኑን ምንጮቹ ሲናገሩ አብራሪዎቹ ግን ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ፍላጎቱ እንዳላቸው እና አውሮፓ ሆነው ትግሉን መርዳት እንደሚችሉ ሲናገሩ ተደምጠዋል::አብራሪዎቹ እጃቸውን የሰጡትም ሆነ የተቀላቀሉት ከኤርትራ መንግስት ጋር እንጂ ከሌላ አካል ጋር እንዳልሆነ ምንጮቹ አረጋግጠዋል::

ከደብረዘይት አየር ሃይል አከባቢ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በድሬዳዋ ያለው የአየር ሃይል ካምፕ ሃላፊዎች ላይ ከፍተኛ ግምገማ ተደርጓል::በዚህም መሰረት የሃገሪት የአየር ክልል ሳይቀር ከራዳር ውጪ ነው የሚል ጉዳይ ተነስቶ መነጋገሪያ እና መገማገሚያ ሆንዋል::እርስ በርስ መወነጃጀል እንኳን ባልተደፈረበት ግምገማ ላይ እያንዳንዱ መኮንን ሃላፊነቱን ወስዶ ዋጋ ሊከፊል ዪገባዋል ሲሉ ከፍተኛ አዛዦች በቁጣ ተናግረዋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በመጪዎቹ ሳምንት በሚካሄደው የግንቦት ሰባት እና የአርበኞች ግንባር ውህደት ላይ እስካሁን ወኪል ያላከው የአርበኞች ግንባር አንድ ሰው ከአውሮፓ አንድ ሰው ከአውስትራሊያ በመምረጥ ለእህደት ስብሰባው ማስትላለፉን ምንጮቹ ተናግረዋል::የተመረጡት አስመራ እንደደረሱ በውህደቱ ዙሪያ ንግግር እንደሚጀመር እና የፊርማው ውህደት እንደሚጸድቅ ኮሎኔል ፍጹምን ዋቢ ያደረጉ ምንጮች ጠቁመዋል::


አየር ሃይል እየታመሰ መሆኑን ምንጮች ገለጹ

ታኀሳስ ፲፬(አስራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአየር ሃይል ባልደረባ የሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በጋራ በመሆን የሚያበሩትን ሄሊኮፕተር ይዘው ከጠፉ በሁዋላ የአየር ሃይል አዛዦች አስቸኳይ ግምገማ ከተጠሩ በሁዋላ እርስ በርስ እየተገማገሙና ከእነዚህ ሰዎች ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው የሚያስቡትን የአየር ሃይል አባላት ለማሰር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በተለይም የትግራይ ተወላጅ ከሆኑት ሻምበል ሳሙኤል ግዴይና ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ጋር የቅርብ ግንኙነት አላቻው የተባሉ ሰዎች እየተጠሩ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል። የመከላከያ ሚኒስትር ሻምበል ሳሙኤል ግደይን ከሃዲ ሲል ሲፈርጀው፣ መቶ አለቃ በልልኝ ደሳለኝንና ቴኒኪሻን ጸጋ ብርሃንን ደግሞ ተገደው መብረራቸውን ገልጿል።የኢሳት ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት ከፍተኛ የበረራ ልምድ ያላቸው ሻምበል ሳሙኤል

አንዳርጋቸው ጽጌ ከታፈነ እነሆ ስድስት ወር ሞላው:: እኛ ምን ሰራን

Today marks 6 months since Ethiopian opposition leader was kidnapped at Yemen international airport

Amnesty International

አመነስቲ ባወጣው መግለጫ የዛሬ ስድስት ወር በየመን አየር ማረፊያ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች የታፈነው ወደ ኢትዮጵያ የተላለፈውን የአንዳርጋቸውን ደህንነት በተመለከተ የብሪታንያ መንግስት ዜጋው ያለበትን ሁኔታ የደረሰበትን ደረጃ እንዲያሳውቅ በይፋ ጠይቋል::

Amnesty International

‘I appeal to the UK to not forget Andy and to make every effort to ensure his safety’ – partner of Andargachew Tsege

10 ቢሊዮን ብር በከንቱ ለባከነበት “የነፋስ ተርባይኖች” ቅሌት፣ ተጠያቂው ማን ነው?

“ለነፋስ ተርባይኖች” ግዢ በሚል ሰበብ በየአመቱ እንደዘበት የሚባክነው የቢሊዮን ብሮች ሃብት ሲታይ፣ በእርግጥም በኢትዮጵያ ታሪክ አቻ የማይገኝለት ቅሌት ነው ማለት ይቻላል። በየትኛውም አገር ቢሆን፣ በበለፀጉት አገራትም ጭምር፣ ከፍተኛ ሃብት በከንቱ እንዲባክን ማድረግ አሳፋሪ ተግባር ነው። አብዛኛው ህዝብ ችግረኛ በሆነባት፣ ሩብ ያህሉ ካለምፅዋት ሕይወቱን

የወደፊቱ የተሻለ የህይወት ተስፋ ያለው ወያኔ መቃብር ላይ ነው!!

ግንቦት 7ወያኔ በሀገራችን የዘረጋው ማህበራዊ ፖለቲካዊና የኢኮኖሚ ስርአት ለጠቅላላ ህዝባችን፣ በተለይ ለወደፊቱ ሀገር ተረካቢ ወጣት ሲኦል መሆኑ ቅጥሏል። በሀገሬ ውስጥ፣ ሰርቸ የተሻለ ህይወት እኖራለሁ ብሎ ማለም ቅዠት ሆኗል። ከዚህ ይልቅ ያብዛኛውን ወጣት ተስፋ ሀገር ጥሎ በገፍ መሰደድ ከሆነ ውሎ አድሯል።በእጅጉ በሚዘገንን ሁኔታ በግፍ ተሰቃይተው ከሳውዲ አረቢያ ወደሀገራቸው ከተመለሱት ከ160 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ግማሽ ያህሉ ተመልሰው መሰደዳቸውን በቅርቡ የወጣ ጥናት አረጋግጦል። በዚህ ሁኔታ ከተሰደዱ ወገኖቻችን ውስጥ ቁጥራቸው ከ70 በላይ የሚሆኑት ቀይ ባህር ላይ የነበሩበት ጀልባ ሰምጦ አልቀዋል። እነዚህ ወገኖቻችን ጉዞቸው በሞትና ህይወት መሃል መሆኑን አስቀድመው ያውቃሉ። ይህንን ያስመረጣቸው ግን የወያኔ ስርአት ነው። የ

ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አገዱ

(አዲስ አድማስ ታህሳስ 11 2007 ዓ.ም):-ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና በሰጠችው ማኅበር ላይ ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል›› ባላቸው አንዳንድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት አስተዳዳሪዎች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አፈጻጸም ‹‹ሕገ መንግሥቱንና ሰብአዊ መብትን የሚፃረር ነው›› በሚል ፓትርያርኩ ማገዳቸው ተገለጸ፡፡ ፓትርያርኩ ባለፈው ኅዳር 30 ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ ‹‹አፈጻጸሙ እንዲቆይ›› በማለት ያገዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በተካሔዱ ጉባኤዎች÷ ‹‹ተገቢ ያልኾነ ቃል ተናግረዋል፤ ይህም አነጋገር ጉባኤውን ቅር አሰኝቷል፤›› ያላቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎች፤ቀኖናዊ ምክርና ተግሣጽ እንዲሰጣቸው በአንድ ድምፅ ተስማምቶ ያሳለፈው እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

አየር ሃይል የጠፉ አብራሪዎችን መፈለጉን አቆመ

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን ኤም አይ 35 የተባለ የውጊያ ሄሊኮፕተር ይዘው በመጥፋት ወደ አልታወቀ ስፍራ የተጓዙት ሁለቱን አብራሪዎችና አንድ ቴክኒሻንን ለመፈለግ አየር ሃይል በተለያዩ አካበባዎች አሰሳ ሲያደርግ ቢቆይም በመጨረሻ ፍለጋው እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ፍለጋው እንዲቋረጥ የተደረገበት ዋና ምክንያት አብራሪዎቹ ሆን ብለው መጥፋታቸውና ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወደአልታወቀ ስፍራ መሄዳቸውን የአየር ሃይል አዛዦች ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸው ነው።
ኢሳት መጀመሪያ ላይ በደረሰው መረጃ መሰረት የጠፉት 2 አብረራዎች መሆናቸውን መዘገቡ የሚታወስ ቢሆንም፣ ከአየር ሃይል የደረሰውን መረጃ መሰረት አድርጎ ባደረገው ማጣራት የጠፉት 2 አብራሪዎችና አንድ የበረራ ቴክኒሻን መሆናቸውን ለማረጋገጥ ችሎአል። ከፍተኛ የአብራሪነት ልምድ የነበራቸው ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በመሆን ሄሌኮፕተሮቻቸውን በመያዝ የተሰወሩ ሲሆን፣ ሰዎቹ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሎአል።
ጉዳዩን በተመለከተ የአየር ሃይል ም/ል አዛዥ የሆኑትን ብርጋዲየር ጄኔራል ማሾ ሃጎስን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ይሁን እንጅ አየር ሃይሉን እና ስምሪቶችን ከጀርባ ሆነው ይመሩታል የሚባሉት የድሬዳዋ አየር ሃይል ምድብ አዛዥ ኮ/ል አበበ ተካን በስልክ ለማነጋጋር ጥረት ያደርግን ቢሆንም፣ ኮሎኔሉ ከየት እንደምንደውል ከጠየቁን በሁዋላ የምንደውልበትን ቦታና ድርጅት ስንነግራቸው፣ ” ለእናንተ ደውለውላችሁ ነበርን ?” ብለው ከጠየቁን በሁዋላ፣ እኛ መረጃ ደርሶን እንደደወልንላቸው ስንገልጽላቸው ” ዝጋ ” ብለው ስልኩን ዘግተውታል። በዚሁ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃውን እየተከታተልን የምናቅርብ መሆኑን እንገልጻለን።


Monday, December 22, 2014

ከመከላከያ ሰራዊት እንዲባረሩ የታሰቡ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ለስርአቱ ደህንነት ሲባል በቦታቸው እንዲቆዩ መደረጉ ታወቀ::

በከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊት አመራር ውስጥ በከፍተኛ ሃላፊነት ሲሰራ የነበረው ሌተናል ጄነራል አበባው ታደሰ ባለፈው አመት ከቦታው መባረሩ ተከትሎ መባረር አለባቸው ተብለው ውስጥ ለውስጥ የተጨረሰላቸው በርካታ ከፍተኛ ባለማእረግ መኮንኖች ቢኖሩም፤ ከኋላ ሊነሳ የሚችለውን ችግር ግምት ውስጥ በማስገባት በተደረገው ግምገማ ላይ በማስጠንቀቅያ ብቻ እንዲታለፉ መደረጉን ታውቋል::

መባረር አለባቸው ተብለው ከተቀመጡት ከፍተኛ መኮነኖች አብዛኛዎቹ የሌተናል ኮረኔል ማእረግ ያላቸው እንደሆኑ የገለፀው መረጃው የጄኔራል አበባው ተከታዮች ስለሆኑና እንቅፋት ስለሚፈጥሩብን ተብለው እንዲባረሩ የተወሰነባቸው ቢሆንም፤ በመጪው ምርጫ ታሳቢ በማድረግ በህዝቡ መሃል ገብተው ኢህአዴግን ለመጣል ሊያነሳሱ ስለሚችሉ ግምገማ በማድረግ በማሰጠንቀቂያ እንዲታለፉ መደረጋቸውን መረጃዎች አምልክተዋል::መረጃዉም አያይዞ እንደጠቀሰው ክምርጫ መረጋጋት በኋላ በርካታ መኮንኖች ሊባረሩ ይችላሉ::


አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን አስጠነቀቁ

ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋር በቀጥታ እየተገናኙ የሀገራችንን ጥቅምና ሰላም ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች አሉ ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ ዛሬ በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፓለቲካ ፓርቲ አባላት እየታሰሩ መሆናቸውን አስመልክቶ በቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አሸባሪ ከሚባሉ ቡድኖች በቀጥታ እየተገናኙና እያቀዱ ሀገር ለማሸበር እየዶለቱ የሚውሉ ሃይሎች መሆናቸውን በመጥቀስ መንግስት ይህንን እያየ ዝም አይልም ብለዋል፡፡
ሀገራችን እንደአንዳንድ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት እዚህም እዚያም ቦምብ የሚፈነዳባት ሀገር እንድትሆን አንፈልግም ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ፣ መንግስት በሕጋዊነት በተመሰረቱ ፓርቲዎች ውስጥ ከሽብር ቡድኖች ጋር የሚተባበሩ ግለሰብ መሪዎች ስላሉ የፓርቲው አባላት መሪዎቻችን ለምን ታሰሩ ብለው ሊጠይቁ አይገባም በማለት ተናግረዋል፡፡

ለሰላማዊ ዜጎች ጥያቄ ጥይት መፍትሄ አይሆንም! – ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ለሰላማዊ ዜጎች ጥያቄ ጥይት መፍትሄ አይሆንም! – ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

በባህርዳር ከተማ ለዘመናት የእምነት ቦታ ሆኖ ለአምልኮ አገልግሎት ሲውል የነበረ የህዝብ ይዞታ በማያውቁትና ባልመከሩበት ሁኔታ ባለሀብት እንዲያለማው በከተማው መስተዳድር ተሰጥቷል መባሉን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች ባዶ እጃቸውን ሆነው በሰላማዊ መንገድ ባሰሙት የተቃውሞ ድምጽ መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በወሰደው ዘግናኝና አሰቃቂ በጥይት የታገዘ የኃይል እርምጃ እስካሁን የአምስት ንፁኃን ዜጎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡

ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ አዛውንት እማሆይንና አካል ጉዳተኛ ጨምሮ በርካቶችን በማቁሰል የአካል ማጉደል ደርሶባቸዋል፡፡ ይህ የኃይል እርምጃ በምንም መለኪያና ሁኔታ፣ ባለሥልጣናት ጥያቄው ያስከትላል ብለው የቱንም ታሳቢ ቢያደርጉ የህግም ሆነ የሞራል መከራከሪያ ሊቀርብለት የማይችል ህገወጥና ኃላፊነት የጎደለው ‹‹መንግሥት ነኝ›› ከሚል አካል የማይጠበቅ ዘግናኝ የአረመኔ ተግባር ነው፡፡

Former US Diplomat Calls for Free and Fair Elections in Ethiopia

(VOA News) – Former US Assistant Secretary of State for African Affairs Herman Cohen said Ethiopia should not be afraid to have free and fair elections or a free press.

Cohen said the government is doing good things that it can win an election on, such as creating jobs, carrying on infrastructure development and boosting trade. But he cautioned that the government has made no move to implement his suggestions.

“Ethiopia, I believe, should open up more toward multiparty democracy. Right now, you have opposition parties that exist, but they really do not have much access to the public. The press really does not give them much voice, and journalists have been imprisoned for saying things that the government doesn’t like. So, I think it’s time for the government to loosen up because they are doing good things in Ethiopia,” he said.

የአሸባሪ ሚስት ድሮም አሸባሪ ናት ሂጃብ አውልቂ ከተባለች ለምን አታወልቅም አይደለም ሂጃብ ይቅርና ካስፈለገን ቀሚሳቸውን አሶልቀን እናያቸዋለን (አቶ አምባዬ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ)

አቡ ዳውድ ኡስማን
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙት ኮሚቴዎቻችን እና ኡስታዞቻችን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በዚህ ሳምንት የጀመረውን ሙስሊም ሴቶችን ሂጃባችሁን አውልቃችሁ ሳንፈትሻቹ አትገቡም የሚለውን ክልከላ አስመልክቶ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ሃላፊ ላቀረቡት አቤቱታ በማረሚያ ቤቱ ሃላፊ በአቶ አምባዬ ከፍተኛ ስድብ እና ዛቻ ተፈፅሞባቸው ከቢሮ በፖሊስ ተገፍትረው እንዲወጡ መደረጋቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡

የኮሚቴዎቻችን እና ወንድሞቻችን ባለቤቶች እና ሴት ቤተሰቦች ሂጃባችሁን አውልቃችሁ ሳንፈትሻችሁ አትገቡም በሚል ማረሚያ ቤቱ በዚህ ሳምንት ተግባራዊ ማድረግ በጀመረው ጸረ ህገ መንግስታዊ የሆነ የመብት ክልከላ ላይ ለማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጥያቄያቸውን ለማቅረብ ወደ ሃላፊው ቢሮ ያመሩት ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣፣ኡስታዝ ያሲን ኑሩ፣ ኡስታዝ ሰኢድ አሊ እና ኡስታዝ ባህሩ ኡመር በማረሚያ ቤቱ ሃላፊ መሰደባቸው እና ተገፍትረው ከቢሮ በፖሊስ ሃይል እንዲወጡ መደረጋቸው ታውቋል፡፡

ኢሳት ዜና 





ኢሳት ዜና :-የደቡብሱዳንፕሬዝደንትሳልቫኪርባለፈውአርብ  አዲስአበባውስጥከተቀናቃኛቸውዶ/ርሪክማቻርጋርየሰላምስምምነቱንየፈረሙትጠቅላይሚኒስትርኃይለማርያም “አስርሃለሁ” ብለውስላስፈራሩኝነውሲሉየተናገሩት “ለቀልድነው” ሲልየኢትዮጵያመንግስትመግለጹን ሰንደቅ ዘግቧል።
ሳልቫኪርከተቀናቃኛቸውዶርሪክማቻርጋርየሰላምስምምነትፈርመውወደሀገራቸውእንደተመለሱጁባየአየርማረፊያተሰብስበውለሚጠብቋቸውሰዎችበሰጡትመግለጫየኢትዮጵያውጠቅላይሚኒስትርኃይለማርያምደሳለኝእሳቸውንምሆነተቀናቃኛቸውንየሰላምስምምነቱንሳይፈርሙከአዲስአበባንቅንቅእንደማይሉእንዳስጠነቀቋቸውተናግረው ነበር።
አቶሀይለማርያምዶ/ርማቻርንባናገሩበትዕለትጠዋትእሳቸውንም፦ “ይሄንንስምምነትካልፈረምክአስርሃለሁ” እንዳሏቸውየጠቀሱትሳልቫኪር፤ እሳቸውምበምላሻቸው “በዚህችጥሩሀገርእኔንካሰርከኝእርግጠኛነኝጥሩምግብይቀርብልኛል።ስለዚህወደጁባመመለስአያስፈልገኝም።በነፃምትመግበኛለህ” ብለውመመለሳቸውንነውየገለጹት።
ይህየሳልቫኪርመግለጫብዙዎችንያስገረመሲሆን፤የኬንያውንደይሊኔሽንንጨምርበበርካታሚዲያዎችሽፋንአግኝቷል።ነገሩማነጋገሩንበቀጠለበትበአሁኑወቅትሰንደቅሳምንታዊጋዜጣስለጉዳዩጥያቄያቀረበላቸውየጠቅላይሚኒስትርሀይለማርያምደሳለኝቃልአቀባይአቶጌታቸውረዳ፤<< ፕሬዝዳንቱይሄንንቃልየተናገሩትየሰላምስምምነቱንበማስፈራራትናበጫናመፈረማቸውንለማመልከትሳይሆንለቀልድሲሉ  ነው>> በማለት ምላሽሰጥተዋል።
<<የፕሬዝዳንቱአነጋገርየሰላምስምምነቱንአስፈላጊነትበተመለከተያላቸውንቁርጠኝነትለመግለፅእንጂንግግራቸውስምምነቱንበግዴታየተፈፀመለማስመሰልአይደለም፤ሆኖምሚዲያዎችግንሁኔታውንአሉታዊበሆነመንገድማራገባቸውየተለመደነው፤ኢትዮጵያሁለቱንተቀናቃኝወገኖችየሰላምንአቅጣጫእንዲከተሉጥረቷንትቀጥላለች።የእነሱሰላምየእኛምሰላምመሆኑንበመረዳትበተሟላመልኩተሳትፎአችንንእንቀጥላለን>> ሲሉምአቶጌታቸውአክለዋል።




ፕሬዚዳንትሳልቫኪር እስካሁን ድረስ “ለቀልድስልየተናገርኩትነው>> በማለት ማስተባበያ አልሰጡም።

‹‹ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታዘን ነው›› በሚሉ ፖሊሶች የቃሊቲ እስረኞች እቃ ተበረበረ:: - የእስክንድር ነጋና የአንዱዓለም አራጌ ማስታወሻዎች ተወስደዋል::

ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች ባልታወቀ ምክንያት ‹‹ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታዘን ነው›› በሚሉ የፌደራል ፖሊሶች እቃቸው በድንገት እንደተበረበረና እንደተወሰደ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡

ዛሬ እሁድ ታህሳስ 12/2007 ዓ.ም ጠዋት ጀምሮ ቃሊቲ እስር ቤትና አካባቢው በበርካታ የፌደራል ፖሊሶች ተከቦ እንደነበር የገለጹት ምንጮቹ ባልታወቀ ምክንያት የሁሉም እስረኞች እቃ በድንገት የተበረበረ ሲሆን በተለይም ፖለቲካ ነክ ጽሁፎች የሰፈሩባቸው ማስታወሻዎችና ሰነዶች መወሰዳቸውን ከእስረኞቹን ጠይቀው እንደተረዱ ምንጮች ገልጸውልናል፡፡

ፖሊስ ባደረገው ብርበራም የታዋቂው ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ከ30 በላይ ገጽ የፖለቲካ ትንታኔ ጽሁፎች፣ እንዲሁም የአንዱ ዓለም አራጌ ማስታወሻዎች መወሰዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፖሊስ ማስታወሻዎችንና ሌሎቹንም የእስረኞቹን ንብረቶች እያስፈረመ የወሰደ ሲሆን እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ድረስ እስር ቤቱ አካባቢ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደነበሩ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አክለው ገልጸዋል፡፡

Sunday, December 21, 2014

ጠቅላይ ሚንስትሩ እና ወጣቸው (የአብስራ ዳኛቸው)

           ኢትዮጵያ ከአክሱም ሥርኦ መንግስት አንስቶ በአመራራቸው እና በማስተዳደር ቡቃታቸው እንዲሁም በአነጋገር ለዛቸው የተመሰገኑ መሪዎች ነበሯት። አሁን አሁን ግን ኢትዮጵያ የማስተዳደር ብቃት ያለው መሪ ብቻ ሳይሆን የማሰብና የመናገር ብቃት ጭምር የለው መሪ ካጣች ከሁለት አስርት አመታት በላይ ተቆጠ። አንድ የሀገር ርዕሰ- መስተዳድር ማለት ህዝብን ወክሎ በተለያዩ አለም አቀፍ ቦታዎች ላይ ንግግር ያደርጋል። ታድያ ይህ የሚይደርገው ንግግር ሀገርን ከሀገር ህዝብን ከህዝብ የማያጋጭ መሆን አለበት። ህዝብ መሪያችን መጣ ብሎ ንግግሩን በመናፈቅ የሚጠብቀው ለዛው የሚስብ፣ የተናገረውን የሚፈፅም፣ ግብረ-ገብነት የተሞላ መሆን አለበት።
        ይህን ለማለት ያነሳሳኝ ወያኔ ጠቅላይ ሚንስቴር አድርጎ ያሥቀመጣችው በአንድ ሆስፒታል ምርቃት ላይ ለተሰበሰበው ህዝብ ባሰሙት ንግግር በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ ኢትዮጵያኖችን ያሳፈረ እና የወያኔ የፕሮፓንዳ ስልት ምን ያህል የወረደ እና ከእውቀት የፀዳ እንደሆነ የታየበት አጋጣሚ ትኩረቴን ስለሳበው እንደ ኢትዮጵያዊነቴ የተሰማኝን ልበል።

Friday, December 19, 2014

የባህርዳር ህዝብ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ነው

ነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጸው ዘገባ


የባህርዳር ህዝብ ተቃውሞውን እየተቀላቀለ ነው

ዛሬ ጠዋት ባህርዳር ከተማ ላይ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ፖሊስ በኃይል ለመበተን ጥረት እያደረ ቢሆንም ህዝቡ በብዛት ተቃውሞውን እየተቀላቀለ መሆኑን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከቀበሌ 10 አባይ ማዶ ያለው መንገድ ተቃውሞውን በተቀላቀለው ህዝብ የተዘጋ ሲሆን ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድም መዘጋቱ ታውቋል፡፡ የቀበሌ 8፣ 10ና 11 ነዋሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተቃውሞውን እየተቀላቀሉ ነው ተብሏል፡፡ የአፈ ጉባኤ ጽ/ቤት አካባቢም በርካታ ህዝብ የተገኘ ቢሆንም ርዕሰ መስተዳደሩን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣናት የሉም እንደተባሉ ገልጸውልናል፡፡

ባህርዳር ከተማ ውስጥ 04 ቀበሌ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የጥምቀት ታቦት ማደሪያ ለባለሀብት ይሰጣል መባሉን ተከትሎ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ ተቃውሞውን በማሰማት ላይ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጸዋል፡፡

ምንጮቹ እንደገለጹት እጅግ በርካታ ህዝብ አደባባይ የወጣ ሲሆን፣ ሰልፈኞቹ በእምነታቸው እየተደረገባቸው የሚገኙትን ጣልቃ ገብነቶችና ሌሎቹንም ስርዓቱ እየፈጠራቸው የሚገኙትን ችግሮች የሚቃወሙ መፈክሮች እያሰሙ ይገኛሉ፡፡


Thursday, December 18, 2014

አክራሪ … አሸባሪ … የሰለቸን መንግስታዊ መዝሙር … የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አክራሪነት/አሸባሪነት የህዝቦች ስጋት ነው፡፡ – ምንሊክ ሳልሳዊ

ሃገሪቱን የሚያሰጋት የሃይማኖት አክራሪነት/አሸባሪነት ሳይሆን የፖለቲካ የበላይነት የፈጠረው አሸባሪነት ጽንፈኝነት እና አክራሪነት ነው:: ጥላችሁን እንዳታምኑ እየተባለ ሃይማኖት መንግሥታዊ ቅርጽ ይዞ እንዲወጣ ለማድረግ መሞከር አክራሪነት ነው፡፡

«መጾም፣ መጸለይ፣ ሥርዓተ-አምልኮን መፈጸም ሃይማኖታዊ አልባሳትን መልበስ ለሃይማኖቱ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ እንጂ አክራሪነት ሊባል አይችልም፤»…የአክራሪ ክርስትና ወይንም እስልምና ቡድን መኖር የክርስትና እና እስልምና ተከታዮችን በሙሉ «አክራሪ» አስብሎ ሊያስፈርጃቸው አይችልም::አክራሪ ተብሎ የሚፈረጀው የሚራመዱ የፖለቲካ ጡዘቶች በሰዎች ላይ ሌላ እምነትን በመጫን በግዳጅ እና በሃይል ሊያስገድዱ ሲሞክሩ ይህ ማለት አህበሽን እና ተሃድሶን በጥንታውያኑ እስልምና እና ተዋህዶ ላይ በኢትዮጵያ እንደተሞከረው ማለት ነው::

ንግድ ባንክ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራርን ከስራ አገደ

የሰማያዊ ፓርቲ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ አቶ እያስፔድ ተስፋዬ ከሚሰራበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአዳር ሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ በደረሰበት እስር ምክንያት ከስራው ታገደ፡፡ እያስፔድ ተስፋዬ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጨለማና ቀዝቃዛ ክፍል ታስረው ከነበሩት አመራሮች መካከል አንዱ ሲሆን ከእስር ከተፈታ በኋላ ታስሮ ስለመቆየቱ ማስረጃ ቢወስድም ለ15 ቀን ከስራ ታግዶ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡

‹‹ታስሬ መቆየቴን የሚያሳይ ማስረጃ ወደምሰራበት ቅርንጫፍ ስወስድ ከእኛ አቅም በላይ ስለሆነ ወደ ዲስትሪክት ውሰድ ተባልኩ፡፡ ዲስትሪክት ስወስድ የንግድ ባንክ ዳይሬክተር የሰው ኃይል አስተዳደር ማመልከቻና ታስረህ የቆየህበትን ማስረጃ አስገባና እነሱ ወደ ስራ ገበታህ ተመለስ ካሉህ ነው የምትመለሰው፤ እነሱ ተመለስ እስኪሉህ ድረስ ግን ወደ ስራ ገበታ መመለስ አትችልም አሉኝ፡፡ ባሉኝ መሰረትም ለሰው ኃይል አስተዳደር ደብዳቤና ከፖሊስ ጣቢያ የተሰጠኝን ማስረጃ ወሰድኩ፡፡ ዳይሬክተሩ እስኪያየው ድረስ ተብሎ አንድ ቀን ቀጠሮ ተሰጠኝ›› የሚለው እያስፔድ በቀጠሮው መሰረት ሲሄድ ጉዳዩ ለቅሬታ ሰሚ ኮሜቴ እንደተላከ፣ ነገር ግን የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባሎች ስልጠና ላይ በመሆናቸው ለ15 ቀን ስራ መግባት እንደማይችልና ለታገደበት ቀናትም ደመወዝም እንደማይከፈለው እንደተገለጸለት ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድቷል፡፡

ቀደም ሲል የሰላማዊ ሰልፉን ተከትሎ አቶ ወሮታው ዋሴ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባረሩ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
ምንጭ ነገረ ኢትዮጵያ

Wednesday, December 17, 2014

‹‹በሰላማዊ ሰልፈኛ ላይ ዱላ መሰንዘር ሽንፈት ነው›› እስክንድር ነጋ

ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች በትብብሩ ውስጥ የታቀፉ ፓርቲዎች በጠሩት የአዳር ሰልፍ ላይ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደውን አሳፋሪ እርምጃ ሰምቻለሁ፡፡ እርምጃው ሁለት ነገሮችን በጉልህ ያሳዬ ነበር፡፡ አንደኛ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሽንፍትን ያሳየ ነው፤ ሁለተኛው ደግሞ ሰላማዊ ትግሉ እየተጠናከረ መምጣቱን ያመላከተ ነው፡፡
አንተ ባዶ እጅህን መብትህን ለመጠየቅ ስትንቀሳቀስ፣ መሳሪያ ወደታጠቀ አካል በሰላም ስትገሰግስ ባለመሳሪያው ዱላውን ከሰነዘረብህ አሸናፊው አንተ ሰላማዊው ታጋይ ነህ፡፡ በትብብሩ ሰልፍ ላይ የሆነው ይኸው ነው፡፡ አሁን ሰላማዊ ትግሉ ፍጹም ሰላማዊነቱን እንደጠበቀ መጠናከር ነው ያለበት፡…፡ ሰላማዊ ትግል ላይ ልብ ማለት ያለብን ነገር አለ፤ እሱም ሰላማዊ ሆኖ መዝለቅ የሚለው ጉዳይ ነው፡፡

‹‹እኛ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጥነው ምርጫ ላይ ሳይሆን የምርጫ ሂደቱ ላይ ነው›› አቶ ግርማ በቀለ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ

ቤኒሻንጉል ጉሙዝን ለመገንጠል የሽብርተኝነት ድርጊት ፈጽመዋል በሚል የተጠረጠሩ ተከሰሱ የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ፀኃፊ አቶ ግርማ በቀለ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሰጡት አስተያየት ትብብሩ ያለ ቅድመ ሁኔታ ወደ ምርጫ እንደሚገባ በማህበራዊና በሌሎች ሚዲያዎች ተላልፏል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ያቀረብንላቸው አቶ ግርማ እንደሚከተለው መልስ ሰጥተውበታል፡፡

የቀድሞ ኢቲቪ የአሁኑ ኢብኮ ትርምስ ውስጥ ነው።

የተመልካች ድርቅ የመታው ኢቲቪ ጭንቅ ውስጥ እንዳለ ማነው የሚረዳው? ጭንቀቱ ሲጀማምረው መጀሪያ ስሙን ቀየረ።መች ችግሩ ከስሙ ሆነና!በማስከተል ሎጎውን ቀየረው።የቢቢሲን ኮፒ አድርጎ አሳየን።ይህንንም ለአንድ ወር ሳይገለገልበት አሁን በሚጠቀምበት በአረንጏዴ ቀየረው።መደበኛ ዜና መግቢያው ከአፍሪካ ዋንጫ መግቢያ ተመሳሳይ ነው።እንደውም ስፖርት የሚጀምር ይመስላል።ይህም አንድ ወር መቆየቱ እንጃ! በዚህም ስላረካ እባካቹ ተመልካቾች ሎጎ ምረጡልኝ በስምንት መቶ ምናምን ቁጥር ኤስኤምኤስ አድርጉ ይለናል።ታየኝ የሱን ሎጎ ለመምረጠ ቴክስት ስናረግ። የዚህ ጉደኛ ድርጅት መች በዚህ አበቃ አብረው ከሚሰሩት ጋርም እየተባላ ይገኛል።ተወዳጅ የሆነው ባላገሩ አይዶል ባለፈው ቅዳሜ ሳይተላለፍ ቀርቷል።አንደሰማሁት ከሆነ ከአብርሃም ወልዴ ጋር ውዝግብ ውስጥ ናቸው።ከዚህም በተጨማሪ ከዳና ድራማ አዘጋጆች ጋር አለመግባባት ተከስቷል። ለውዝግቡ ዋና ምክንያት ዳና ድራማ በሚተላለፍበት ቀን እና ሰዓት ከቀጣዩ ወር ጀምሮ ሌላ አዲስ ድራማ መተላለፍ እንደሚጀምር ከተነገረ በኃላ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።ለመሆኑ የዚህ ሁሉ ትርምስ ምክንያት ኢቲቪ ተመልካች ስላጣ ይሆን?አይደለም ቀድሞስ ተመልካች ነበረው እንዴ? ትልቅ እራስምታት የሆነበት ኢሳት ከያንዳዱ ቤት የካድሬዎችን ጨምሮ ዘልቆ መግባቱ ነው።በተለይ የሚያቀርበው ዜና ታአማኒ ከመሆኑ በተጨማሪ በመዝናኛው ፕሮግራም በታማኝ ሾ ታዋቂ አርቲስቶች በእንግድነት መጋበዛቸው ኢቲቪ ከነመፈጠሩም እንዲዘነጋ ኢሳት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል።በርግጥም ኢቢኤስም ቢሆን ኢቲቪ ተመልካች አልባ እንዲሆን መጠነኛ ተፅኖ ፈጥሯል።እናም እንሆ የኢቲቪ ትርምስ ይቀጥላል።ሳይወድ በግድ ለነፃ ሚዲያዎች ቢሮውን ክፍት የሚያረግበት ቀን እሩቅ አይደለም።
ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኑር!!!!!!ታሜ የገብርዬ ልጅ


በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ኢሳትና የግንቦት 7 ፣ በፕሮቴስታንት ደግሞ የኦነግ ሰዎች አሉ ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተናግሩ!!

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች በባህርዳር በተሰባሰቡበት ወቅት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ፣ ይህን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋም የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ መሆኑን ለማስረዳት ነው። ዶ/ር ሽፈራው ከአፋር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ” መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል? ለምንስ በአገራችን የሌለ ችግር ያመጣብናል?” በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ዶ/ር ሽፈራው ይህንን ለማስረዳት ይጠቅማል ያሉዋቸውን ምሳሌዎች አቅርበዋል።  በጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ የኢሳት ሬዲዮና ቴሌቪዥን የሲኖዶሱን ውሎ በእየለቱ ሲዘግብ የነበረው በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በሚገኙ አባላት አማካኝነት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ፣ ግንቦት7 እና ኢሳት ሃይማኖትን ለፖለቲካ እምነት ማራመጃ ለመጠቀም እንደሚፈልጉ ዋናው ማሳያ ነው ሲሉ ደምድመዋልፕሮቴስታንት ሃይማኖት ለኦነግ አላማ ማስፈጸሚያ እያገለገለ መሆኑን  የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ ኦነግ ከፕሮቴስታንት አልፎ ዋቄ ፈታንም እየተጠቀመ ነው ብለዋል አክራሪነት ስልቱን ቀየረ እንጅ አልተሸነፈም ያሉት ዶ/ር ሽፈራው፣ በሚቀጥሉት ወራት በሃይማኖት ተቋማት ላይ፣

የአርበኞችና ግንቦት ሰባት ዲሞክራሲያዊ ግንባር በአስመራ ሊመሰረት ነው::የግንቦት ሰባት አመራር አባላት አስመራ ገቡ ::

ከአስመራ ከተማ የሚገኙ ምንጮቼ በስልክ እንዳስታወኩኝ ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የሆኑት አቶ ነእመን ዘለቀ:የአቶ አንዳርጋቸው ወንድም አቶ ብዙአየሁ ጽጌ አቶ አበበ ቦጋለ እና ሌሎች የኢሳት ሪፖርተሮችን አስከትለው አስመራ የገቡ ሲሆን የአርበኞች ግንባር አመራሮች ወደ አስመራ የሚልኩትን ሰው መርጠው ባለመጨረሳቸው እንደዘገዩ ሲጠቆም እስከ እሁድ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::ዶክተር ብርሃኑ ነጋ መግባታቸውን ለማረጋገጥ ቢሞከርም ሆተሎች ጥብቅ የጸጥታ ክትትል ስለሚደረግባቸው መረጃዎች ለጊዜው እንዲዘገዩ ተደርጓል::

Tuesday, December 16, 2014

የስቃይ ድምጾች በሦስተኛ ፖሊስ

ዜጎችን በአደባባይ የሚደበድብ ‹‹መንግስት››
በላይ ማናዬ

ካዛንቺስ በተለምዶ እንደራሴ በተባለው ቦታ ቅዳሜ ህዳር 27 ቀን 2007 ዓ.ም ረፋድ ላይ የሆነው እንዲህ ነው….
በቅርቡ በሰማያዊ ፓርቲ እና በሌሎች 8 ፓርቲዎች ስምምነት የተመሰረተው የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የትግል መርሃ-ግብር ማሳረጊያ ሊደረግ በነበረው የ24 ሰዓት የአዳር የተቃውሞ ሰልፍ ያሉ ሁኔታዎችን ለመዘገብ የሰልፉ መነሻ በሆነው የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሰልፉ ይጀምርበታል ከተባለው ጊዜ መዘግየቱን አስመልክቶ ከቢሮ ወጣ ብዬ ሁኔታውን ለመቃኘት እየሞከርኩ ነበር፡፡ ድባቡ ፍጹም ዝብርቅርቁ የወጣ ነበር፡፡ ሰልፍ ለመውጣት የወሰኑት ሰዎች በቢሮው ውስጥ መሰናዷቸውን እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ከቢሮ ውጭ ያሉ ፖሊሶችና ሲቪል የለበሱ የደህንነት ኃይሎች ደግሞ ቁጥራቸው በየደቂቃው እየጨመረ አካባቢውን መክበብ ተያይዘውት ነበር፡፡

ተጨማሪ 20 ቀናት ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና የጋዜጠኞች የፍርው ቤት ውሎ

የህሊና እስረኛ የሆኑት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና የጋዜጠኞች ክስ በዛሬው እለት ታይቷል::
ተጨማሪ 20 ቀናት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን 9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ተጨማሪ 20 ቀናት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ዛሬ ታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ለ13ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ጦማርያኑና ጋዜጠኞች በጠበቆቻቸው አማካኝነት ቀደም ብሎ ተሻሽሎ በቀረበባቸው ክስ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
የተከሳሽ ጠበቆችም ተሻሻለ በተባለው ክስ ላይ አስተያየታቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ጠበቆቹ አስተያየታቸውን በጽሑፍ ከማቅረባቸው በተጨማሪ በቃል ለችሎቱ ለማስረዳት ጠይቀው የነበር ቢሆንም ፍርድ ቤቱ፣ ‹‹በጽሑፍ ካቀረባችሁ በቃል መድገም አያስፈልግም›› በሚል ሳይፈቅድላቸው ቀርቷል፡፡ጠበቆቹ ‹‹ተሻሻለ የተባለው ክስ ምንም መሻሻል የለውም›› በማለት ለፍርድ ቤቱ ለማስረዳት ቢሞክሩም፣ ችሎቱ ንግግራቸውን አቋርጦ ‹‹ክሱ በታዘዘው መሰረት መሻሻል አለመሻሻሉን መርምሮ የሚወስነው ፍርድ ቤቱ ነው›› ሲል አስረድቷል፡፡
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ጠቦቆች የቀረበውን አስተያየትና ቀደም ብሎ ለአቃቤ ህግ ክሱን እንዲያሻሽል የሰጠውን ትዕዛዝ በማገናዘብ ጉዳዩን መርምሮ ክሱ በምን አግባብ እንደተሻሻለ አይቶ ብይን ለመስጠት ለታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር


ሰበር ዜና - በኢትዮጵያ የስዊድንን አምባሳደር ጨምሮ በ12 ስዊድናውያን ላይ የመግደል ሙከራ ተደረገ

ኢሳት ራድዮ ዛሬ ታህሳስ 6/2007 ዓም እንደዘገበው በግድያ ሙከራው ላይ የስዊድን የመገናኛ ብዙሃን በብዛት እየዘገቡበት መሆኑን ያብራራል።
እንደ ዘገባው በኦሞ ስምጥ ሸለቆ ለሽርሽር የሄዱት በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች 12 ስዊድናውያን የነበሩ መሆኑን እና የተኩስ እሩምታ እንደወረደባቸው ይገልፃል።
አቶ ሞላ ይግዛው በስዊድን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፎረም ምክትል ሊቀመንበር በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል -
http://netsanetlegna.blogspot.com/2014/12/12.html
''አስራ ሁለት የስዊድን ዜጎች አምባሳደሩን ጨምሮ ይላልእዛ ላይ አራት ሰዎች የጫነው መኪና ላይ ስዊድናውያንን ለመግደል ያለመ እና ያነጣጠረ ተኩስ ነው የተከፈተው።ከእዚህ ጋር በጥያየዘ ባለፈው ጊዜ H&M የተሰኘው ድርጅትን ያጋለጠ አንድ ጋዜጠኛ በእዛ አካባቢ ወይም ደቡብ ኢትዮያ የሚደረገውን ግፍ ለዓለም ማጋለጡ እና በዓለም የሌለ ዲክታተር መባሉ ይታወቃል።ከእዛ በፊት አንድ ቀን የስዊድን የጦር ፍርድቤት ያቀረብነውን የወንጀል ክስ ተቀብሎ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቆ ነበር።በመሆኑም ይህንን ያደረገው ወያኔ ነው ሌላ ሊሆን አይችልም'' ብለዋል።

ኢሳት ራድዮ በመጨረሻ ላይ እንደገለፀው ጉዳዩን የስዊድን ጋዜጦች፣ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ሌሎች የመገናኝ ብዙሃን ሽፋን ቢሰጡትም ኢህአዲግ ም ሆነ የሚቆጣጠራቸው ራድዮ እና መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ምንም ያሉት ነገር እንደሌለ ይገልፃል።


Monday, December 15, 2014

በከፍተኛ ህመምና እንግልት ላያ ያለው የጋዜጠኛ ተመስገን ዳሳለኝ የቃሊቲው ክራሞት

ተሜን ትላንት መጎብኘት ተከልክሎ ዛሬ ግን ተፈቀደ!

Tariku Desaleng

ትላንት እሁድ ታህሳስ 5/07 ዓ.ም ተሜን ለመጠየቅ ታላቅ ወንድማችን ባሳዝነው ደሳለኝና ሰውዓለም ታዬ ወደ ቃሊቲ አምርተው ነበር፡፡ እኔ ደግሞ ዛሬን እንኳን ልረፍ ብዬ የነርሱን መምጣት ለመጠበቅ ወስኛለሁ፡፡ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ በማለዳ ስደውል ግን የሰማሁት የጠበኩትን አልነበረም፡፡ በተመስገን ጉዳይ ላይ ምንም ብሰማ ላለመራድ በመወሰኔ ተረጋግቼ ማውራቴን ቀጠልኩ፡፡ “ደርሰናል፤ ተመስገንን መጠይቅ ግን አትችሉም” ብለውናል ሲሉ ነገሩኝ፡፡ አልደነገጥኩም፤ ሰሞነኛው የእስር ቤቱ አስተዳደር ተከታታይ እርምጃ ይሄ እንደሚመጣ ይናገር ነበር፡፡

አቶ ሽመልስ ከማል ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር በመጋጨታቸው አኩርፈው ቤት መቀመጣቸው ተሰማ

ታኀሳስ ፮(ስድት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ።
የአቶ ሽመልስን ሃላፊነት ደርበው እየሰሩ ያሉት በቅርቡ ከዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተርነት ተነስተው የመንግስት ኮምኒኬሽን ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን የተሾሙት አቶ እውነቱ ብላታ ናቸው።

ምርጫ ቦርድ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ተሰማ

ለጋሾች ይሰጣሉ ተብሎ የነበረው 7.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አልተገኘም

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው 5ተኛው አገራዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአንድ ለጋሽ ድርጅት ተወካይ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጀት ከለጋሾች በተለይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) ከመሳሰሉ ለጋሾች ከሚገኝ እርዳታ የሚመነጭ ቢሆንም ለ2007 ዓ.ም ምርጫ ለጋሾች ለምርጫ ቦርድ እርዳታ ባለመስጠታቸው ቦርዱ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከተለያዩ ለጋሾች 7.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማሰባሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ድጋፍ እንዳላገኘ ተወካዩ ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በተለይ በምርጫ ወቅት በጀቱን ያሳውቅ የነበር ቢሆንም የዘንድሮውን አመት በጀት ይፋ እንዳላደረገ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከለጋሽ አገራትና ድርጅቶች ይሰበሰባል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ገንዘብ ባለመሰብሰቡ እንደሆነ ተገምቷል፡፡

የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገንዘብ የሚያሰባስብባቸው እና ከአሁን ቀደም ምርጫ የታዘቡ አካላት በዘንድሮው ምርጫ በታዛቢነት እንደማይቀርቡ መገለጹ ይታወሳል፡፡


Sunday, December 14, 2014

የፈሪ ዱላ ነፃነትን አያስቀርም !

ህወሃቶች ኢትዮጵያን “ለመምራት” ያላቸው አቅም ተሟጦ አልቋል። ፍርሃት አቅላቸውን አስቷቸዋል። ፍርሃታቸው ጭካኔን ወልዷል። ይህ ጭካኔያቸው ወሰን አጥቷል። ልጥ ባዩ ግዜ እባብ እየመሰላቸው ልጡን በቆመጥ ሲደበድቡ ውለው ያድራሉ። ፍርሃት ያ ደካማ ማሰቢያቸውን ጥርቅም አድርጎ ዘግቶታል። የፈሪ ዓይን ማየት እንደማይችል፤ ጆሮውም መስማት እንደተሳነው ከህወሃቶች ተርድተናል።እኛ ግን እንዲህ እንላለን ህወሃቶች ዓይናችው እያየ፤ ጆሮዋቸውም እየሰማ የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነቱን ይቀዳጃል። እውነት እውነት እንላችኋለን የነፃነቱ ግዜ እሩቅ አይደለም። ህወሃቶች ከነፍርሃታቸው ወደ መረጡት መቃብራቸው መውረዳቸው እንደማይቀር ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለንም።የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ ነፃነት ነው።ይህን ነፃነት ከህወሃቶች እጅ ለምነን የምናገኘው አይደለም። ነፃነታችንን ታግለንና አሸነፈን የምንቀዳጀው ንፁህ ሃብታችን ነው። ይህን ንፁህ ሃብታችንን በቀማኞች አስነጥቀን ዝም ብንል እርግማን ይሁንብን ያሉ ኢትዮጵያዊያን እያደረጉ ያሉት ትግል ተስፋ ሰጪ ነው። በተለይም ወጣቶች እምቢ ለክብሬ፤ እምቢ ለነፃነቴ እምቢ ለማያውቁን ህወሃቶች ማለታቸውን ስናይ ተስፋችን ከመቸውም ግዜ በላይ ለምልሟል።ህወሃቶች ኃላፊነት የሚሰማቸው ቢሆኑ ኑሮ “በሃሳባችሁ ባንስማም ልዩነታችሁን መግለፅ የምትችሉበትን መብት ለማስከበር እሰከ ሞት ድረስ እንቆማለን” ይሉ ነበር። አለመታደል ሁኖ ህወሃቶች

የወያኔ መንግስት እስካሁን ድረስ በአፋር ህዝብ ላይ ያየውን ትዕግስት እንደ ፊራቻ ወይም አለማወቅ ወሰዶታል

በአፋር ህዝብና በዒሳ ብሄረሰብ መሀከል ለብዙ ዘመናት የቆየው የብዙ ሰዎች ህይዎት ያለፈበት የድምበር ግጭት በብዙ መንግስታት ዘላቂ መፍትሄ ሳያገኝ ለዚህ አሰከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይሁንና የአፋር ህዝብና ሶማሊኛ ተናጋሪው የዒሳ ብሄረሰብ አሁንም በኢህአዴግ መንግስት ዘላቂ መፍትሄ አላገኘም። ባለፉት ሁለት አስር አመታት የደቡብ አፋር ነዋሪዎችና ዒሳዎች መሃከል በተከሰተው ደም አፋሳሽ በሆነው ግጭት ከሁለቱም ብሄሮች ብዙ ሰዎች ሞተዋል። ከሶማሌ ክልል ከሺኒሌ ዞን በኮንትሮባንድ ስራ ወደ አፋር ክልል እየተጠጉ እዛ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የአፋር ነዋሪዎችን በማሸበር የአፋር መሬትን በሃይል መያዛቸውን የሚነገርላቸው ዒሳዎች ከዚህም ባለፈ የብዙ አፋሮችን ግመሎች፣ ከብቶችና ንብረቶች ዘርፈዋል።

ወዛደር እና ወታደር ይለይለት! – ከዳንኤል ፈይሳ

(ጨዋታው ተጀምረ፡፡ ይህ ጨዋታ ለሕዳሴው ግድብ ድጋፍ ሲባል የሚደረግ መሆኑን ያለማሳወቅ አያስፈልግም፡፡ ያለእንደዚህ ያሉ የድጋፍ ሰጪ ጨዋታዎች የህዳሴው ግድብ ፕሮጄክት አይጠናቀቅም ሲሉ ቃል አቃባዩ እንጂነር ስመኘው ገልፀዋል፡፡)

በሃገራችን ኢትዮጵያ እንደ ውሃ ወለድ በሽታዎቻችን ብዛት ሁሉ ሁኔታ-ወለድ የሆኑ ብዙ ክስተቶች ያጋጥማሉ፡፡ከነዚህ መሃል በተለይ በፖለቲካው መስክ ሰዎች የሚያገኙት ስፍራ ከማንነታቸው ጋር የማይገጥም እየሆነ ተቸግረናል፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረው የወታደሮቻችን ሁኔታ ነው፡፡ ጉዳዩ እንኳን ለእኛ ለሲቪሎቹ ለራሳቸውም ለወታደሮቹ እንደቸገራቸው ያስታውቃል፡፡እና ካወቅክ ምን ትቀባጥራለህ?! እና ካልቾ!.. ከቀረበልኝ ግን ‹‹እኔን ስትጠልዝ ጎሉ ወዳንተ ነው የሚገባው!›› ከማለትውጪ ምን እላለሁ? – ምንም፡፡(0 ለ 1)እንዴት ቢሉ ዳኛው ፍትሃዊ ነዋ! (0 ለ 1) አላልኳችሁም ?..ጨዋታው ቀጥሏል፡፡

ሕወሐት ደ/ፂዮንን ጠ/ሚ/ር ለማድረግ አቅዷል * የአዜብና የደህንነቱ ሹም ያልታሳካ እቅድ


(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ የተካሄደው የአራቱ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በብአዴንና ኦህዴድ በኩል ቅሬታና ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ የሕወሐት አመራሮች ስልጣኑን በእጃቸው ለማስገባት ቆርጠው መነሳታቸውን

Saturday, December 13, 2014

አገር ውስጥ እየኖሩ መሞት፣ በስደት ጉዞ መሞት፣ በስደት እየኖሩ መሞት!

* አገር ውስጥ “ባርነት”፤ ከአገር ተሰድዶ “ባርነት”ከጥቂት ቀናት በፊት በአገራቸው መኖር ያቃታቸው 70 ኢትዮጵያዊያን ቀይ ባህርን በጀልባ አቋርጠው ወደ የመን ሲያመሩ በደረሰ አደጋ ሁሉም መሞታቸው ተገልጾዋል። ኢህአዴግ እነዚህ በእርግጥ ኢትዮጵያውያን ለመሆናቸው ማስረጃ እንደሌለውና “እያጣራ” መሆኑን በቃል አቀባዩ በኩል ተናግሯል፡፡በዚህ ዓይነት ሁኔታ ከአገራቸው እየተሰደዱ ለባህር፣ ለአውሬ፣ … የተዳረጉት ወገኖቻችን ብዛት ተቆጥሮ አያልቅም፡፡ ይህንን ሁሉ አልፈው ወዳሰቡት የደረሱት ደግሞ በስደት የሚኖሩባቸው በተለይ የአረብ አገራት ይህ ነው የማይባል ሰቆቃ ይደርስባቸዋል፡፡ ይህንን ሁሉ የሚሰማው ወገን አሁንም በየኤምባሲው ቪዛ ለማስመታት በተገኘው ቀዳዳ ከአገሩ ለመውጣት ይጥራል፡፡ በዚህ በኩል ያልተሳካለት ድንበር በማቋረጥ አስጨናቂውንና አስፈሪውን ጉዞ ይጀምራል፡፡“አገር እየለማች” ነው ለሚለው ኢህአዴግ ይህ ምንም ዓይነት ምላሽ የሚሰጥበት

Friday, December 12, 2014

አንዳርጋቸው ፅጌ እንዴት ተያዘ?

አንዳርጋቸው ፅጌን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት የ2014 የፋሲካ በአል በዋለ ማግስት ነበር። ወደ ለንደን
መንገድ ስለነበረው ከተከዜ በረሃ ወደ አስመራ መጥቶ ሳለ ደወለልኝና ተገናኘን። ሳገኘው ታሞ ነበር። ከምግብ
ወይም ከውሃ ጋር የተያያዘ ቀላል ህመም እንደሆነ ነገረኝና ወደ ፋርማሲ ሄደን መድሃኒት ገዛን።እየደወልኩ ስለ ጤንነቱ ስጠይቀው ቆየሁ። በሶስተኛው ቀን ተሲያት ላይ ይመስለኛል ወደ ቤቱ ብቅ
አልኩ። የግቢውን በር ገፍቼ ስገባ አንዳርጋቸው በሁለት እጆቹ ልሙጥ የባህር ድንጋዮችን ተሸክሞ ቁጭ ብድግ
እያለ ስፖርት ሲሰራ አገኘሁት። ማጅር ግንዱ በላብ ርሶአል። ግቢው ውስጥ ካለችው የብርቱካን ዛፍ ላይ
ያንጠለጠለውን ፎጣ አንስቶ ላቦቱን ማደራረቅ ያዘ።

በረንዳው ላይ ቁጭ ብለን ጥቂት ካወጋን በሁዋላ ለመሄድ ተነሳሁ። በዚህ ጊዜ ከሶስት ቀናት በሁዋላ ወደ
ለንደን ለመሄድ ትኬቱን እንደቆረጠ ገልፆልኝ በነጋታው ምሽት የራት ቆይታ እንድናደርግ ጠየቀኝ። ሁለታችንም
በጋራ የምናውቀውን ሰው ስም ጠቅሶም በራት ቆይታው ላይ እንደሚገኝ ጠቆመኝ። ተስማማሁና ቀጠሮ ያዝን።
በነጋታው በቀጠሮአችን መሰረት ተገናኘን። ምንም ልዩ ርእሰ ጉዳይ አልነበረንም። ስለ አካባቢያችን

አስራ አንዱን የማዕከላዊ ገራፊዎችን እወቋቸው

ከዳዊት ሰለሞንበማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ጋዜጠኞችን፣ፖለቲከኞችን፣የሀይማኖት ምሁራንና ያለ ምንም ተሳትፎ ኦሮሞዎች በመሆናቸው ብቻ በኦነግነት ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ መተኪያ አልባ ዜጎችን በማሰር ቃላት ሊገልጸውና የሰው ልጅ ሊሸከመው አይችልም ተብሎ የሚታሰብን ሰቅጣጭ ድርጊት በመፈጸም ረገድ ወደር የሌላቸው ገራፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ ተደርጓል፡፡እነዚህ ሰዎች አሁንም በዚሁ ድርጊታቸው ጸንተው ወንድሞቻችንን እያሰቃዩ የሚገኙ በመሆናቸው ህዝብ ሊያውቃቸውና ቀን ሲወጣም ፍትህ ሊጠይቅባቸው ይገባዋል፡፡

ግንቦት ሰባት ሆይ…. ከሄኖክ የሺጥላ

ውድ ወዳጆቼ ሆይ ፣ ዛሬ ተክሌን መሆን አምሮኛል ( ተክሌ ይሻውን ሳይሆን ተክለሚካዔል ሳህለ ማርያምን )። ልጅ ተክሌ መቼም እኔ’ነቴን ለምን ወሰድክብኝ እንደማትለኝ ነው ። እንኩዋን እኔነት ፣ የእኔነት መፈጠሪያ የሆነችውን ሀገርህን ወስደዋትስ የለ ።የዛሬ ጽሁፌ የሚያጠነጥነው ትልቁንና እና ጠንካራውን ድርጅት ግንቦት ሰባትን ላይ ነው ። እንደውም ጽሁፌን ከማውጠንጠን ማነጣጠር ሳይሻል አይቀርም ( የታጠቀን እንዲያ ነው እንጂ !) ። እና የምወደውን ግንቦት ሰባት ፣ ባልሞትለት እንክዋ የምደማለት ግንቦት ሰባትን ፣ የኔ የምለውን ግንቦት ሰባት ፣ የ አንዳርጋቸውን ግንቦት ሰባት ፣ የብርሃኑ ነጋን ግንቦት ሰባት ፣ የዔፍሬም ማዴቦን ግንቦት ሰባት ፣ የአበበ ገላውን ግንቦት ሰባት ፣ አዎ ስለሱ ነው ።

የወያኔ/ኢሕአዴግ የውስጥ መተራመስ ቀጥሏል:: በአዲስ አበባ ከወትሮው በተለየ መልኩ ውጥረት ነግሷል::

- የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በዚህ ከቀጠለ ወያኔ እድሜ አይኖረውም::
- የያዝነው መስመር አያዋጣም:እስከመቼስ እንዲህ ይቀጥላል?" የሚሉ አመራሮች ተነስተዋል::
- ካድሬዎች ሕዝቡን እየዞሩ በመቀስቀስ ዳግም እንዲያደራጁ እየተደረገ ነው::
መምጣት ጋር በተያያዘ የወያኔው ጁንታ በህዝብ እና በተቃዋሚ ሃይሎች ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ ተከትሎ በወያኔ/ኢሕአዴግ ፓርቲ ውስጥ በአመራሮች ደረጃ የውስጥ መተራመሱ መቀጠሉ ታውቋል::ሕዝቡን ማዋከብ እና ተቃዋሚውን ማሰር እንዲሁም በየጊዜው የሚከሰተው የውጪ ሃይሎች ጫና አደጋ ውስጥ ይከተናል ልንጠነቀቅ ይገባል የያዝነው መስመር አያዋጣም በሚሉ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ ውዝግብ መከሰቱን ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::

Thursday, December 11, 2014

የቅሊንጦ አንበሶች (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

http://www.goolgule.com/lions-of-kilintto/

ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ቅሊንጦ የሚባል ጫካ አለ እዚያ ጫካ ውስጥ በርካታ ጥቁር አንበሶች አሉ፡፡ ለጥቂት ቀናት እዚያ ጫካ ውስጥ ከትቸ ነበር፡፡ በገባሁ በዐሥረኛ ቀኔ ትቻቸው ወጣሁ፡፡ እዚያ በነበርኩበት ወቅት ካገኘኋቸው አናብስት የሁለቱን ታሪክ ብቻ በአጭር በጭሩ ላጫውታቹህ፡፡

አንደኛው አበበ ካሴ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ጎንደር ነው፡፡ አምና 2006ዓ.ም. ጥር 12 ቀን ነበር የተያዘው፡፡ ወደዚህ ጫካ ከመምጣቱ በፊት በተለያዩ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የማሰቃያ ቦታዎች ሰቆቃ ሲፈጸምበት ቆይቶ በመጨረሻ ነው እዚህ ጫካ ውስጥ የታሰረው፡፡ አበበ ካሴ የግንቦት 7 ቆራጥ ታጋይ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ከ1981-1993ዓ.ም. ድረስ የቀድሞው ኢሕዴን የአሁኑ ብአዴን ታጋይ ሆኖ ለ12 ዓመታት አገልግሏል፡፡ ከዚያ በኋላ እሱና ጓዶቹ ታግለው ለዚህ ያበቋቸው መሪዎቹ ከዚህ በስተቀር የማይባል ሁለንተናዊ ድጋፍ እየሰጠ ባበቃቸው ሕዝብ ላይ የሚፈጽሙት ገደብ የለሽ ግፍና በደል አንጀቱን ሲቆርጥበት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ የፍትሕ ጥያቄ የመመለስ ብቃቱ ወኔው ፍላጎቱ ጽናቱ እንደሌላቸው ባረጋገጠ ጊዜ ጥሏቸው በረሀ ገባ፡፡ በረሀ ሆኖ ለሦስት ዓመታት ያህል በግሉ ሲንቀሳቀስ ቆይቶ በኋላ እንደሱ የከፋቸው ቢጤዎቹህ ተቀላቀለ ከዚያም ወደ ግንቦት 7 ተቀላቅሎ ድርጅቱ ላዘዘው ተልእኮ አምና ጎንደር ላይ እስከተያዘበት ቀን ድረስ ለ9 ዓመታት ያህል ነፍጥ አንሥተው ከሚታገሉ ወገኖች ጋራ ሲታገል ቆይቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ገመና (ተመስገን ደሳለኝ)

ተመስገን ደሳለኝ  (ከዝዋይ እስር ቤት)ነዋሪ “ጄል-አዳብ” (የገሃነም እስር ቤት) እያለ በሚጠራው ማጎሪያ ውስጥ እጅግ በጣም የከፋ ምድራዊ መከራ እንደተቀበለሀዘን በተጫነው ድምፅ ይናገራል፡፡ በሠውነቱ የተለያዩ ክፍሎች ላይ እንደ ፍም ቀልተው የሚታዩት ጠባሳዎቹም ያሳለፈውንሥቃይ አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ፡፡ ለአራት ወራት ያህል አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻው ተቆልፎበት፤ ሃያ አራት ሠዓታትሙሉ እጆቹ በካቴና ተቀፍድደው፣በቀን ከአምስት ጊዜ በላይ ለምርመራ እየተጠራ ያለዕረፍት ከባድ ስቅየት (ቶርቸር)ሲፈፀምበት ቆይቷል:፡ በመጨረሻም ለአንዲትም ቀን የፍርድ ቤት ደጅ ሳይረግጥ፣ ለኦብነግ አባላት አንድ ፓኬት ሲጋራሲያቀብል እጀ-ከፈንጅ ተይዟል በሚል ክስ የጅጅጋ ዞን ፍርድ ቤት በሞት እንዲቀጣ መወሰኑን እዛው እስር ቤት ሆኖከኢትዮጵያ ሬዲዮ የዜና እወጃ  እና ከቪኦኤ ሶማሊኛ ፕሮግራም ሠምቷል፡፡ከፍርዱ በኋላም በተመሳሳይ ወንጀል ከተከሰሰ አንድ እስረኛ ጋር በካቴና ተጠፍሮ በቀን አንድ እንጀራ ለሁለት ተካፍሎእንዲበላ እንደ ውሻ እየተወረወረለት 60 ቀናትን አሳልፏል፡

ደህንነቶች እስረኞችን ነጣጥለው እያዋከቡ ነው

የገዥው ፓርቲ ደህንነቶች የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) የሚገኙትን የተወሰኑ እስረኞች ‹‹አብራችሁን ካልሰራችሁ አንለቃችሁም!›› እያሉ እያዋከቡ ነው፡፡ ሶስተኛ ታስረው ከሚገኙት መካከል ሳሙኤል አበበ፣ ምኞት መኮንን፣ ሜሮን አለማየሁና መርከቡ ሀይሌ ውጭ ሌሎቹ የመታወቂያ ዋስ አምጥተው እንዲለቀቁ የተጠየቁ ሲሆን አራቱን እስረኞች ‹‹አንራችሁን ካልሰራችሁ አንለቃችሁም!›› እያሉ እያዋከቧቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ ፖፖላሬ እስር ቤት ከሚገኙት መካከል ዮናስ ከድርንና ተስፋዬ መርኔን ደህንነቶች ‹‹የእናንተን ምርመራ አልጨረስንም፡፡ ትቆያላችሁ!›› እንዳሏቸው ተገልጾአል፡፡


የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ምሁራን ወያኔን እና ህጉን አብጠለጠሉት:

ሚዲያው በመንግሥት ሥር መውደቁ ለሰብአዊ መብቶች አለመከበር ምክንያት ሆኗል::

ዛሬ የሰብአዊ መብቶች ቀን ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው የሰብአዊ መብቶች ጥናት ክፍልም ቀኑን አስመልክቶ አንጋፋ የዩኒቨርሲቲውን ምሁራን ጋብዞ ውይይት በማድረገት ላይ ይገኛል፡፡ እስካኹን ከሥነሰብ (አንትሮፖሎጂ)፣ ከጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት፣ ከፖለቲካል ሳይንስና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ክፍል እንዲኹም ከሕግና አስተዳደር ኮሌጅ የተውጣጡ ምሁራን ወረቀቶችን አቅርበዋል፡፡

ከጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን ትምህርት ቤት የመጡት ምሁር ሚዲያው በመንግሥት ፍጹም ቁጥጥር ሥር መውደቁ ለሰብአዊ መብቶች አለመከበር ምክንያትና ምልክት እንደኾነ አመልክተዋል፤ ከሕግና አስተዳደር ኮሌጅ የመጡት ምሁር በበኩላቸው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣንን ሠራተኞች የሚመለከተውን ዋስትና ከልካይ ሕግ፣ የፀረ ሽብር ሕጉን፣ የሲቪክ ማኅበራትን ዐዋጅ ሰብአዊ መብትና ሕግ የተጣሉባቸው መኾናቸውን አሥምረውበታል፡፡

ከፖለቲካል ሳይንስ ክፍል የተገኙት ምሁር ዓለም ዐቀፉ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ የሚመለከተው ግለሰቦችን ቢኾንም መብቶቹን እንዲጠብቁ አደራ የሰጠው ግን ለመንግሥታት መኾኑ በራሱ ድክመት እንደኾነ አመልክተዋል፡፡ የእኔ መብት አደራ መሰጠት ያለበት ለእኔ እንጂ ለማንም አይደለም፡፡ በልማታዊ ዐይን ካየነው ስብሰባው ሊበራሊዝምንና ሊበራል አስተሳሰቦችን የሚያስፋፋ ነው፡፡


Wednesday, December 10, 2014

‹‹አብረውን የታሰሩት ካልተፈቱ በስተቀር ብቻችን አንወጣም፡፡››

ሰበር ዜና
ፖሊስ እስረኞቹን ነጥሎ ለማጥቃት እየጣረ ነው
‹‹አብረውን የታሰሩት ካልተፈቱ ብቻችን አንወጣም፡፡›› ሴት እስረኞች
ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ታፍሰው የታሰሩትን አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችን ነጣጥሎ ለማጥቃት ጥረት እያደረገ መሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በሰልፉ ወቅት ከታሰሩት መካከል በዛሬው ዕለት አብዛኛዎቹ ሴት ታሳሪዎችና የተወሰኑ ወንዶች ብቻ የመታወቂያ ዋስ አምጥተው እንዲወጡ የተነገራቸው ቢሆንም ታሳሪዎቹ ‹‹አብረውን የታሰሩት ካልተፈቱ በስተቀር ብቻችን አንወጣም፡፡›› እንዳሉ ተሰምቷል፡፡
በጉዳዩ ያነጋገርናቸው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ‹‹ፖሊስ በተመሳሳይ ወንጀል ያዝኳቸው ያላቸውን ሰላማዊ ታጋዮች አንዱን በመታወቂያ ዋስ ውጣ ብሎ ሌላውን አስሮ በማቆየት ልዩነት የፈጠረው በዚህ አጋጣሚ ያሰጉኛል የሚላቸውን አመራሮችና ግለሰቦች ለማጥቃት ቀዳዳ እየፈለገ እንደሆነ ያሳያል›› ሲሉ ገልጾልናል፡፡
ለአዳሩ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ እያሉ በተመሳሳይ ጉዳይ ታስረው ከነበሩትን የሰማያዊ ፓርቲ አ

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ውሳኔዎችን አስተላለፈ

• ‹‹አገዛዙ የወሰደውና ወደፊት የሚወስደው ከእስካሁኑ የባሰ አረመኔነት እርምጃ ይበልጡን ያጠናክረናል››

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ትናንት ህዳር 30/2007 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ትግሉን ያጠናክራሉ ያላቸውን ውሳኔዎችን አስተላለፈ፡፡ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ‹‹ህወሓት/ኢህአዴግ በፈፀመው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እና እስር ምክንያት ክፍተት ሳይፈጠር የፓርቲው እንቅስቃሴ እንዲቀጥልና ትግሉም እንዲጠናከር የሚያስችሉ ናቸው›› ሲሉ የብሄራዊ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ሰይድ ኢብራሊም ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ብሄራዊ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ህወሓት/ኢህአዴግ በአመራሩ፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ላይ የፈጸመው ጭካኔ ለሰላማዊ ታጋዮች ባለው ጥልቅ ጥላቻና ጭካኔ በተሞላበት እርምጃው ከትግሉ ያፈገፍጋሉ ከሚል ስሌት እንደሆነ በመግለጽ ‹‹አገዛዙ የወሰደውና ወደፊትም ሊወስደው የሚችለው ከእስካሁኑ የባሰም አረመኔነት የተሞላበት እርምጃ ይበልጡን ያጠናክረናል እንጅ ከትግላችን ቅንጣት ያህል ወደኋላ እንደማናፈገፍግ›› ብሏል፡፡

ህዝብን በማይሽር ቁስል አየጎዱ በፕሮፓጋንዳ ማከም አይቻልም:

Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ).
ወቅሰን ወቅሰን ወንጅለን ወንጅለን የሰለቸን ለመስማትም የታከተን ነገር ቢኖር ያለፉት ስርአቶች ላይ እና ሌላው ላይ ማሳበብን አንዱን ከአንዱ ለማፋጀት ማፈራረጅን መጠቋቆምን የመሳሰሉት ኢሕአዴጋዊ ባህርያት ናቸው::ወያኔ ኢሕኣዴግ የጭንቅ ነገር ውስጥ ሲገባ አጣብቂኙ መላወሻ ሲያሳጣው ያቆሰለውን የረገጠውን ህዝብ በማደናበሪያ ፕሮፓጋንዳ መሸንገል እና ማከም መልሶም መዋጥ አንደኛው አምባገነን ባህርይው ነው::ከዚህ በፊት እንደገለጽኩት ታሪክ ይቅር የማይለው ከባድ መንግስታዊ ወንጀል በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ተፈጽሟል::http://minilik-salsawi.blogspot.com/2014/…/blog-post_23.html በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ የደረሰው ግርፍት እና መከራ ቁስሉ የኔም ነው።

አሳዛኙ ብሔራዊ ውርደታችን፣ኢትዮጵያ መንግስት አላት ወይ? የአሜሪካ አምባሳደር ለኢትዮጵያ መንግስት በቀይ ባህር ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሃዘን መግለጫ ላኩ።ኢህአዲግ/ወያኔ እስካሁን አንዳች አልተነፈሰም።Statement by Patricia Haslach, U.S. Ambassador to Ethiopia

በያዝነው ሳምንት መጀመርያ ላይ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች በየመን የባህር ዳርቻ፣ በቀይ ባህር ውስጥ ከሰባ በላይ  የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መስመጣቸው መሰማቱ ይታወቃል።ጉዳዩ በሀገር ቤት እና  በመላው ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ሃዘን አስከትሏል።

Tuesday, December 9, 2014

21 bodies recovered after 70 Ethiopian migrants drowned off Yemen coast: UN

SANAA (AFP) – The UN refugee agency said Monday 21 bodies have been recovered after Yemen reported dozens of Ethiopian migrants drowning when their boat sank near the entrance to the Red Sea.

The interior ministry in Sanaa said in a statement posted on its website Sunday that 70 migrants had died when their vessel capsized in bad weather off the port of Al-Makha, near Bab el-Mandab strait.

ቦርድ የወጡ አንዳንድ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሶማሊያ እንዲዘምቱ ጥሪ ቀረበላቸው

ኀዳር ፳፱)  ፳፻፯ ዓ ኢሳት ዜና :-ከዚህ ቀደም ሶማሊያ ውስጥ ዘምተው የነበሩና መከላከያን የአገልግሎት ዘመናቸውን በመጨረስ ወይም በጉዳት የለቀቁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ መከላከያ ተመልሰው እንዲዘምቱ በደብዳቤ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ጥሪው የደረሳቸው ወታደሮች ጥሪውን ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑም።

ጥሪ የተደረገላቸው የሰራዊት አባላት “የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰላም አስከባሪ ሃይል በሚል ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ በዶላር ቢልክም እግረኛው ሰራዊት የሚከፈለው ገንዘብ እጅግ አነስተኛ በመሆኑ፣ የክፍያ መጠኑ እስካልተሻሻለ ድረስ አንዘምትም” ብለዋል።

ወታደራዊ አዛዦች ከፍተኛ ገንዘብ ሲከፈላቸው ሌላው ወታደር ቤተሰቡን ለማኖር በማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ወታደሮች በመጥቀስ ጥሪ ላቀረበላቸው አካል መልስ መስጠታቸው ታውቋል።


ከብሔረሰብ በዓል ወደ ለታላቁ ሩጫ! – በእውቀቱ ስዩም

ከአምስት ዓመት በፊት ይመስለኛል፣ በደቡብ የሚገኝ የግብርና ዩንቨርሲቲ የብሔር ብሔረሰቦቸን ቀን ምክንያት በማደረግ የክብር አንግዳ አድርጎ ጠራኝ። ትንሽ ካቅማማሁ በኋላ ማየት አይከፋም ብየ ሚኒባስ ተሣፈርሁ። ካምፓስ እንደ ደረስሁ የምግብ ትርኢት ወደ ሚካሄድበት ትልቅ አዳራሽ መሩኝ። ባዳራሹ ትልቅ የግብር ማብያ ጠረጴዛላይ ብሔሮችን የሚወክሉ መብሎችና መጠጦች ተደርድረዋል። ሁሉንም ብሔር ላለማስከፋት ሰማንያ ጉርሻ መጉረስ ይጠበቅብኝ ይሆን በማለት በልቤ እያጉረመረምሁ ለቅምሻ ተሰናዳሁ። ሥጋና ወተት የሁሉም የኢትዮጵያ ብሔሮች ተወዳጅ ምግቦች መሆናቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አስተዋልሁ። ያም ሆኖ፣ ተማሪ ሁላ የራሱን ብሔር ምግብ ልዩ ግኝት አድርጎ ሊያሳይ ይጥራል። አንዱ በተለጎመ ቅል ያቀረበውን ወተት፣ሌላው በሸክላ ጥዋ ያቀርበዋል። አልተሸወድሁም። ወተቱም የላሚቱ ፣ ቅሉም የተፈጥሮ ግኝት እንደሆነ አውቃለሁ።

ግንቦት 7 – በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እናወግዛለን!!!

በአብዛኛው በወጣት ወንዶችና ሴቶች የተገነባው ሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነበት የዘጠኝ ፓርቲዎች ኅበረት፣ “ነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ” የተሰኘ የአንድ ወር መርሀ ግብር አውጥቶ፤ ችግሮችን ተጋፍጦ አብዛኛውን ተግባራዊ አድርጓል። የመርሀ ግብሩ አቢይ አካል የነበረውና በህዳር 27 እና 28 ሊከናወን ታድቆ የነበረው የ24 ሰዓት የአደባባይ ተቃውሞ ግን በአገዛዙ የኃይል እርምጃ ምክንያት በታቀደው መንገድ ሊከናውን አልቻለም። የህወሓት ቅልብ የሆኑት ሲቪል የለበሱ ሰላዮችና የፌደራል ፓሊስ በተቃውሞው ተሳታፊዎች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ጥቃት ፈጽመዋል።

መድረክ፣ የጠራው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና አገኘ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጥላሁን እንደሻው ለፍኖተ- ነጻነት ገለጹ፡፡
ሰልፉ ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ከቀኑ 7፡00 የሚዘልቅ ሲሆን፤ መነሻውን ግንፍሌ ድልድይ አድርጎ መዳረሻውን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ታቦት ማደርያ ያደርጋል፡፡ በሰልፉ ከሚነሱት ዋና ዋና አጀንዳዎችም መካከል በ2007 ዓ.ም የብሄራዊ ምርጫ ጉዳይን በተመለከተ ኢህአዴግ የያዘውን ግትር አቋም አለዝቦ፣ ለድርድር ዝግጁ እንዲሆን መጠየቅ፤ የ2007 ብሄራዊ ምርጫ ፍትሃዊ እና ዲሞክራሲያዊ ይሆን ዘንድ በገለልተኛ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች እንዲፈፀም፣ ምርጫ ቦርድ ከገዢው ፓርቲ ተላላኪነት ነፃ እንዲሆን፤ ኢህኣዴግ በምርጫ ዋዜማ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን ማሳደድና ማሰር እንዲሁም ምርጫውም ማወኩን እንዲያቆም፣ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ. ኢህአዴግ ነፃ ፕሬስን ማፈንና ጋዜጦኞችንና ጦማርያንን ማሳደድና ማሰር እንዲያቆም፣ ኢህኣዴግ ላፀደቀው ህገ-መንግስት ተገዢ እንዲሆንና እንዲያከብረው እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ የትራንስፖርት እና የውሃ እጥረት እንዲፈታና የከተማው የቴሌኮሚኒኬሽን እና የመብራት መቆራረጥን የመሳሰሉ ጥያቄዎች እንደሚነሱ መድረክ አስታውቋል፡፡

መላው የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ፤ ፍትህና ነፃነት የጠማቸው ኢትዮጵያውያን፤ በኑሮ ውድነት ተማረው ከሰው በታች የሚኖሩ ዜጎች፤ በመብራትና በውሃ መቆራረጥ የተሰቃየው ነጋዴ፤ በአጠቃላይም መላው የከተማው ነዋሪ ለዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ስኬት እንዲረባረብ መድረክ ለፍኖተ ነፃነት በላከው መልዕክት ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉ በአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና እንዳገኘም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Monday, December 8, 2014

ብሄራዊ ብድር የዕድገታችን ምንጭ እንጂ የደኅንነታችን ስጋት ሊሆን አይገባም

እኛ ሰዎች ሁሌም ከምንፈራዉና ከምንጠላዉ አንዴ ከገባንበት ደግሞ የቱንም ያክል ብንጠላዉና ብንፈራዉ እየደጋገምን የምንዘፈቅበትና በቀላሉ የማንወጣዉ አዘቅት ቢኖር ብድር ወይም የብድር ልጅ የሆነዉ ዕዳ ነዉ። ብድር ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ የንግድ ድርጅቶች፤ ማዘጋጃ ቤቶች፤ ትላልቅ ኮርፓሬሺኖችና አገሮች በአጭርና በሪጂም ግዜ የሚያጋጥማቸዉን የገንዘብ እጥረት የሚሸፍኑበት መንገድ ነዉ። ወይም ቀለል ባለ አማርኛ ብድር ወደፊት በምናገኘዉ ገቢ ዛሬን መኖር ማለት ነዉ። ብድር ግለሰቦች፤ ድርጅቶች ወይም አገሮች የመከፈል አቅማቸዉን እያዩ ቢበደሩና የተበደሩትን ገንዝብ ዉጤታማ በሆነ መንገድ ከተጠቀሙበት የእድገትና የብልጽግና መንገድ የሚከፍት አለዚያም የምንበደረዉ ብድር ከአቅም በላይ ከሆነና ዉጤታማ ባልሆነ መልኩ ከተጠቀምንበት ደግሞ በቀላሉ የማንወጣዉ መቀመቅ ዉስጥ ይዞን የሚገባና ጫናዉ ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚተላለፍ ዕዳ ነዉ።

እነ ፍቅረማሪያም የሽንት ቤትና ሌሎች ቆሻሻዎች የሚፈስበት ጋራዥ ውስጥ ታስረዋል

በሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት ወቅት ታፍና ቤላ 18 ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ታስራ የምትገኘው ወይንሸት ንጉሴና ሌሎች 6 ወጣቶች ሾላ አካባቢ በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርበው 7 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ወይንሸት ‹‹ባልፈተቀደ ሰላማዊ ሰልፍ በመሳተፍና ሁከት መፍጠር›› የሚል ክስ የቀረበባት ሲሆን እሷ በበኩሏ ሰልፍ ማሳወቅ እንጅ ማስፈቀድ እንደማያስፈልግ በመጥቀስ የዋስትና መብቷ ተረጋግጦላት እንድትፈታ ጠይቃለች፡፡‹‹የያዝናቸው በቅርብ ቀን ነው፣ ያልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው አሉ፣ መረጃም እናሰባስባለን›› ያለው ፖሊስ 14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ተጠይቆ 7 ቀን ተሰጥቶለታል፡፡በሌላ በኩል ኮተቤ አካባቢ የታሰሩት እነ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ ተስፋሁን አለምነህ፣ ሺፈራው ዋለና ሌሎች 8 ታሳሪዎች የሽንት ቤት ፍሳሽ በሚልፍበት ጋራጅ ቤት ውስጥ መታሰራቸውን ገልጸዋል፡፡ እነ ፍቅረማሪያም የታሰሩት ፖሊስ ከግለሰብ የተከራው ህንጻ ውስጥ ሲሆን የታሰሩበት ጋራዥም ከህንጻዎቹ ላይ የሚገኙት ሽንት ቤቶችና ሌሎች ቆሻሻዎች የሚያልፉበት ነው ተብሏል፡፡ እነ ፍቅረማሪያም ከ2 ቀን በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው ‹‹በሽብርተኝነት›› ክስ 10 ቀን እንደተቀጠረባቸው ይታወቃል፡፡

የህወሃት ምርጫ የህዝብ መከራ!

ህወሃቶች እኛ ከሌለን ይህችን አገር እንበትናታለን፤ ይህችን አገር የምንሰብር እኛ የምንጠግን እኛ እያሉ እንደሚያሟርቱ ሰምተናል። እኛ የቀረፅነው ፖሊስ ከሚቀየር ሞታችንን እንመርጣለን እያሉ ማቅራራታቸውም ከህዝብ የተሰወረ ነገር አይደለም። የህወሃት ፖሊሲ የሚቀየረው በመቃብርችን ላይ ነው የሚል የማይናወፅ አቋማቸው መቼም ቢሆን በሠለጠነ መንገድ በውይይትና በድርድር እንደማይቀየር ደጋግመው አሳይተውናል። ህወሃቶችን በሠለጠነ መንገድ ተደራድሮ እና ሰጥቶ በመቀበል መርህ ለለውጥ አዘጋጃለሁ ማለት ከእባብ የእርግብ እንቁላል እንደመመኘት ያህል ነው። ከእባብ የእርግብን ዘር የሚጠብቅ ማን ነው?እንግዲህ ህወሃቶች ይህን የመሰለ የከረረ አቋም ይዘው ምርጫ ለምን ያደርጋሉ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።

የትብብሩ አመራሮች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰሱ

‹‹ህገ መንግስቱን ማየት አለብኝ›› ዳኛው

በሰላማዊ ሰልፉ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ‹‹ህገ መንግስቱን በኃይል በመናድ›› ወንጀል ተከሰው 14 ቀን ተቀጠረባቸው፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ አቶ አርጫፎ ኤርዳሎ፣ አለሳ መንገሻና ሌሎቹም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሮች፣ አባላትና በሰልፉ ላይ የታፈሱ ዜጎች አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው ለታህሳስ 13/2007 ዓ.ም ተቀጥሮባቸዋል፡፡

ችሎቱ በዝግ የታየ ቢሆንም ሶስተኛ ከሚገኙት ሴት ታሳሪዎች ጠይቀን ማረጋገጥ እንደቻልነው ‹‹ሁከት በመፍጠር ህገ መንግስቱንና ህጋዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ እና መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ በመውጣት›› የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ በበኩላቸው ‹‹እኛ ህጋዊና ሰላማዊ ታጋዮች ነን፡፡ በህጉ መሰረት ሰልፉን እንደምናደርግ አሳውቀናል፡፡ በመሆኑም የዋስ መብታችን ተከብሮ ልንለቀቅ ይገባል›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡ አቃቤ ህግ ‹‹ምርመራዬን አልጨረስኩም፡፡ የምሰበስበው ተጨማሪ መረጃ አለ፡፡ መረጃዎችን ይደብቁብኛል፡፡ ሌሎች ተባባሪዎችም አሉ፡፡

አመራሮቹ ዛሬ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

በሰላማዊ ሰልፉ ታፍሰው የታሰሩት የትብብሩ አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ዛሬ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ይቀርባሉ፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ ኤራጫፎ ኤርዴሎ፣ አለሳ መንገሻን ጨምሮ በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎቹ እንደሚያነክሱ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

በተመሳሳይ ከሰልፉ በፊት ታፍና ቤላ አካባቢ ታስራ የነበረችው ወይንሸት ንጉሴ ሾላ ደርሳለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኮተቤ ፖሊስ መምሪያ ታስረው የሚገኙት 10 ታሳሪዎች ሾላ ምድብ እንዲሁም ጨርቆስ ታስረው የሚገኙት ቄራ ወይንም ሜክሲኮ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡


Sunday, December 7, 2014

በቂሊንጦ ግንቦት 7 ነው ተብሎ የታሰረው ወጣት 10 ጥፍሮቹን ነቅለው እንዳሰቃዩት ተጋለጠ

የግንቦት 7 አባል ነው ተብሎ የታሰረው አበበ ካሴ የተባለ ወጣት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሕወሓት/ኢሕአዴግ ካድሬ ወታደሮች ከፍተኛ የሆነ ግፍ እየተፈጸመበት መሆኑን ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ መረጃ ያደረሱ ወገኖች አስታወቁ።
“ዛሬ ከወደ ቂሊንጦ የደረሰኝ መረጃ እጅግ የሚዘገንና እንቅልፍ የሚነሳ ነው” በሚል መረጃውን ያቀበለን ውስጥ አዋቂ አበበ ካሴ ግንቦት 7 ነው በሚል የታሰረ ሲሆን መቀጣጫ እናደርግሃለን፤ ምስጢር አውጣ እያሉ በሚዘገንን መልኩ የ10 ጣቶቹን ጥፍሮች እንደነቃቀሉት አስታውቋል። እንደ መረጃ ምንጩ ገለጻ ከሆነ ብልቱ ላይ የታሸገ የላስቲክ ውሃ (ሃይላንድ) በማንጠልጠል ሲያሰቃዩት የቆዩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከብልቱ ፈሳሽ መውጣት መጀምሩም ተገልጿል። እንደመረጃ ምንጩ ገለጻ ከሆነ አበበ በብልቱ ላይ በደረሰበት ከፍተኛ ሕመም ህክምና እንዲደረግለት ቢጠይቅም “ሕክምና ማግኘት አይደለም ገና እንግድልሃለን” ብለው ከልክለውታል።

አበበ በአሁኑ ወቅት የእስረኛ መለያ መታወቂያውን መቀማቱን ያጋለጠው የመረጃ ምንጫችን የሚፈጸምበት ግፍ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ መምጣቱን እና እየተፈጸመበት ያለው የጭካኔ ተግባርም በምን ዓይነት ቋንቋ መግለጽ እንሚቻል ከባድ እንደሆነ ገልጾልናል።


ከእስር ቤትየተላከ መልዕክት

ትናንት ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ታፍሰው ከታሰሩት አመራሮች መካከል ጥረት አድርገን ነበር፡፡ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) የታሰሩትን አመራሮችን መጠየቅ አይቻልም በመባሉ ማነጋገር ባንችልም ጨርቆስ ፖፖላሬ የሚገኙትን ሁለት አመራሮች መልዕክት እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

‹‹ከጉዟችን አንዲት ሴንቲሜትር ወደኋላ አንመለስም››

አቶ ግርማ በቀለ የዘጠኙ ፓርቲዎች ፀኃፊ

ኢንጅነር ይልቃል ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ

አመራሮቹ ጨለማ ቤት ታስረዋል

ህዳር 27/2007 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ታፍሰው ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ ጨለማ ቤት መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ከሰማያዊ ጽ/ቤት አካባቢ በጀመረው ሰልፍ ላይ ታፍሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ታስረው የሚገኙት መካከል ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬና ሌሎቹም ለየ ብቻቸው ጨለማ ቤት መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ታሳሪዎቹ ትናንት ህዳር 27/2997 ዓ.ም ምሽት ላይ ከጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) የተዛወሩ ሲሆን ‹‹ምርመራ ላይ ናቸው፡፡›› በሚል እንዳይጠየቁ ተደርገዋል፡፡

በሌላ በኩል ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ የተነሳው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ ከነበሩት መካከል አብዛኛዎቹ እግርና እጃቸውን እንደተሰበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር የታፈሱት አመራሮች በፒክ አፕ መኪና ተጭነው በሚወሰዱበት ወቅት ደህንነቶች ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትን ከመኪናው ላይ ገፍተው ለመጣር ሙከራ አድርገው እንደነበርና አብረው የተጫኑት ታሳሪዎች ይዘው እንዳስቀሯቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡


የታሰርነው ለቆምንለት አላማ ነው

ትናንት ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ታፍሰው ከታሰሩት አመራሮች መካከል ጥረት አድርገን ነበር፡፡ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) የታሰሩትን አመራሮችን መጠየቅ አይቻልም በመባሉ ማነጋገር ባንችልም ጨርቆስ ፖፖላሬ የሚገኙትን ሁለት አመራሮች መልዕክት እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

‹‹ከጉዟችን አንዲት ሴንቲሜትር ወደኋላ አንመለስም››

አቶ ግርማ በቀለ የዘጠኙ ፓርቲዎች ፀኃፊ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር መግለጫ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ባለፈው አንድ ወር ‹‹ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› በሚል መርሃ ግብር ቀርጸን ስንቀሳቀስ ዋናው አላማችን የስርዓቱን አረመኔያዊነት ለህዝብ በማጋለጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በትግሉ እንዲሳተፍ ማድረግ ነው፡፡ እንደጠበቅነው ገና ከጅምሩ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ትግላችንን በጭካኔ ለማስቆም ጥሯል፡፡ ህዳር 7/2007 ዓ.ም የመጀመሪውን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ በጠራንበት ወቅት ስብሰባውን በኃይል በትኗል፡፡

ትብብራችን ከመቸውም ጊዜ በላይ ያሰጋው ህወሓት/ኢህአዴግ በተለይ የህዳር 27/28 2007 ዓ.ም የአደባባይ አዳር ሰልፍን እንዳይካሄድ የትብብሩን አመራሮችና አባላቶቻችን በማዋከብ፣ በመደብደብና በማሰር ተጠምዶ ሰንብቷል፡፡ በተለይ በትናንትናው ዕለት ሰልፍ በወጣንበት ወቅት ስርዓቱ አመራሮችንን፣ አባላቶቻችንን፣ ተሳታፊዎችንን እንዲሁም አልፎ ተርፎ መንገደኛውን ህዝብ በጭካኔ ደብድቧል፡፡ አፍሶ አስሯል፡፡ ሙስሊም እህትና ወንድሞቻችን በየጎዳናው ታፍሰው የአገዛዙ አረመኔያዊ እርምጃ ሰለባዎች ሆነዋል፡፡ በርካቶችም በ እስር ቤቶቹ ታጉረዋል፡፡

አሁንስ ሰዎቹ ጫካ የነበሩም አልመስልህ አለኝ።ጫካ የነበረ እኮ ከአራዊቱም ከእፅዋቱም ሕግ ይማራል

ሕግ ሕግ ሕግ!!! ቅንጣት ታክል ሕግ የማያከብሩ ለማክበርም ፍላጎት የሌላቸው ሰዎች ተሰብስበው መንግስት መሆናቸው እየቆየ ይብሱን የሚያንገበግብ ጉዳይ እየሆነ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግ/ወያኔዎች የዛሬ 20 ዓመት አፀደቅነው ያሉትን ሕግ እየጠቀሰ ሲሞግታቸው እና ሕግ አክብሩ ሲላቸው ዓመታትን አስቆጠረ።በሕግ ስልጣን ባትይዙም በሕግ ስልጣን  ለሕዝብ አስረክቡ ቢባሉም አልሰሙም።ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ ብዙዎች ብዙ ሊመክሩ ሞክረዋል። በ''ዞን 9'' ጦማርያን፣በፖለቲከኞቹ አንዱዓለም አራጌ፣በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ቀደም ብሎም በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ዳኛ ብርቱካን ደሜቅሳ እና ሌሎችም ስማቸውን ያልተጠቀሰው ሁሉ ሕግ የማክበርን 'ሀሁ' ለማስተማር ቢጥሩም ሰሚ አጡ።ሁሉም ስለ የሕግ የበላይነት ተናግረዋል፣ፅፈዋል።ሰሚ የለም።ይብሱኑ ከአመት ዓመት ትዕቢት ቤቷን እየሰራች በልቦናቸው ላይ እንደ ሸረሪት ድር እያደራች የሚናገሩት እሬት እሬት የሚል የሚሰሩት የውድቀታቸውን ጥልቀት የሚያሳይ ሆነ።
ሕግን ከመከራ ሰሞኑን በያዝነው በኅዳር ወር መጨረሻ ''የሕገ መንግስቱ ሰነድ የፀደቀበት'' እያሉ በሚወተውቱን ሰሞን የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 30 ''የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት'' በሚለው ርዕስ ስር ቁጥር 1 ስር ''ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው
ሕግ ካላወቅህ ለምን እንደመለስከውም አትናገርም

አዲስ ዘመን እና የፀጥታው መስርያ ቤት


ጉዳያችን
ህዳር 28/2007 ዓም (ደሴምበር 7/2014)

ኢትዮጵያ ፋናዬን ትመስላለች – ሀገርና ልጆቿ እንዲህ በመከራ ሰጠሙ።

እሜቴ ነፃነት እንደምን ከርመሻል?!

ከአምናው ሸክማሸክምሽ ዘንድሮ ብሶሻል ።

ዕንባነን አቅንተሽ ዘመን ሸኝተሻል ….

እትብትን ገብረሽ መከራ ወሮሻል። …

ያልፋልም ሳይመጣ እንዲህ ጠቋቁረሻል፤

የፋሽስቱ ኑሮ እንዲህ አሳሮሻል

ያገተው ተፈጥሮሽ – ራሄልን ሆኗል።

የሀገሬ ልጆች እንዴት ናችሁልኝ? የዛሬን „የወያኔን የዱላ ቀን“ ሰበር ዜና ከዘሃበሻ እዬተከታተልኩ – እያነበብኩ የጻፍኩት ነው። ይህ ፎቶ ሀገራችን ከነውስጧ ይናገራል። ስለማያልቀው አሳሯ ይመስክራል። እያደር ስለሚጎላው የበቀል ዱላ ያብራራል። ኢትዮጵያ ለእኔ ፋናዬን ትመስላለች። አዛውንቷ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲህ በግራጫ ዘመኗ ክልትምትም ትላለች። ልጇ እንደ ናፈቃት፣ እንደሳሳት፣ ወጥቶ ሳይመለስ ይቀርባታል። በሰው እጅ ወድቆ በመከራ ስንቅነት ይቀጠቀጣል። ለንዳድ ወይ ለባሩድ ገጸ በረከት ይሰጣል። አዎን እናት ኢትዮጵያ ፋናዬን ትመስላለች ….

Saturday, December 6, 2014

አሜሪካ ዜጎቿ ወደ ኢትዬጵያ እንዳይጓዙ አስጠነቀቀች ከፍተኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ መግለጫው በእንግሊዝኛ

The U.S. Embassy informs U.S. citizens that political rallies or demonstrations may occur without significant notice throughout Ethiopia, particularly in the lead up to Ethiopian national elections in May 2015. Such rallies and demonstrations may be organized by any party or group and can occur in any open space throughout the country. In Addis Ababa, applications for permits to conduct rallies are often requested for Meskel Square or Bel Air Field. Please remember that even public rallies or demonstrations intended to be peaceful have the potential to turn confrontational and escalate into violence. You should, therefore, stay alert and avoid areas of demonstrations, and exercise caution if in the vicinity of any large gatherings, protests, or demonstrations.

read more from Embassy of USA


Stavanger/ ኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን :- በ25 000 NOK (ክሮነር) ሰማያዊ ፓርቲን ለመርዳት ወሰኑ

የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ለሰማያዊ ፓርቲ ታሳሪዎች 25 000 ክሮነር ለመርዳት ወሰነ። ይህ ውሳኔ የተወሰነው ዛሬው እለት የ24 ሰዓት የአደባባይ አዳር ለማድረግ በተወሰነበት ቀን በፓርቲው አመራሮች፣ አባላትና በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ የደረሰውን የድብደባና የእስር እንግልት በሞራል ለመርዳት ሲባል መሆኑን የማህበሩ አዲስ አመራር ገልጿል።


በእርግጠኝነት አደባባዩ ጋ እንደርሳለን!

ጌታቸው ሺፈራው
ትናንት ለሰላማዊ ሰልፉ ዝግጅት ሙሉ ሌሊቱን ነው ስንሰራ ያደርነው፡፡ በተለይ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬና ሳሙኤል አበበ ሌሊቱን ሲለቀቁ ቢሮው ይበልጡን ሞቅ ደመቅ ብሎ አመሸ፡፡ ቢሮ ውስጥ የነበሩት ወጣቶች እስከ አፍንጫቸው አውተማቲክ መሳሪያ የታጠቁ የገዥው ፓርቲ ደህንነትና ፖሊሶች ቢሮውን እንደከበቡት ረስተው ስራቸው ላይ ተጠምደዋል፡፡ ደህንነት ይሁን ፖሊስ ከምንም አይቆጥሩትም፡፡ አቤል፣ ብርሃኑ፣ ወይንሸት፣ እያስፔድ፣ ምኞት፣ በላይ፣ ሜሮን፣ ኃይለማሪያም፣ ሳሙኤል፣ እየሩስ፣ ወሮታው፣ ይልቃል...... ፖሊስ፣ ደህንነት፣ መሳሪያ ቅብጥርጥስ ብሎ የማያስፈራቸው ፍጥረቶች ናቸው፡፡

Friday, December 5, 2014

በጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው ክስ ተሰማ

  በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው የክስ ዝርዝር ከትላንት በስቲያ በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡

ዛሬ ህዳር 24/2007 ጠዋት በዋለው ችሎት፣ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ የቀረበው የክስ ዝርዝር በንባብ የተሰማ ሲሆን በክስ ወረቀቱ ላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መካከል ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦችን አካትቶ እንዲሰጥ ለአቃቤ ህግ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ስለሆነም ሙሉ የክስ ወረቀቱ አርብ ለጠበቆቹ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡

በጠበቆቹ በኩል ክሱ ቀደም ብሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሻሻሉን ለማረጋገጥ ያለፈው የፍርድ ቤቱ ብይን ግልባጭ እስካሁን እንዳልደረሳቸው በመግለጽ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የብይኑ ግልባጭ ሳይደርሰን ተሻሻለ የተባለው ክስ መሰማት የለበትም ብለው የነበር ቢሆንም፣ ክሱን አይታችሁ መቃወሚያ ካላችሁ አስተያየት እንድትሰጡበት እድል እንሰጣለን ያለው ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲሰማ አድርጓል፡፡

ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ ያላቸውን አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ለታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡ (በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር)


አንዱዓለምና እስክንድር ሰው ናፍቀዋል የሰው ያለህ እያሉ ነው!!!! ዛሬ

አንዱዓለም አራጌን ለማየት ቃሊቲ ጎራ ብዬ ነበር ፡፡ ቃሊት ሁለት ሰው ማየት ስለማይቻል ከአንዱዓም ጋር የተሳረውን እስክንድርን ማግኘት አልቻልኩም፡፡ አንዱዓለም እና እስክንድርን መጠየቅ የሚቻልበት ሰዓት እጅግ አጭር ከመሆኑ የተነሳ ጠያቂዎቻቸው ተሰፋ እየቆረጡ እነርሱም ሰው እየናፈቃቸው እንደሆነ ሲነግረኝ ልቤ ስብር ብላለች፡፡ ገና ከአሁኑ ጠያቂዎች ወደኋላ ማለት ከጀምርን እነዚህ ልጆች እየከፈሉ ያለውን መሰዋዕትነት ችላ ማለት ብቻ ሳይሆን ሸክሙን ሁሉ ለቤተሰቦች ጥለን ትግል ላይ ነው ያለነው ማለት አይቻልም፡፡
የህሊና እስረኞች ጉዳይ ያገባናል የሚል ሁሉ ጀግኖቻችንን መጎብኝትና ማበረታት የግድ ይላል፡፡ በቅርብ ያሉት በዚህን ያህል የሰው ናፍቆት ካደረባች እሩቅ የሚገኙት እነ ናትናኤልና ሰይፈ ሚካኤል በምን ደረጃ እንደሚገኙ
መገመት አያሰቸግርም፡፡ ከወሬ ወጥተን አለን ብንል ምን ይመስላችኋል ጎበዝ …. ዘወትር ከአምስት እሰከ ስድስት ሰዓት የመጠየቂያ ሰዓት መሆኑን ማስተወስ ተገቢ መሰለኝ፡፡
በዚሁ አጋጣሚ እነ ሀጎስ ያለምንም ማጉላላት ከአንዱዓለም ጋር ተገናኝቼ ለ45 ደቂቃ እንድናወጋ በማድረጋቸው ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ እስረኛ መጠየቅ ህገ መንግስታዊ መብት መሆኑን ዘንግቼው ሳይሆን ስታንገላቱኝ መውቀስ ብቻ እንዳይሆን ብዬ ነው፡፡


የወያኔ ምርጫ – ጭንጫ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 05.12.2014 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

እንደላበዛባችሁ እዬሰጋሁ ግን የገጠመኝን መልካም ነገር ቀድሜ ላወጋችሁ ወደድኩኝ። እባክቻሁ ውዶቼ ፍቀዱልኝ? መቼም ዘንድሮ አውጊ አደራ ሁኛለሁ። …. የማንነት ጽጌረዳ ነውና አትቆርጡም ብዬም አስባለሁ።

እንደ – በር። አልኳችሁ ትንሽዬ ቀጠሮ ኖራኝ ወደ አንድ የማላውቀው ሰፈር ተጓዝኩኝ – ዕለተ – እሮብ። የምሄድበት ቦታ አዲስ ስለነበረም ከቀጠሮዬ ሰዓት በፊት ሁለት ሰዓት ቀድሜ ነበር የደረስኩት። ከዚህ በኋላ ትንሽ ሻይም ቡናም ከተገኘ ብዬላችሁ ላይ ብል ታች ብል ፈጽሞ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአድባሩ የለም። እንዲህ ደግሞ ገጥሞኝ አያውቅም። ወደ ላይ ሲኬድ ቀጥ ያለ አስፓልት ወደ ታች ሲወረድም ቀጥ ያለ አስፓልት።

በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ውስጥ የሚገኘው መንግስት ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲል ከፍተኛ ብድር ይፈልጋል ተባለ

ኢሳት ዜና :-ፋይናንሻል ታይምስ የተባለው አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ከአለማቀፍ የግል ባንኮች ለመበደር የወሰነው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለግል አበዳሪ ተቋማት ባላሃብቶች የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አስተያየቶችን እየሰጡ ነው።

ፋይናንሻል ታይምስ 1 ቢሊዮን ዶላር ለመበደር ጫፍ ላይ የደረሰው መንግስት ለውጭ ባለሀብቶች የሰጠውን ማስጠንቀቂያ ያልተለመደ ወይም እስከዛሬ ያልታየ ነው ብሎታል።

አገሪቱ በኢኮኖሚ እየገሰገሰች መሆኑዋን፣ በምግብ ራሱዋን መቻሉዋን፣ ሰላምና መረጋጋቱ አስተማማኝ ደረጃ ላይ መድረሱን በአጠቃላይ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ እየሆነ መሆኑን በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን የሚገልጸው መንግስት፣ ሚስጢራዊ በሆነ መልኩ ለባላሀብቶች ያቀረበው እና የፋይናንሻል ታይምሱ ዣቪር ብላስ የተመለከተው 108 ገጽ ሪፖርት ፣ እስከዛሬ በመንግስት የሚባለውን ሁሉ የሚያፈርስ ነው። ሙሉውን ሪፖርት ለመመልከት ኢሳት ባይችልም፣ የሪፖርቱ ቅጅ ፋይናንሻል ታይምስ እጅ እንደሚገኝ ጋዜጠኛ ዣቪል ለኢሳት በኢሜል በላከው መልእክት አረጋግጧል።

Thursday, December 4, 2014

የተዘጋውን የአረብ ሀገራት የኮንትራት ሰራተኛ አቅርቦትን ለመክፈት የወጣው ረቂቅ !

 አጠቃላይ* ስለ ሰራተኞች መብት ጥበቃ መነሳቱ አልተዘገበም
* በተወያይ ኤጀንሲዎች በኩል ግን ረቂቁ ውዝግብ አስነስቷል
* ከዚህ ቀደም ያለ በኮንትራት ለተበተኑትስ ዜጎችስ ምን ታስቧል ?አዲሱን መረጃ ያገኘሁት ሃገር ቤት ከሚታተመው ከአድማስ ጋዜጣ ላይ ነው ፣ እንዲህ ይላል ” ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግርና እንግልት ለማስቀረት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየውን አሰራር ለማስጀመርና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ውዝግብ አስነሳ፡፡ ”  … ወረድ ብለን ዝርዝር መረጃውን ስንቃኝ በዋናነት መታየት ያለበት አንኳሩ የሰራተኞች ይዞታና የመብት ጥበቃ ጉዳይ በዘገባው ላይ አልተካተተም። ይህም ይሁን ብለን ዝርዝሩን ስንቃኝ ከዚህ ቀደም በነጻ ያገኙትን ቪዛ በደላላ በየገጠር ከተሞች ሰብስበው እህቶቻችንን ከመላካቸው አስቀድሞ ፈቃድ ሲያወጡ ለመንግስት ያቀረቡት የገንዘብ መያዣ በደል ደርሶባቸው ለሚመለሱ ዜጎች ካሳ ሲከፈል አላየንም አልሰማንም ።

በትግራይ፣ አማራ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎች የተሰጣቸውን የደህንነት ስራ በትክልል አልሰሩም በሚል ተተቹ

ኀዳር ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ባዘጋጀው የ2006 የጸጥታ የደህንነት ግምገማ ላይ የተገኙ የተለያዩ ክልሎች የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች ባቀረቡት ሪፖርት በአዲስ አበባ የሃይማኖት አባቶች የተሰጣቸውን የደህንነት ተልእኮ በፈቃደኝነት አምነው ሲፈጽሙ በትግራይና ፣ በአማራ ክልሎች ግን የሃይማኖት አባቶች ተልእኮዋቸውን በአግባቡ ሳይወጡ ቀርተዋል።
የትግራይ ጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ እንደተናገሩት በክልሉ አብዛኛው ህዝብ የኦሮቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ቢሆንም፣ የሃይማኖት አባቶች ሽማግሌዎች በመሆናቸው የተሰጣቸውን ተልእኮ እንደ ፌደራል የሃይማኖት አባቶች በአግባቡ እንደማይፈጽሙና ከአመራሩ መመሪያ የሚጠብቁ የራስ ተነሳሽነት የሌላቸውና የአቅም ውስንነት ያላቸው ናቸው ብለዋል።
ይህንኑ ሃሳብ የአጠናከሩት የአማራው ክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ደሴ አሰሜ ደግሞ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችን ከክልል እስከወረዳ ለማደራጀት ቢሞከርም ተነሳሽነት በመጥፋቱ የታሰበው ሊሳካ አለመቻሉን ገልጸዋል። በተለያዩ ቦታዎች መስኪዶችን ከአክራሪዎች እጅ እየነጠቁ ለመጅሊሱ ማስረከባቸውንም ሃላፊው ተናግረዋል ። በኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ደግሞ የፌደራል መጅሊስ አመራሮች መከፋፈላቸውን ገልጸው፣ ክፍፍሉ እስከታች በመውረዱ ችግር እየፈጠረ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ መውሰድ ይገባል ብለዋል
በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ለመንግስት የደህንነት ስራ እየሰሩ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወቃል።


ጋዜጠኛ ተመስገን ወደ ቃሊቲ ዞን 3 ተዛወረ

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ጋዜጠኛ ተመገን ደሳለኝን በ”አሸባሪነት” ያሰረው የኢህአዴግ አስተዳደር; አደገኛ ወንጀለኞች ወደሚገኙበት የዞን 3 ቃሊቲ እስር ቤት የተዛወረ መሆኑን ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገለጸ:: እንደታሪኩ ገለጻ ከሆነ “በዞን 3 የሚገኙት እስረኞች በጠቅላላ ማለት ይቻላል በተደጋገመ ስርቆት፣ ማጭበርበርና አስገዳጅ የሌብነት ወንጀል ሲፈፅሙ ተገኝተዋል የተባሉ እስረኞች የሚታጎሩበት ዞን ነው…” ዝርዝር ሁኔታውን የዘገበው ታናሽ ወንድሙ “ዛሬ ደግሞ ተሜን በቃሊቲ…” በሚል ርዕስ ያቀረበውን ጽሁፍ ከዚህ በታች አቅርበነዋል::

ከ5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ?

የትግሬ-ወያኔ ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ23 ዓመታት ደግሞ በገዢነት ተፈናጦ በዐማራ ሕዝብ ባደረሰው የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምን ያህል ንፁሃን ዐማሮች እንደተጨፈጨፉ የተለያዩ አስተያዬቶች ሲደመጡ ቆይተዋል። ሞረሽ ወገኔ ባደረገው ዝርዝር የሕዝብ ብዛት ቆጠራ ትንተና መሠረት ከ1983ዓ.ም. ወዲህ ደብዛቸው ከምድረ-ገፅ እንዲጠፉ የተደረጉት ዐማሮች ብዛት ከ5 ሚሊዮን እንደማያንስ ይጠቁማል። ይህ ምንን ያመለክታል? ከጥናቱ ውጤት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ጎልተው ይወጣሉ።

የእንግሊዝ ኤምባሲ ተወካይ በሰሜን ጎንደር ዞን ከአንድነት የዞን ሰብሳቢ ጋር ተወያዩ

ፍኖተ ነፃነት
የሰሜን ጎንደር ዞን የአንድነት ፓርቲ ህዳር 23 ቀን 2007 ዓ.ም ከእግሊዝ ኤምባሲ ተወካይ ጋር ፓርቲው በአካባቢው በሚያደርገው እንቅስቃሴና በመንግስት እየተወሰደ ባለው ህገ ወጥ እርምጃ ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አቶ አለላቸው አታለል የሰሜን ጎንደር ዞን አንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ ከኤምባሲው ተወካይ ጋር ባደረጉት ውይይት በፓርቲው በዞኑ እያደረገ ስላለው ጠንካራ እንቅስቃሴ ማስረዳታቸው ታውቋል፡፡ ሰብሳቢው አክለው እንዳስረዱት መንግስት አንድነት ፓርቲ በአካባቢው ጠንካራ መዋቅር መዘርጋቱና በህዝብ ከፍተኛ ተቀባይነት ማግኘቱ ስላሰጋው በፓርቲው አመራሮችና አባላት ላይ የሚያደረገው እስር እንግልት፣ አፈና እና እስር የከፋ ነው ብለዋል፡፡

በሰሜን ጎንደር የፖለቲካ እንቅስቃሴ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሌለ፣ በአጠቃላይ በገዢው ፓርቲ ካድሬዎችም ፊት አውራሪነት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን በማሰር ከሽብር ጋር እያገናኙ ህብረተሰቡን በማሸማቀቅ ፓርቲው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመግታት እየሰሩ እንደሆነ በሰፊው ለኤምባሲው ተወካይ ማብራራታቸውን ከዞኑ ለፍኖተ ነፃነት ለፍኖተ ነፃነት የደረሰው መረጃ አመለከተ፡፡


ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አመክሮ ተከለከለች

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ “ሽብርተኛ” ተብላ በእስር ላይ የምትገኝ ሲሆን እንደማንኛውም እስረኛ ልታገኝ የሚገባውን አመክሮ ሳታገኝ ቀርታለች:: በመሰረቱ አመክሮ የሚሰጠው አንድ እስረኛ በ እስር ቤት ቆይታው ወቅት የሚያሳየው መልካም ባህሪ ተገምግሞ ለአንድ እስረኛ ከተፈረደበት አመት ተቀንሶ እንዲወጣ ይደረጋል:: ከቤተሰብ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሆነ ለርዕዮት አለሙ ሊሰጣት የነበረው የአመክሮ ቅፅ “ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” የሚል ነው::Reeyot Alemuጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙን በዚህ ጉዳይ ያነጋገራት ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኤጀንሲ የመጣ ሰው ነበር:: በውይይታቸው ወቅት “ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” የሚለውን አባባል ለመቀበል አልቻለችም:: ምክንያቱም ሃሳቧን በጽሁፍ ስለገለጸች ነው “አሸባሪ” ተብላ የታሰረችው:: ከፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኤጀንሲ የመጣውም ሰው “እንግዲያው አንቺ ከጥፋቴ ታርሜያለሁ” ብለሽ የማትፈርሚ ከሆነ እኛም አመክሮ አንሰጥሽም ብሏታል::ከዚህ በፊትም “አጥፍቻለሁ ይቅርታ ይደረግልኝ” ተብሎ በፕሬዘዳንቱ አማካኝነት የሚደረገውን ሂደት ሳትቀበለው ቀርታ የይቅርታ ደብዳቤ አለማገባቷ ይታወሳል:: አሁን በቅርቡ ማድረግ የሚቻለውን “አመክሮ” ተቀብላ ቢሆን ኖሮ አሁን ከ እስር የምትወጣበት ወቅት እንደነበር ከቤተሰብ አካባቢ ያገኘነው ምንጭ አረጋግጧል::

ለሁሉም እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር

የተለያየ እምነት ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በአገር ላይ የመጣን ችግር በጋራ ሲከላከሉ ዘመናትን አስቆጥረዋል፡፡ የተቀያየሩት መንግስታት ሳይወስኗቸው፣ እምነታቸው ሳይለያያቸው በጋራ ችግሮቻቸውን ሲፈቱ ቆይተዋል፡፡ በእየ እምነቶቻችን ያሉት ጥልቅ ስነ ምግባሮች ጥቃቅን ልዩነቶቻችንን ተሻግረው አብሮ ለመኖራችን ዋነኛ ሚስጥሮች ናቸው፡፡ በዚህ በኩል እምነቶቻችን ኢትዮጵያውያን ለተሳሰርንበት ድር ትልቅ ሚና እንዳላቸው መናገር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ይህን ታሪካዊ መስተጋብር ሲያደርጉ እምነታቸውን በነጻነት ያራምዱ ነበር ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት እምነታቸውን በነጻነት እንዳይከተሉ የተለያዩ በደሎች ደርሰውባቸዋል፡፡ የእምነት ነጻነታቸውን ለማረጋገጥ በተደረገ ትግልም ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል፡፡

አዲስ አበባ በተበተነ ወረቀት ተሸፍና አደረች

        አዲስ አበባ በተበተነ ወረቀት ተሸፍና አደረች። ሚሊዮኖች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በየመንገዱና በየአደባባዩ የተበተኑ ወረቀቶችን እያነበቡ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። የ24 ሰዓቱ የአዳር ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እማኞች እንደሚሉት በተለይ ከጎተራ እስከ ሳር ቤት ባለው መንገድ ላይ የሚቀሳቀስ ሰው በሙሉ የተበተነው ወረቀት መልዕክትና የፊታችን እሁድ የሚደረገው የ24 ሰዓት ሰልፍ ላይ እንደሚገኝ በደስታ እየገለጸ ይገኛል። ባልተለመደ መልኩ አዲስ አበባ ከባድ መሳሪያ በታጠቁ የወያኔ ሰራዊት ተሞልታለች። ወያኔ ራሱ በፍርሃት በፈጠረው ሽብር ተርበትብቷል። ይህ ደግሞ የስርዓቱን ፍርሃት ደረጃና መውደቂያው መቃረቡን ያሳያል።
የውጭ ሃገር የመገናኛ ብዙሃን ያሰማራቸው ፎቶ አንሺዎች ከተማ ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ በድብቅ ከ100-300 ሜትር ርቀት አካባቢ ሆነው በተለይ የአዲስ አበባ ፖሊስንና ታጣቂዎችን በልዩ ካሜራዎች ሲቀርጹ ታይተዋል።

በዝግ ችሎት ታየው የሃና ላላንጎ ጉዳይ

* “አሸባሪዎችን” ለይቶ የመያዝ “ሃና ላላንጎ የተባለችውን ተማሪ በሚኒባስ ታክሲ አፍነው በመውሰድ፣ በቡድን በመድፈርና ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትን አምስት ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ጉዳይ በዝግ ችሎት መታየት ጀመረ፡፡ተጠርጣሪዎቹ ለሦስተኛ ጊዜ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ ቀደም ባለው ቀጠሮ እንደሚሠራቸው ያስመዘገበውን ቀሪ የምርመራ ሒደት፣ ለችሎቱ ያስረዳበትና ተጠርጣሪዎቹን ያቀረበበት ሰዓት፣ ከሌሎች ቀናት የተለየ ነበር፡፡ሟች ሃና ላላንጎ በቡድን ተደፍራ ሕይወቷ ማለፉ በመገናኛ ብዙኃን ከተሰራጨበት ጊዜ አንስቶ እያነጋገረ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በየቀጠሮው ፍርድ ቤት የሚገኘው ታዳሚ ቁጥር ጨምሯል፡፡

Wednesday, December 3, 2014

አሶሳ በከፍተኛ የመከላከያ ጥበቃ ስር መውደቁዋ ተሰማ፡፡


ኀዳር ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-9ነኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል የሚያስተናግደው የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዝግጅት ማጠናቀቁን ቢገልጽም፣ በአካባቢው መንግስትን የሚቃወሙ ኃይሎች በተለያየ ጊዜያት በደፈጣ ውጊያ ጥቃት ማድረሳቸው ያሰጋው መንግስት በአካባቢው ከፍተና ወታደራዊ ሃይል አሰማርቷል።
ህዳር 29 ከሚካሄደውን በዓል ጋር ተያይዞ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል ብዙዎች የሚሰጉ ሲሆን፣ ጥቂት የማይባሉ አመራሮች፣ ባለሃብቶችና ታዋቂ ሰዎች በተለያዪ ሰበቦች የጉዞ እቅዳቸውን የሰረዙ መሆኑ ታውቆአል፡፡
በቤንሻንጉል ክልል የተመሠረተው የአባይ ግድብ ጨምሮ በዋና ከተማዋ አሶሳ ከወትሮው በተለየ መልክ በኮንቮይ የታገዘ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ ሲሆን ለጸጥታ ሲባል እንደልብ መዘዋወር መከልከሉ ተሰምቷል፡፡
የፌዴሬሽን ምክርቤት የዘንድሮው በዓል የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ሕገመንግስቱን ያጸደቁበትን 20ኛ ዓመት ጭምር የሚያከብሩበት ታሪካዊ ዕለት መሆኑን በመጥቀስ በተደጋጋሚ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ይህንን በዓል ለማክበርም ከ2ሺ500 በላይ እንግዶች ወደስፍራው ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቅ እንደነበር ታውቆአል፡፡
ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የተውጣጣ ቡድን ነገ ሐሙስ ወደስፍራው የሚያቀና ሲሆን ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ኮርፖሬሽን (የቀድሞ ኢቲቪ) ብቻ ከ100 በላይ ጋዜጠኞችና ባለሙያዎች አሶሳ መግባታቸው ታውቆአል፡፡
በስተሰሜን ምዕራብ ሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሁኑ ሰዓት የህዝብ ቁጥሩ 964 ሺ 647 ደርሷል፡፡ በክልሉ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ማለትም በርታ ፤ ጉሙዝ ፤ ሽናሻ ፤ ማኦ፣ ኮሞ ኦሮሞና አማራ የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ብሔር ብሔረሰቦች ከዚህ ሥርዓት ቀጥተኛ ተጠቃሚ ካለመሆናቸውም በላይ መሬታቸው ለውጪ ባለሃብቶች ጭምር ያለፈቃዳቸው በገፍ የሚሰጥ በመሆኑ በጅምላ የመፈናቀል አደጋና በሰፈራ ስም ከቀዩአቸው እንዲሰደዱ በመደረጋቸው በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ቅሬታ መኖሩን ዘጋቢያችን ገልጻለች።


• 5 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረዋል

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በተመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ የተባሉት፣ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) አመራሮች፣ አቶ አንዱዓለም አራጌና አቶ ናትናኤል መኰንን፣ እንዲሁም የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ

ፓርቲ (መኢዴፓ) አመራር፣ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደርጐ፣ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀናባቸው፡፡

ሰበር ሰሚ ችሎቱ አቤቱታውን ውድቅ አድርጐ የሥር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ያፀናው፣ በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም. ፍርደኞቹ ያቀረቡትን አቤቱታ ሲመረምር ከርሞ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ነው፡፡

የ24 ሰዓቱ ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ ቀጥሏል •

• 5 የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረዋል
ህዳር 27 እና 28 2007 ዓ.ም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የሚያደርጉት የአዳር (24 ሰዓት) ሰልፍ ቅስቀሳ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃ ላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ እስካሁን ሰው በሰውና ቲሸርት በመልበስ ቅስቀሳ ሲደረግ እንደቆየና በተለይ ዛሬ ህዳር 24/ 2007 ዓ.ም ከሰዓት ጀምሮ በአዲስ ከተማ፣ ጉለሌ፣ አራዳ፣ የካ፣ ንፋስ ስልክ፣ ኮልፌና ሌሎች የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማዎች ወረቀት በመበተን የተሳካ ቅስቀሳ መደረጉን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል አራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ አካባቢ ለአዳር ሰልፉ ሲቀሰቅሱ ከነበሩት መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ሜሮን አለማየሁ፣ ወይንሸት ንጉሴ፣ ባህረን እሸቱ፣ ማቲያስ መኩሪያ እንዲሁም ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ሲቀሰቅስ የነበረው ሲሳይ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ተግልጾአል፡፡
ከአሁን ቀደም ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ ሲያደርጉ በርካታ የፓርቲው አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ያስታወሱት አቶ ዮናታን ‹‹ይህ የገዥው ፓርቲ የተለመደ እርምጃ ነው፡፡ በቀጣይነትም ሌሎች አባላትንና አመራሮች መታሰራቸው አይቀረም፡፡ ትግሉ መስዋዕትነት የሚያስከፍል እንደመሆኑ በእስሩ ሳንገታ ትግሉን እንቀጥላለን፡፡›› ሲሉ እንቅስቃሴያቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ የዛሬው ቅስቀሳ 12 ሰዓት ላይ የተጠናቀቀ ሲሆን ነገ ጠዋት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ግልጽ ደብዳቤ ወይዘሮ ገነት ዘውዴ:- ከፈቃደ ሸዋቀና

የዱሮ ወዳጄ ሰላምታዬ ይድረሽ። እንደምታውቂው ከተያየን ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሆኗል። እኔም ካገሬ ከወጣሁ 21 ዓመት አለፈኝ። በጤናና በምቾት እንደምትኖሪ እሰማለሁ። እግዚአብሄርም መንግስትም ጥሩውን ነገር ሁሉ አብዝቶ እንዲሰጥሽ ምኞቴ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጓደኝነት ከምቀርባቸውና ከማከብራቸው ስዎች ውስጥ አንቺ አንዷ እንደነበርሽ ራስሽምብዙ ሰዎችም ያውቃሉ። ከጊዜ ብዛትና በስልጣንም ርቀት ምክንያት ጓደኝነቴን ብትረሽውም አልፈርድብሽም። እኔ ግን ከሀገሬ ባለስልጣኖች አንዷ በመሆንሽ አልፎ አልፎም ቢሆን ስላንቺ የሚባለውን ከፉም ደግም እሰማለሁ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ስላንቺ ክፉ ሲናግሩ ስሰማ የጓደኝነት ነገር እየሆነብኝ ደስ አይለኝም። ተሳክቶልኝ እንደሆን ባላውቅም ስላንቺ የማውቃቸውን በጎ ነገሮች በማንሳትም ልሟገት የሞከርኩበት ጊዜ ጥቂት አይደለም። ብዙ ሰዎች ያኔ 41 መምህራን ከዩኒቨርሲቲ ስንባረር አንቺን እንዳባራሪ እያዩሽ ለምን እንደማልጠላሽ ይገርማቸዋል። እስከዚህ ደቂቃ ድረስ ዉሳኔው ሲቀርብልሽ አትፈርሚም ብዬ ባልከራከርም አንቺ በኔ መባረር ላይ ትወስኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም። አስተያየት እንድትሰጭ ብትጠየቂም በኔ ላይ ክፉ የምትናገሪም አይመስለኝም። መንግስታችን ላንቺ አይነት ሰዎች ትልቅ ወንበር እንጂ ትልቅ የውሳኔ ሰጭነት ስልጣን አብሮ እንደማይሰጥ እንደ ብዙ ሰው አውቃለሁ። ድሮ ጀምሮ ካንቺ ጋር ውቃቢያችሁ የማይዋደደው ወዳጄ ዶክተር መ

ፓርቲዎች በምርጫ አንሳተፍም ቢሉ…..

ምርጫ አለመሳተፍ መብት ነው !በኢትዮጵያ ያለው ጭላንጭል የፖለቲካ ምኅዳር ሲታይ፣ይህ ውሳኔ የሕግ፣የፖለቲካ እና የሞራል ድጋፍ አለው፡፡ሆኖም ግን በምርጫ ያለመሳተፍ መብት በራሱ-የራሱ የሆነ ተግዳሮቶች አሉትና፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትርፍ-ኪሳራ ሥሌት የግላቸው ነው የሚሆነው፡፡

ይድነቃቸው ከበደ

ይህ ጹሑፍ በምርጫ አለመሳተፍ መብት መሆኑን ከህግ አንፃር ለማየት እንጂ፣ የሚጪው አገረ አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ “ኢሕአዴግ ለመርጫ አልተዘጋጀም !” እና “የ24 ሰዓት ተቃውሞ በአዲስ አበባ !” በሚል ዕርሶች ከዚህ በፌት በፃፍኳቸው ፁሑፍ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫ፣ ገዥው መንግስት ለነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ እራሱን አዘጋጅቶ፣ ውጤታማ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል የግል እምነቴን ገልጫለው፡፡

“ፖለቲካ ውስጥ አትግባ” የምትባል ፖለቲካ!!!!!!!

አዲሱ የእኛ አገር ፖለቲካ ሰውን “ኧረ ፖለቲካ ውስጥ አትግባ” የምትባል ፖለቲካ ናት። እንዲህ ለሚሉ ሰዎች ትክክለኛውን ምላሽ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ቆዝሜያለኹ። አሁን እንኳን በዚህች መሸዋወድ የለም። በነገራችን ላይ፤ ፖለቲካ ውስጥ እንዳትገባ የሚነግሩህ ማንነትህን በሚመጥን መልክ ነው።1. ሃይማኖተኛ ከመሰልካቸው፣ ለዚያ የሚስማማ ጥቅስ እና አባባል አዘጋጅተዋል።2. “ምሁር ነገር” ከመሰልካቸው ምሁርነት ከአገራችን ፖለቲካ በላይ በመሆኑ ራስህን በዚያ ውስጥ እንዳታቆሽሽ ያስጠነቅቁሃል።3. ንግድ ላይ ካለህ በፖለቲካ መነካካት ሊያመጣ የሚችለውን መአት ያመለክቱሃል።4. ዳያስጶራ ብትሆን አገር ቤት ያሉ ዘመዶችህ ላይ ሊመጣ ያለውን ችግር ያመለክቱሃል፤ ራስህም ብትሆን እዚያችን አገር ድርሽ እንደማትል ያስጠነቅቁሃል።
ፖለቲካ በተለይ የፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ እንዳልገባህ ስለምታውቀው “እኔ ፖለቲካ ውስጥ አልገባሁም” ብትላቸው ከቻልክ ዝም ማለት፣ ካልቻልክ መንግሥትን መተባበር እንጂ እንኳን ሌላ ነገር “የመንግሥትን ጭካኔ እንኳን መቃወም” መጥፎ ፖለቲካ መሆኑን ይነግሩሃል።የእነርሱ ደጋፊ ብትሆንስ? እሱ ፖለቲካ ውስጥ መግባት አይደለም። ሃይማኖተኛ ከሆንክ መንግሥትን መደገፍ ማለት “እግዚአብሔር የሾመውን ማክበር” ነው ትባላለህ። ምሁር ከሆንክ “የማንም ደጋፊ ሳትሆን ሚዛናዊ ሰው ነህ ማለት ነው፤ ወይም የአገር ልማት ደጋፊ” ትባላለህ። ነጋዴ ከሆንክ “ልማታዊ ነጋዴ” ትባላለህ። ዳያስጶራ ከሆንክ “የኢትዮጵያን ዕድገት የሚናፍቅ፣ አገራችን እኮ አደገች” ባይ ትባላለህ።ስለዚህ አዲሱ ፖለቲካ “ፓለቲካ ውስጥ አትግባ” ናት

ዞን ዘጠኞች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው እየታየ ያሉት ጦማርያን እና ወዳጅ ጋዜጠኞች ላይ የተመሰረተው ክስ ተሻሽሎ ቀርቧል የተባለው የክስ ዝርዝር ዛሬ በልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ህዳር 24/2007 ጠዋት በዋለው ችሎት፣ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ ተሻሽሎ የቀረበው የክስ ዝርዝር በንባብ የተሰማ ሲሆን በክስ ወረቀቱ ላይ ከተመለከቱት ነጥቦች መካከል ግልጽ ያልሆኑ ነጥቦችን አካትቶ እንዲሰጥ ለአቃቤ ህግ ትዕዛዝ ተሰጥቶታል፡፡ ስለሆነም ሙሉ የክስ ወረቀቱ አርብ ለጠበቆቹ እንደሚደርስ ይጠበቃል፡፡

በጠቦቆቹ በኩል ክሱ ቀደም ብሎ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መሻሻሉን ለማረጋገጥ ያለፈው የፍርድ ቤቱ ብይን ግልባጭ እስካሁን እንዳልደረሳቸው በመግለጽ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲደርሳቸው ጠይቀዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የብይኑ ግልባጭ ሳይደርሰን ተሻሻለ የተባለው ክስ መሰማት የለበትም ብለው የነበር ቢሆንም፣ ክሱን አይታችሁ መቃወሚያ ካላችሁ አስተያየት እንድትሰጡበት እድል እንሰጣለን ያለው ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲሰማ አድርጓል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ ያላቸውን አስተያየት ይዘው እንዲቀርቡ ለታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል፡፡


Tuesday, December 2, 2014

ህጋዊ ተቃዋሚዎችን በአክራሪነት ሰበብ ለመምታት የሚያስችሉ ሃሳቦች ቀረቡ

 ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ካካሄደው ውይይት ለመረዳት ተችሎአል፡፡
የትግራይ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰማያዊ ፣አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ጽንፈኞች በመሆናቸው በአክራሪነት ሲሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን በማሰባሰብ ለሽብር እያዘጋጁ ነው በማለት የገዢውን መንግስት ፖሊሲዎች በሰላማዊ መንገድ የሚቃዎሙትን ፓርቲዎችን በወንጀለኛነት ሲፈርጁ ተደምጠዋል፡፡
መልካም ተሞክሮ ነው በማለት በየክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ኃላፊዎች የቀረበው ሪፖርትና የወደፊት እንቅስቃሴ በመጭው ምርጫ 2007 የተፈረጁት ፓርቲዎች የህዝብ ድምጽ በማግኘት የገዢው መንግስት ስጋት እንዳይሆኑ ከማሰብ የተነሳ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡
በሃገሪቱ በትጋት ከሚንቀሳቀሱና የህዝብ ድጋፍ በብዛት እያገኙ ከመጡት የተቀናቃኝ ፓርቲዎች መካከል የሚመደበው የሰማያዊ ፓርቲን እንቅስቃሴ ለማስቆም እና የምርጫ 2007 ስጋት መሆናቸውን ለማክተም ገዢው መንግስት በየአካባቢው የሚከሰቱ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ከተቀናቃኝ ፓርቲዎች ጋር ማገናኘት መጀመሩ ሆን ተብሎ ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ለመምታት የተዘጋጀ መሆኑን ምንጮች ጠቅሰዋል።

የትግሬ ወያኔዎች በ ሶስት ወይ በ ምንናምን ይከፈላሉ ( ሄኖክ የሺጥላ )

1.  የመጀመሪያዎቹ መጻኢው የ ወያኔ ህውሃት ዕጣ ፈንታ በደንብ የገባቸው እና ሰላም ምናምን በሚል የእርግብ ስዕል  የፈስ ቡክ ገጾቻቸው የተንቆጠቆጠ  ፣ ትንሽ ግዜ ስጡን እንጂ ስልጣን እንለቃለን የሚሉ ፣ በልባቸው ግን መሰሪዎች እና አደገኛ ሰላዮች ናቸው ። ይሄኛው ቡድን የተቃዋሚ  ቤተክርስቲያን ሄደው ይሳለማሉ ፣ የወያኔ ደጋፊ መሆናቸውን በፍጹም አታውቅባቸውም ፣ እንደውም አንዳንዴ ካንተ ጋ አብረው ስርዓቱን ይሰድቡታል ፣ ግን በጣም ተራ በሆኑ ነገሮች ላይ ነው ተቃውሞ-አቸውን የሚያቀርቡት ፣ ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ጥያቄ ስታነሳ ሰላም ይሻላል ፣ እኛ አንድ ሕዝብ ነን ይሉሃል ፣ በጣም ሙልጭልጭ ናቸው ፣ ከተቃዋሚ ጎራ ገብተው የፈለጉትን ነገር የማድረግ ብቃት አላቸው ። የማህበረ -ሰቡ የ’ለት ተለት ኑሮ ውስጥ ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው ፣ ለቅሶ ላይ ከንፈር መጣጮች ናቸው ፣ በችግርህ ጊዜም ይደርሱልሃል ። ባጠቃላይ በደልህ ላይ የተዛባ አመለካከት እንድትይዝ የሚያረጉህ እነዚህ የወያኔ ክንፎች ናቸው ። ስለ ሰላም ሲያወሩ ” አፌ ቁርጥ ይበል !” የምትልላቸው ናቸው ፣ በጣም ዘመናዊ ናቸው ፣ አንተን ማለስለስ ሁነኛ ስራቸው ነው ። እነዚህ ሰዎች ስለ አባይ ቦንድ ጠቀሜታ ሲነግሩህ ላገር በመቆርቆር ስሜት ነው ስለዚህ በፍጹም ልታውቃቸው አትችልም ። ያም ሆኖ ማን ተቃዋሚ ነው ማን አይደለም የሚለውን ሪፖርትም የሚያቀርቡት እነዚህ ናቸው ። ምክንያቱም ካንተ ጋ ነው የሚውሉት ፣ ሃገራዊ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ በጣም የጠለቀ እውቀት አላቸው ( ለምሳሌ የእግር ኩዋስ እና የመሳሰሉት ነገሮች ላይ ማተኮር ይወዳሉ አንተም ወደዚያ

በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ለመንግስት የደህንነት ስራ እንደሚሰሩ ታወቀ!

ኢሳት ዜና :-የፌደራል መንግስቱ የ2006 የጸጥታ አጠባበቅ ግምገማ በሚያደርግበት ስብሰባ ላይ እንደተገለጸው በአዲስ አበባ 7ቱም የሃይማኖት ተቋማት ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ጋር በጋራ በመቀናጀት የደህንነት ስራ እየሰሩ ነው።

አጠቃላይ ውይይቱን በተመለከተ ለኢሳት የደረሰው ሚስጥራዊ የድምጽ መረጃ እንደሚያስረዳው በአዲስ አበባ በተቋቋመው መዋቅር ውስጥ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበት ሲሆን፣ መንግስት መኪና፣ ኮምፒዩተር፣ ጽ/ቤትና ሌሎች ቁሳቁሶች ሰጥቷቸው ከመንግስት ጋር በመሆን ጸጥታን ለመከላከል እየሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው በጉባኤው ላይ ተናግረዋ ህገመንግስቱ መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ መሆናቸውን

” በፀሀዩ መንግስታችሁና ሀይማኖታችሁ መካከል አለመጣጣም ቢከሰት የቱን ትመርጣላችሁ?”

በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀና ” የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሠራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል ለምርጫ 2007 የተሻሻለ ጥቅምት 2007″ የሚለውን 23 ገፅ የያዘ ማንዋል አነበብኩት። ሰነዱን ለላካችሁልኝ የዘወትር ተባባሪዎቼ ምስጋና ይድረሳችሁ።
ማንዋሉን አንብቤ ስጨርስ የተዘበራረቀ ስሜት ተሰምቶኛል ። የግል ስሜቴን ለጊዜው በመተው ማን እንዴት ሊጠቀምበት ይችላል የሚለውን ወደ ማሰብ ተሸጋገርኩ። በቅድሚያ ፊትለፊቴ የመጡት በሐገር ቤት በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱት ሰማያዊና አንድነት ፓርቲዎች ናቸው። ለጀመሩት ትግል ማጠናከሪያ እንዲሆን ተቀናጅተው አንድ ነገር ማድረግ የሚችሉ ይመስለኛል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን አስገራሚ የደሞዝ ጭማሪ አደረገ

ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት 111 በመቶ የደሞዝ ጭማሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ በአማራ እና በኦሮምያ ክልል በተከታታይ ተገቢ የሆነ የደሞዝ ማስተካካያ አላደረገም በሚል ጥያቄ ሲቀርብብት ቆይቷል።

ሰሞኑን የካቢኔ አባላት ተሰብስበው የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ከግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እንዲሁም የኦሮምያ ክልል ጋዜጠኞች ከኦነግ ጋር የሚሰሩትና ለኢሳት መረጃ በማቅረብ በክልሎች መንግስት ላይ ህዝቡ አመኔታ እንዲያጣ የሚያደርጉት በገንዘብ ችግር የተነሳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።

ይህን ተከትሎም የሁለቱንም የክልል መገናኛ ብዙሃን በቦርድ ሰብሳቢነት የሚመራው የመንግስት ኮሚኒኬሺን መስሪያ ቤት ከሌሎች የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች በተለየ ከ80 እስከ 100 ፐርሰንት ጭማሪ እንዲያገኙ ተወስኖላቸዋል፡፡

በዚህ ውሳኔ መሰረት የአንድ አስተባባሪ ደሞዝ እንደ የስራ መደቡ 9 ሺ 810 ብር እንደሚከፈለው ታውቋል፡፡ ጭማሪው ከሌሎች መስሪያ ቤቶች ጋር ሲነፃፀር ከመቶ ፐርስንት በላይ ብልጫ አለው፡፡

ይህንን ጭማሪ ተከትሎ ተጠቃሚ ያልሆኑ ደጋፊ የስራ ሂደት ሰራተኞች ማለትም ሾፌር ፤ ላይብረሪ ፤ፅሃፊዎች ፤ ጥበቃ እና ዝቅተኛ የስራ መደብ ተደርገው የተቆጠሩት የፋይናንስ መደብ ሰራተኞች ተቃውሞ ቢያነሱም፣ “ልቀቁ ሌላ ይቀጠራል” በመባላቸው ቅሬታቸውን ለዘጋቢያችን ገልጸውላታል።

ደጋፊ ሰራተኞች ክስ የመሰረቱ ቢሆንም ይህ ነው የሚባል ውጤት አላገኙም።

ዘጠኙ ፓርቲዎች ለቀጣይና ለቀሩ ስራዎቻቸው ያወጡትን እቅድ በተመለከተ መግለጫ ሰጡ።እንዲሁም የህዳር 27 እና 28 የተቃውሞ ሰልፉን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።

ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው።ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል፡፡“በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ ” ማስገባቱንም ገልጸዋል።የፓርቲዎቹ መግለጫ አያይዞም “ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ በመሆኑ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና  ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28  ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን።” ብሎአል። ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!

በድቡብ ሱዳን አራት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተመቱ

ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንዳለው በዋና ከተማዋ ጁባ አንድ ወንድና አንድ ሴት ሲገደሉ ሁለት ሴቶች ግን በጠና ቆስለው ወደ ኢትዮጵያ ተወስደዋል። የሁለቱም ሟቾች አስከሬንም በኢትዮጵያውያን እርዳታ ወደ ኢትዮጵያ መሄዱ ታውቆል:: ሰዎቹ በምን ሁኔታ እንደተገደሉና እንደቆሰሉ
እንዲሁም ጥቃቱን ያደረሱትን ወገኖች ዝርዝር ለማወቅ አልተቻለም። በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኢትዮጵያውያን የሚደረገውን ግፍና እንግልት ከመከታተል ይልቅ በዶላር ጥቁር ገበያ ምንዛሪ መሰማራቱን የገለጸው ወኪላችን ፣ የቀድሞ የህወሃት ባለስልጣናት በጁባ ከተማ የሚያራምዱትን የቢዝነስ ተቋምና በጋምቤላ በኩል የሚያመጡትን የጤፍና የተለያየ ሸቀጣሽቀጥ ንግድ ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት አብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሚያቀርቡትን አቤቱታ እንደማይሰማ ተናግሯል። ለህወሃት አባሎች ህጋዊ የመኖረያ ፈቃድና የንግድ ፈቃድ ለማስወጣት የጁባ ባለስልጣናትን ደጅ የሚጠናው ኢምባሲው ምርቶችን ወደ ደደቡብ ሱዳን በማስገባት በኩል ወኪል ሆኖ እየሰራ መሆኑን ጠቅሷል።


Monday, December 1, 2014

እናታችን ፋናዬና ተመስገን በዝዋይ…. (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም እንደፃፈው)

ከታሪኩ ደሳለኝ
(የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም)

ያቺ የስምጥ ሽለቆ ከተማ ይበልጥ መንደድ ከጀማመራት አንድ ወር አልፏታል:: በፍትህ መዛባት ስሜቱ የተጎዳ፣ በወገኖቹ ስቃይ መንፈሱ የታመመ፣ ሀገራቸውን ከስቃይ መታደግ በሚችሉበት እድሜያቸው በታሰሩ፣ በተሰደዱና በተገደሉ ወገኖቹ ልቡ ያዘነ፣ ለሀገሩና ለባንዲራው ያለው ፍቅር ጥልቅ የሆነ አንድ ወጣት ጋዜጠኛ በውስጧ ይዛለች፡፡ ዝዋይ፡፡
ከዚህች ከተማ ሦስት ኪሎ ሜትር ገደማ ወደሚርቀው የዝዋይ እስር ቤት ለመሄድ የአስፓልት ዱካ እንዳረፈበት በሚያሳብቀው ኮሮኮንቻማ መንገድ ማለፍ የግድ ይላል፡፡ ከረጅም ዓመታት በፊት ተሰርቶ ዛሬ አስታዋሽ ያጣው ይህ ጎዳና እስረኞችን የመጠየቁን ጉዞ አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ከፀሐዩ ግለት ትይዩ ያለው የመሬቱ አቧራ በእግሩ ቆሞ ይሄዳል ብል አይበዛበበትም፡፡ ይህን አልፈን ግዞት ቤቱን እናገኛለን፡፡ የእስር ቤቱን መግቢያ ያለበሰው አቧራ ደግሞ ቅጥሩን በቁፋሮ የተገኘ ጥንታዊ ከተማ አስመስሎታል፡፡ የግቢው ገፅታ ለዕይታ በማይስቡ ነገሮች ቢከበብም፣ ተናፋቂውን ብዕረኛ ግን ደጋግሜ እንድጠይቀው ከወንድምነት የሚዘለው ጥንካሬው ይስበኛል፡፡

አንገት የሚያስደፋ እውነታ! 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች ውደ ምዕራብ አፍሪካ ሊሄዱ እየተዘጋጁ ነው፡፡

አንድ ወዳጄ ትላንት አመሻሽ አከባቢ ተደዋውለን ሻይ ቡና እያልን በወሬ መኸል ኢቦላ ሕመምተኞችን ለማከም ወደ ምዕራብ አፍሪካ ለመሄድ “እነዳለፈ” ነገረኝ::

በድንጋጤ “ምን ማለትህ ነው ‘አለፍኩ’ ስትል?” አልኩት:

“እንዴ፡ የቀረ ሐኪም እኮ የለም፡፡ እዚሁ ትግራይ ከሚሰሩ ጠቅላላ ሓኪሞች ከግማሽ በላይ ተመዝግበው ነበር፡፡ ጥቂቶች በዋናነት በግልጋሎት ግዜ ብዛት ተመረጥን” አለኝ፡፡

“እንዴት እንዲህ ሰው ሊበዛ ቻለ?”

“እንዴ፡ የወር ክፍያው እኮ እዚህ ኢትዮጵያ በሶስት ዐመት የምታገኘው አይደለም፡፡ 250 ዶላር አበል በቀን፣ ሙሉ የምግብና የመጠልያ ወጪ፤ አበሉን ብቻ ብታሰላው 250 ዶላር በቀን 7500 ዶላር በወር ነው፡፡ ይህ በኛ 150 ሺህ ብር ነው፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ 150 ሺህ ብር ሴቭ ለማድረግ እኮ 5 ዐመትም አይበቃህም፡፡ ለ3 ወር ስለሆነ 450 ሺህ ብር አገኝህ ማለት ነው፡፡ ያ አበል ብቻ ነው፤ ተጨማሪ ሌላ ክፍያም አይጠፋውም፡፡ ምናልባት ይህ ገንዘብ አሁን ባለችው ሀብቷ በባለስልጣናትና ጥቂት ተባባሪዎቻቸው ደንቆሮ ነጋዴዎች የተያዘው ኢትዮጵያ 10፣ 15 ዐመት ለፍተህም የምታገኘው አይደለም፡፡ ታድያ ለዚህ የሐገሪቷ ሐኪሞች ቢጋደሉ ምን ይገርምሀል የኔም የሌላ ተመዝጋቢዎችም ምክንያት በዋናነት ይህ ነው፡፡”

ስለክፍያውና ሌላሌላው እኔም ሰምቼ ነበር፡፡ ገንዘቡ ትንሽ እንዳልሆነ እኔም እስማማለሁ፡፡ እዚህ ሀገሬ ውስጥ ያለውን መራር ሐቅም በደምብ አውቀዋለሁ፡፡ ቢሆንም ጓደኛየ እንዲህ በሚያም መልክ ሲገልፀው ግን እንደአዲስ የሆነ ውጋት ነገር ተሰማኝ፡፡
ጓደኛየ ዘንድሮ የሆነ ትምህርት ለመማር እየተዘጋጀ ነበር፡፡ ያንን ጭምር መስዋእት አድርጎ ነው እየሄደ ያለው፡፡ ከጥቁር አምበሳና ዐይደር ሪፈራል ሆስፒታልም ትምህርት አቋርጠው ለመሄድ የተዘጋጁ እንዳሉ ይሰማል፡፡
የትውልዴ፣ የምሁሩ፣ የብርቱ ሰራተኛው ክፍል ተስፋ መቁረጥ አንገት የሚያስደፋ ነው፡፡ እኔ ይህ ብሄራዊ ውርደት ይመስለኛል፡፡


የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር! 

ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ – በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል።
— ክንፉ አሰፋ –

“እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል… ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።”
እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም… ይመስላል።

ፍርደ ገምድሉ የወያኔ ፍርድ ቤት ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ ለተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

አሸባሪው የወያኔ አገዛዝ ትንታግ የሆኑትን ወጣት ፖለቲከኞች በሽብር ወንጀል ተካፍለዋል፣ ድርጊቱን ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል፣ ህዝብን ለአመጽ ቀስቅሰዋል በሚል የፈጠራ ክስ አጎሮ ስቃይ እየፈጸመባቸው ሲሆን የካንጋሮው ፍርድ ቤት አራቱ ወጣት ፓለቲከኞችን እና በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት ሌሎች 6 ተከሳሾች ለቀረበባቸው የፈጠራ ክስ መቃወሚያ እንዲያቀርቡ ለታህሳስ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አገዛዙ በወጣት ፖለቲከኞች ላይ ያቀረበውን የፈጠራ ክስ እያወገዙ መቀጠላቸው ታውቋል። ወጣት ፖለቲከኞቹን ጨምሮ በአገዛዙ የፈጠራ ክስ ሰለባ ሆነው በእስር እየተሰቃዩ የሚገኙትን የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አገዛዙ በአስቸኳይ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የበይነ መረብ ዘመቻ መከፈቱም የታወቀ ሲሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን ዘመቻውን በመደገፍ ፋሽስታዊው አገዛዝ ሁሉንም የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታ አበክረው እየጠየቁ እንደሚገኙ ዘጋቢያች አመልክቷል።በሌላ ዜና የፋሽስቱ ወያኔ አገዛዝ እያደረሰባቸው ያለው ወከባ፤ አፈናና እስር ትግሉ እንደማይቆም የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አስታወቀ። “ነጻነታችን በእጃችን” ነው የሚለው ትብብሩ፣ ፋሺስታዊው አገዛዝ እየወሰዳቸው ባሉት እርምጃዎች ፈጽሞ ወደኋላ እንደማይል በማሳሰብ እቅዱን በህጋዊ መንገድ ለማስቀጠል እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል ያለውን ቁርጠኝነት ገልጿል።በመጨረሻም አገዛዙ ከአፈና ድርጊቱ እንዲገታና ለቀረበው ህጋዊ የዕውቅና ጥያቄ በአስቸኳይ መልስ እንዲሰጥ የጠየቀው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግሉ አላማ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ መሆኑን በማመልከት በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ለቀጣዩ ትግል የሚቀርበውን ጥሪ በንቃት እንዲከታተሉና ከፓርቲዎች ጎን እንዲቆሙ፣ ትብብሩን ያልተቀላቀሉ ፓርቲዎችም እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርቧል።

Sunday, November 30, 2014

በህዳር 27ቱ ሠላማዊ ሰልፍ እንሳተፋለን !!! ከኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ ኮሚቴ የተላለፈ የአጋርነት መግለጫ

ሠማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነት መድረክ በመፍጠር ሰላማዊ ሰልፍ ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2007 ዓ/ም ለማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀው የሐገሪቱ ህዝብ በቦታው በመገኘት ድምፁን እንዲያሠማ ባሳወቁት መሠረት የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እና የማህበሩ አባላት በሠላማዊ ሠልፉ ላይ ከሌላው የሐገራችን ህዝብ ጋር በመሆን ድምፃችንን እንደምናሠማ እየገለፅን ለሠላማዊ ሠልፉ መሣካት የበኩላችንን ደርሻም ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ በዚህ በጨለማ ዘመን ኃላፊነት ወስደው ይህንን ታላቅ ሠለማዊ ሠልፍ ላዘጋጁት የሠለማዊ ሠልፉ አዘጋጆች ምስጋናችንን በማቅረብ ነው፡፡
እንዳለመታደል ሆኖ ኢትዮጵያን እያስተዳደሩ ሳይሆን እየገዙ ያሉት ብዙሀኑ ባለስልጣናት ከትምህርት አለም እር

ኩማ ደመቅሳ በዋሽንግተን ዲሲ ሆስፒታል ተኝተዋል

(ኢየሩሳሌም አርአያ)

አቶ ኩማ ደመቅሳ በዋሽንግተን ዲሲ ሆስፒታል ተኝተው እንደሚገኙ ታማኝ ምንጮ አስታወቁ።

ኩማ በጭንቅላት እጢ (ቲዩመር) በሽታ ምክንያት ለከፍተኛ ህክምና ዲሲ መምጣታቸውን የጠቆሙት ምንጮቹ የመዳን ተሳፋቸው 90 በመቶ የተመናመነ መሆኑን ከሃኪሞች እንደተገለፀላቸው አስታውቀዋል።

ከባለቤታቸው ጋር የመጡት ኩማ ሆስፒታል ከመግባታቸው በፊት ባለፈው ሳምንት ማርዮት ሆቴል አርፈው እንደነበረ ሲታወቅ ሁለት ኢትዮጵያውያንን በሆቴሉ መተላለፊያ ላይ ሲያገኙ ክፉኛ ደንግጠው እንደነበረ ማወቅ ተችሏል። አሜሪካ -ዲሲ መምጣታቸው እንዳይታወቅባቸው የሚጠነቀቁትና ፍርሃት የሚታይባቸው ኩማ የስጋታቸው ምንጭ እንደሌሎች ባለስልጣናት ተቃውሞ ይገጥመኛል በሚል እንደሆነ ሲታወቅ የማያውቁትን ስልክ እንደማያነሱ ማረጋገጥ ተችሏል።

በተለይ የመዳን ተስፋ እንደሌላቸው ከተነገራቸው በኋላ ከኢትዮጵያ የሚደወልላቸውን ስልክ እንደማያነሱ ታውቋል። ኩማ ደመቅሳ ከ1993ዓ.ም በፊት ሙስና ውስጥ እንዳልገቡና ነገር ግን የአዲስ አበባ ከንቲባ ከሆኑ በኋላ በከፍተኛ ሙስና ከተዘፈቁት ባለስልጣናት ተርታ እንደተመደቡ ይታወቃል።


Saturday, November 29, 2014

የሕወሓት ሰዎች በብአዴን እና በኦሕዴድ ባለስልጣናት ላይ በአዲስ መልክ ሽብር እየፈጠሩ ነው::

ምንሊክ ሳልሳዊ
- የሕወሓት ስጋት ውስጥ ውስጡን ክሻእቢያ ጋር ግንኙነቱን እንዲያጠናክር አድርጎታል::
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ውስኝ የለውጥ ወቅት ላይ መሆኑን አውቆ አደባባይ በመውጣትወያኔን ሊያስወግድ ይገባል::ከፊታችን አደጋ አለ በሚል ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገቡት እና በመፍትሄፍለጋ ስብሰባዎች የተወጠሩት የሕወሃት ሰዎች ክከፍተኛ ባለስልጣናት ጀምሮ እንከ በታች ሹሞች ድረስ በብአዴንና በኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ ክፍተኛ የማስፈራራት እና የማዋከብ ሽብር እየፈጸሙ መሆኑን አንድ ከፍተኛ የኢሚግሬሽን እና ደህንነት ባለስልጣን ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ የሚገኙ የብአዴን እና የኦሕዴድ አባላት በግል እንዳይገናኙ እንዲሁም ከመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ጋር እንዳይገናኙ ከፍተኛ የሆነ ክትትል እየተደረገባቸው ሲሆን በባለስልጣናት ደረጃ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የሚያጠና የደህንነት ቡድን የተመደበባቸው ሲሆን ስልኮቻቸውም እየተጠለፉ መሆኑን እኚሁ ባለስልጣን ተናግረዋል::

የብአዴንና የኦሕዴድ ሰዎችን ከፍተኛ አነስተኛ እና ጥቃቅን በሚል ተከፍለው በሕወሓት እየተሰለሉ ስልካቸው እየተጠለፈ ሲሆን እንደ በግ የሚታዘዝላቸው የደቡብ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ውስጥ ዘልቀው እንዳይገቡ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑ ታውቋል::ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የሆኑ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለስልጣናት መቀራረብ እና አብሮ መዋል የሕወሓት ሰዎችን ማሳሰቡን እና የደህንነት ክትትል እያደረጉባቸው እንደነበረና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደመቀ መኮንን እና ከሙክታር ከድር ጀምሮ እስከ በታች የፌዴራል ባለስልጣኖች ላይ ከፍተኛ ስለላ እየተካሄደ ምንጮች መረጃ ሰተው እንደነበር ሲታወቅ ይህ በአሁኑ ወቅት በእጥፍ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቋል::ሁኔታዎች መልካም አይደሉም ከፊታችን አደጋ ተደቅኗል::ለውጥ ያስፈልጋል::የሚሉ የተቆጡ ድምጾች በስፋት በኢሕኣዴግ አባላት እየተሰሙ ያለበት አጣብቂኝ ውስጥ የከተተው ሕወሓት በግል እና በጋራ ባለስልጣናቱ ላይ ከፍተኛ ማስፈራራት እና ዛቻ እያደረገባቸው መሆኑን የተናገሩት ምንጮቹ ኢሕአዴግን ለመናድ ብትሞክሩ ሃገሪቷ ትበታተናለች::እንደ ሱማሊያ መንግስት አልባ ሆና እንደ ሩዋንዳ ትበጠበጣለች እያሉ ከማስፈራራትም አልፎ በግል የተነከራችሁበት ሙስና አደባባይ እናወጣዋለን:: እኛን ማንም ሊጠይቀን አይችልም ቁልፉ እኛ ጋር ነው የሚሉ በኣደገኛ መርዞች የተሞሉ ማስፈራሪያዎች መሰንዘር ክጀመሩ እንደቆዩ ተገልጿል::የኢትዮጵያን ህዝብ እንደ ሶማሌ እና ሩዋንዳ ማስብ ጅልነት ነው::የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ እንጂ ፍጅት ስለማይፈልግ ኢሕ አዴግ ሲፈርስ ሕወሓት እንደሚያስበው ሳይሆን ትልቅ ሰላም በሃገሪቱ ላይ ይሰፍናል ያሉት ምንጩ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ባለስልጣናት የየቀን ሪፖርት እና ግንኙነት በተመለከተ ማን ከማን ጋር እንደዋለ ማን እነማን ቤት እንደሄደ በመከታተል እየቀረበ ሲሆን የሃገሪቱን የደህንነት ቢሮ በጋራ የሚመሩት ጸጋዬ:ጌታቸውና ደብረጺሆን በየቀኑ ለትግሪኛ ተናጋሪ ደህንነቶች በአጫጭር ስብሰባዎች መመሪያ እያወረዱ ከመሆኑም በላይ አደጋ ውስጥ መሆናቸውን እየደጋገሙ እንደሚናገሩ ምንጮቹ አክለዋል::በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ ወሳኝ የትግል ወቅት ላይ መሆኑን በማወቅ የበሰበሰውን የወያኔ አምባገነን ስርአት ለመጣል በጋራ አደባባይ በመውጣት የሚያካሂደውን አብዮት የመከላከያ ሰራዊት የፖሊሱ እና የብአዴን እንዲሁም የኦሕዴድ ፓርቲ ለውጡን እንደሚደግፉት የህዝቡን መነሳሳት እየጠበቁ መሆኑን እና ሕወሓት ከመስጋቱ የመጣ ከሻእቢያ ጋር በውስጥ ግንኙነቱን አጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም ለተመረጡ የኤርትራ ስደተኞች የደህንነት ትምህርት የተሰጠ እንደሚገኝ እኚሁ ባለስልጣን መረጃ አድርሰውኛል:

Unipolar power in decline, new cold war & EPRDF in fear

By Robele Ababya, 28/11/2014I would like to start writing this piece, centered on respect for basic human rights, with this quote derived from the address to the European Parliament by His Holiness Pope Francis on 25 November 2014:- “Promoting the dignity of the person means recognizing that he or she possesses inalienable rights which no one may take away arbitrarily, much less for the sake of economic interests.” These are immortal words delivered to the August EU Parliament received with standing ovation and warm applause of the distinguished audience.It is needless to elaborate that genuine fighters for freedom, unity, equality, democracy and prosperity under the supreme rule of law should understand the alignment of global powers at play in terms of politics,

Court hands down prison sentence for an Eritrean trained terror convict

The Federal High Court 19th Bench handed Gashaw Shibabaw, a member of the outlawed Ethiopian People Patriotic Front (EPPF), a prison sentence of four years and eight months without probation.

The convict received shelter, training and logistical assistance from the Eritrean regime under the auspices of the terrorist group EPPF, before crossing into Ethiopia with his full military gear to launch terrorist attacks in the country.

In a statement the convict gave to police, he admitted to joining EPPF, a terrorist group supported by the notorious regime in Asmara and received military and political training in a place called Erena.

Two years ago, the convict crossed into Ethiopia with a small insurgent group to mount terrorist attacks in the country and was involved in several skirmishes with local security personnel, before being arrested in May, 2013.

The Federal Prosecutor brought terrorism charges against the individual and the convict admitted to joining an outlawed terrorist organization, to receiving military and political training in Eritrea, tirelessly working to carry out the group’s missions, illegally crossing into Ethiopia through River Tekeze with his full military gear, forcefully recruiting farmers to join the terrorist group, engaging Ethiopian security forces militarily and attempting to attack government institutions.

As such, the court sentenced the convict to serve a prison term of four years and eight months without probation.

በሚሰሩት መንገዶች ደስተኞች አይደለንም ሲሉ የባህርዳር ነዋሪዎች ገለጹ

ኢሳት ዜና :- የገዢው መንግስት በምርጫ 2007 ያለውን ተቀባይነት ለማጠናከር በማሰብ የተለያዩ የህብረተሰቡን ክፍሎች በየክፍለ ከተማው በማሰባሰብ የተሰሩ ስራዎችን በማቅረብ ለመመስገን ሙከራ ቢያደርግም፤ተሰብሳቢዎች ግን ምንም እንዳልተሰራና ተሰራ የተባለውም ችግር ያለበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የመንገዶች መበላሸት ያሳሰባቸው ነዋሪዎች በአካባቢው ላሉ አመራሮች የስራውን የጥራት ጉድለት ቢያሳውቁም የተስተካከለ ነገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ “በ2006 የተሰራው ስራ በሙሉ ዜሮ ነው፡፡ በየክፍለ ከተማው ያለው የሰራተኛ ቁጥር ከ 8 ወደ 102 እንዳደገ ብትነግሩንም ለኛ የተረፈን የባለስልጣን ጋጋታ እንጅ የህዝቡን ስራ የሚሰሩት በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜየችሁን በስብሰባና የፖለቲካ ስራ በመስራት ታሳልፋልችሁ ” በማለት የተሰራው ስራ ለፖለቲካ ትረፍነት እንጅ ለህዝብ ተብሎ እንዳልሆነ የተናገሩ ወገኖች አሉ፡፡ ሌላው ቅሬታ አቅራቢ በአሁኑ ሰዓት ያሉ የኮብል ስቶን ስራዎች የመኪና ጎማ የሚደበድቡ ጥራት የሌላቸው በመሆናቸው በመንገዶች ዙሪያ የሚሰሩት የተፋሰስ ስራዎች ሁሉ ጥራታቸውን ያልጠበቁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

Friday, November 28, 2014

የእስክንድር ነጋ ያገባኛል ባይነት!

በላይ ማናዬ
‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል!››

ይህን ያለው ትንታጉ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር ነጋን ካወኩት ወዲህ እንደዛሬ በኃይለ ቃል ሲናገር ሰምቼው አላውቅም፤ ወይም ትዝ አይለኝም፡፡ ዛሬ (ህዳር 19/2007 ዓ.ም) እኩለ ቀን ላይ እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሆኖም ሁኔታው ሁሉ እንደማንኛውም ቀን አልነበረም፡፡ በር ላይ ስደርስ በርከት ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰሞኑን እያካሄዱት ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ በማስመልከት እስክንድር ነጋን፣ አንዱዓለም አራጌን እና ሌሎችንም ሊጠይቁ በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡

በጠዋት ቂሊንጦ የሚገኙ ወዳጆቼን ጠይቄ አብረውኝ ከነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ጋር ነበር ወደ ቃሊቲ ያመራሁት፡፡ ቃሊቲ የተገኘው ሰው ሁሉ መጠየቅ የሚፈልገውን ሰው እና ሙሉ አድራሻውን እያስመዘገበ ሳለ በመሐል እኔም እስክንድርን መጠየቅ እንደምፈልግ ነግሬ ተመዘገብኩ፡፡ ከትንሽ ቆይታ በኋላ ግን ስማችሁ ከዚህ ቀደም ያልተመዘገባችሁ አሁን መግባት አትችሉም መባሉን መዝጋቢ ፖሊሱ አረዳን፡፡ እኔ እና ትንሽ ሰዎች መግባት ስንችል አብዛኛው ሰው ግን መግባት እንደማይችል ተነገረን፡፡

በዚህ ሁኔታ እስክንድር ጋር ደርሰን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አንድ የአንድነት ፓርቲ አባል ሰሞኑን ፓርቲያቸው እስረኞችን በተመለከተ በማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ እየተሰራ ያለውን ስራ ለእስክንድር ያብራራለት ጀመር፡፡ እስክንድር በተለመደ ጥሞናው ሲያዳምጠው ቆይቶ፣ በግሉ የተሰማውን እና መሆን ቢችል ያለውን ነጥብ ተናገረ፡፡ በመሐል ወጣቱ የአንድነት አባል ወደ እስክንድር ጠጋ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን ሲነግረው ድንገት አንድ የፖሊስ አዛዥ ጨዋታቸውን እንዲያቆሙና እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እንዲገባ፣ ወጣቱ የአንድነት አባል ደግሞ ወደ ውጪ እንዲወጣ በትዕዛዝ ማጣደፍ ያዘ፡፡

ይህኔ እስክንድር ለስለስ ባለ አነጋገር ምንም እንዳላጠፋን በመግለጽ ፖሊሱ መረጋጋት እንዳለበት አስረዳ፡፡ የፖሊስ አዛዡ ግን ጭራሽ ብሶበት ወጣቱ በቶሎ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ‹ፖለቲካ ማውራት አቁሙ› የሚል ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎ እስክንድር ድንገት በኃይለ ቃል ተናገረ፡፡ ‹‹መብቴን አሳልፌ አልሰጥም፤ የትም ብሆን ስለመብቴና ሀገሬ ያገባኛል፡፡ እዚህ ከሚጠይቁኝ ሰዎች ጋር የፈለኩትን ማውራት እችላለሁ፡፡ እናንተ ከፈለጋችሁ በር ላይ መልሷቸው እንጂ እኔ ጋር ከመጡ በኋላ ስለሀገሬ ከእነሱ ጋር መነጋገር መብቴ ነው፡፡ አዎ የትም ቦታ ብሆን፣ መቼም ቢሆን ስለ ሀገሬ ያገባኛል! የማወራው ስለ ሰላማዊ ትግል፣ ስለህጋዊ ትግል ነው!›› አለ እስክንድር በስሜት ውስጥ ሆኖ፡፡

በግሌ እስክንድር እንዲረጋጋ፣ ሁኔታው ግን ያልተገባ እንደሆነ ገለጽኩ፡፡ ፖሊሱ ግን ሊረጋጋ አልቻለም፡፡ እስክንድርን ይዞት ሄደ፡፡ ‹‹በርቱ! እንቅስቃሴያችሁ ህጋዊና ሰላማዊ ይሁን እንጂ ትግላችሁን ቀጥሉ!›› ሲል እስክንድር ወደ እስር ቤቱ እየገባ ተናገረ፡፡ የፖሊስ አዛዡም ከእስክንድር ጋር የነበረንን ቆይታ ሰዓቱ ሳይደርስ ገታው፡፡ የእስክንድር ያገባኛል ባይነት አስደመመኝ፡፡ እስር ቤት ሆኖም፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም እስክንድር ስለ ሀገሩ እንደሚያገባው በስሜት ተናገረ፡፡ መብቱን መቼም ቢሆን አሳልፎ እንደማይሰጥ አስረገጠ፡፡

ስለ ያገባኛል ባይነት ሳስብ በጠዋት ቂሊንጦ ያገኘኋቸውን የዞን 9 ጦማሪዎች አስታወስኩ፡፡ ‹ስለሚያገባን እንጦምራለን!› ይላሉ ወጣቶቹ ጦማሪያን፡፡ ከአብርሃ ደስታ ጋር አብረው ያገኘኋቸው እነ በፍቃዱ ኃይሉ እና አጥናፍ ብርሃኔ ብዙ ጉዳዮችን እያነሱ አወጉኝ፡፡ ‹‹ህወሓት አንድ ወይም ሁለት ነባር የህወሓት ባለስልጣናትን በሽብር ከከሰሰ ስርዓቱ እንዳበቃለት እቆጥራለሁ፡፡ ምክንያቱም ሽብር ማታለያ መሆኑ ይቀራል›› አለኝ በፍቃዱ ኃይሉ፡፡ አብርሃ ደስታ ቀበል አድርጎ ‹‹እናት አልጋነሽ በሽብር ስትከሰስ በጣም ብዙ ሰው ተቃውሞ ነበር›› አለ፡፡ አጥናፍ በበኩሉ ‹‹ቄስና ሸህ ሽብርተኛ እየተባለ አይደለም እንዴ›› በማለት ጠየቀ፡፡

አብርሃ ደስታ አንድ ነገር በኃይል እንደሚቆጨው ተናገረ፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅሁት፡፡ ‹‹ብዙ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ ሳላደርግ መታሰሬ ይቆጨኛል!›› አለ፡፡ በፍቃዱ በበኩሉ፣ ‹‹እኔም የገባኝ ነገር ያለውን የሰላማዊና ህጋዊ የመስሪያ ልክ አለመስራታችን ነው፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እንዲህ ለሚያስሩን ስንት ህጋዊና ሰላማዊ እንቅስቃሴዎችን እንኳ ሳናደርግ በትንሽ ነገር በርግገው እዚህ ሲያስገቡን ይቆጨኛል›› በማለት ሀሳቡን ቀጠለ፡፡ ‹‹በእርግጥ አንድ ሰው አሁን መጠንቀቅ ያለበት የሚሰራው ስራ ህጋዊ መሆን አለመሆኑን እንጂ፣ ይህን ካደረኩማ ያስሩኛል የሚለውን መሆን የለበትም፡፡ እነሱ ከፈለጉ ያስሩሃል፤ ስለዚህ መብትህን ተጠቅመህ መታሰሩ ይሻላል እንዲሁ ምንም ሳይሰሩ ከመግባት›› ሲል አብርሃ ሀሳቡን አካፈለ፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች 8 ሺህ ብር ዋስትና ተጠየቀባቸው

ለህዝባዊ ስብሰባ ሲቀሰቅሱ በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ዮሴፍ ተሻገር እንዲሁም የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆነው ሲሳይ በዳኔ ዛሬ ህዳር 19/2007 ዓ.ም ሾላ አካባቢ በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርበው 8 ሺህ ብር ዋስትና እንዲያስይዙ ተወስኖባቸዋል፡፡

መርማሪው ም/ሳጅን ዳንኤል ከበደ የምርመራ መዝገቡ እንዳለቀ ቢያምኑም ‹‹ተጠርጣሪዎቹ ከወጡ ተመሳሳይ ወንጀል ስለሚፈጽሙ ተጨማሪ ቀነ ቀጠሮ ይሰጥልን›› ብለው ተከራክረዋል፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል አቶ ዮሴፍ ‹‹በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አመራሮች በመሆናችን ወጥተንም የምንሰራው ህጋዊ ስራ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች በመሆናችን የዋስትና መብታችን ሊጠበቅልን ይገባል›› ሲሉ ተከራክረዋል፡፡

አቶ ሲሳይ በዳኔ በበኩሉ ‹‹አሁንም በምርመራ ወንጀል መስራታችን የሚያሳይ ነገር አላገኙም፡፡ ምንም አይነት ወንጀል ሳንሰራ ነው የታሰርነው፡፡ ቋሚ መኖሪያ ያለን ሰዎች ነን፡፡ በመሆኑም ዋስትናችን ሊከበርልን ይገባል›› ሲል ተከራክሯል፡፡ በመጨረሻም ዳኛ አያሌው ደስታ ሁለቱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እያንዳንዳቸው 4 ሺህ ብር የገንዘብ ማስያዢያ (ዋስ) እንዲያቀርቡ ወስነውባቸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ለእስር የተዳረጉት ሌሎች ሁለት የፓርቲው አባላት ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ ሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ እንደተሰጠባቸው የሚታወስ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ሰማያዊ ፓርቲ ባደረጋቸው ሰልፎች በፖሊስ የሚያዙ የፓርቲው አባላት በተደጋጋሚ የገንዘብ ዋስትና ሲጠየቅባቸው ቆይቷል፡፡

“Breaking the Cycle of Dysfunction in Ethiopians Institutions forum”

November 18, 2014. Washington, DC–. At the recent  in Washington D.C. on November 15, it was quite evident that Ethiopia does not lack for gifted people who possess the essential capabilities, virtue, and experience needed to build a New Ethiopia.

It was inspiring to hear from a wide array of speakers who portrayed the qualities of courage, strength, faith, wisdom, integrity, and an attitude of respect towards others, even when some differences of opinion emerged. This was a civil dialogue, meant to be a model for how Ethiopians with grievances against each other or simply of diverse backgrounds might come together to forge a better future. People came together as people first. Then, they came together around shared values—a desire to see a society where truth, freedom, justice, civility, opportunity, and harmony could prevail for all its people.Discussions both within the forum and outside the formal discussions were lively as people, most of whom had never met, shared opinions, ideas, and stories. New connections were made. The forum, Breaking the Cycle of Dysfunction in Ethiopians Institutions was unique in that it focused on providing a structured venue where Ethiopians could  It was broken into two sessions.

ቅኝ ግዛት እና ሕዝቡን ቢራ እንዲጠጣ ማበረታታ ምን እና ምን ነበሩ? ዳቦ ሳንጠግብ እና የምናነበውን ጋዜጣ ሁሉ ዘግተው አዕምሯችንን እያደነዘዙ የቢራ ፋብሪካ መደርደር ምን ይባላል?

በባዕዳን በቅኝ ግዛት ተይዘው የነበሩ ሀገሮች ሁለት ዋና ዋና ሀብታቸውን አጥተዋል።( በነገራችን ላይ በባዕዳን ቅኝ ግዛት የተያዙቱኑ ነው ያልኩት እንጂ ፕሬዝዳንት መሆን ያማረው ሁሉ ቅኝ ግዛት ነበርኩ እያለ የእራሱን እና የህዝቡን ክብር ገደል የሚጨምረውን አይመለከትም።)ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ካልተገዙ ጥቂት ሃገራት አንዷ ነች።ኢትዮጵያውያንን ቡና አትጠጡ ቢራ ብቻ ጠጡ ብሎ ያስገደዳቸው ቅኝ ገዢ አልነበረባቸውም።እድሜ በደማቸው ሀገራቸውን አስከብረው ለኖሩት አባቶቻችን እና እናቶቻችን።እኛ እንደ ብዙ የአፍሪካ ሃገራት ዋና ከተማችንን የቅኝ ገዢዎች አልመረጡልንም። አለመምረጥ ብቻ አይደለም የከተሞቻችን ህንፃዎች እና መንገዶች በአብዛኛው የተሰሩት በእራሳችን መሀንዲሶች ነው።የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃቤት ፕላን ሲቀርብ አንድ ፈረንሳዊ መሃንዲስ ባለ ብዙ ፎቅ እንዲሆን አድርጎ አቅርቦ ነበር።በኃላ ግን ኢትዮጵያዊው መሃንዲስ (ስማቸውን አላስታውስም) ወደ ንጉሡ ቀርበው ”ይህንን ያህል ፎቅ ብዙ ሕዝብ በእየለቱ በሚወጣበት እና በሚገባበት ህንፃ ላይ አይሆንም።ይህ ማለት ከሀገሩ ሊፍት እንድናስገባ ሊያደርገን ነው።ከእዝያ ይልቅ ወደጎን ነው መለጠጥ ያለበት” ብለው ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት ማዘጋጃ ቤቱ ወደጎን እንዲሰፋ ተደረገ።በእዚህም ብዙ ሕዝብ ለጉዳዩ በቀላሉ ለመውጣት እና ለመግባት ቻለ።ቅኝ ገዢዎች መሰረተ ልማቱን እንዴት ለሀገራቸው ኢንዱስትሪዎች መጋቢ እንዲሆን አድርገው እንደሚቀርፁ የሚያመላክት አንዱ ማሳያ ነው የማዘጋጃ ቤቱ ህንፃ ጉዳይ።

የፓርቲዎች ትብብር ለአዳሩ ሰልፍ ቦታው መስቀል አደባባይ እንዲሆን ወስኗል

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ለአዳሩ ሰልፍ የእውቅና ደብዳቤ አስገባ
የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2007 ዓ.ም ለሚደረገው የአዳር ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ ህዳር 18/2007 ዓ.ም ለአዲስ አበባ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የእውቅና ደብዳቤ አስገባ፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ለሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል የገባው ደብዳቤ በሰማያዊ፣ መኢዴፓ እና ኢብአፓ ተፈርሞ የገባ ሲሆን የእውቅና ደብዳቤውንም ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲና የትብብሩ ሊቀመንበር፣ የከንባታ ህዝቦች ሊቀመንበርና የትብብብሩ ም/ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርጌሎ፣ አቶ ግርማ በቀለ ከኦሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅትና የትብብሩ ፀኃፊ እና የመኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ኑሪ ሙደሲር አስገብተዋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች ወደ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍሉ በሄዱበት ወቅት የአቶ ማርቆስ ተወካይ ለሆኑት አቶ ፈለቀ አበበ ደብዳቤውን ለመስጠት ጥረት ቢያደርጉም ተወካዩ ‹‹የከንቲባ ጉዳዮች ጽ/ቤ ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው የለም፡፡ እሱ ካልመራበት መቀበል አንችልም›› በሚል ደብዳቤውን አልቀበልም እንዳሏቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ አመራሮቹ ወደ አቶ አሰግድ ቢሮ ቢያቀኑም እንዳላገኙዋቸው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ሆኖም የትብብሩ አመራሮች ደብዳቤ መስጠት እንጂ ደብዳቤ ማስመራት የሰራተኞቹ እንጂ የእነሱ ስራ እንዳልሆነ በመግለጽ ደብዳቤውን ዛሬ ህዳር 18/2007 ዓ.ም ታመዋል የተባሉት የአቶ ማርቆስ ተወካይ የሆኑት አቶ ፈለቀ ቢሮ በአራት ምስክሮች ፊት አስቀምጠው መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡ አመራሮቹ የእውቅና ደብዳቤውን አቶ ፈለቀ ቢሮ አስቀምጠው ከመውጣታቸውም ባሻገር በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በፈጣን መልዕክት (ኢ ኤም ኤስ) በሪኮመንዴ ቁጥር eg157416502et መላካቸውን ገልጸዋል፡፡

የአዳር ሰላማዊ ሰልፉ ህዳር 27 ከጠዋቱ 3 ሰዓት ተጀምሮ ህዳር 28 ከቀኑ 6 ሰዓት ላይ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቅ ሲሆን ቦታውም መስቀል አደባባይ ላይ እንደሚሆን መወሰኑ ታውቋል፡፡

የትብብሩ አመራሮች የእውቅና ደብዳቤውን ለማስገባት በሄዱበት ወቅት በቦታው የትብብሩ አመራሮች የሚያውቋቸው ደህንነቶች ባለ ጉዳይ በመምሰል ይመላለሱ እንደነበርና ፖሊሶችም ይከታተሉ እንደነበር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Thursday, November 27, 2014

ተማሪዎች፣ መምህራን እና የተቋማት ፕሬዚዳንቶች ለአመጽ ተነሱ!

ዘረኛውና አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከላትነት ለይቶ የማያይ ስለመሆኑ በተቋማቱ ውስጥ የሚደረጉ ተግባራት ማረጋገጫዎች ናቸው። ለዚህ ተግባሩ በሰነድ ደረጃ መቅረብ ከሚችሉት የቅርብ ጊዜ ማስረጃዎች ዋነኛው በህዳር 2007 ዓ.ም. በሥራ ላይ የዋለው “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል” የተሰኘው በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላለፈው ሰነድ ነው። ይህ ሰነድ፣ የህወሓት አሳፋሪ የትምህርት ፓሊሲ ባፈጠጠ መልኩ የተገለፀበት፤ የኢፌዴሪ መንግሥት ተብሎ በሚጠራው የህወሓት አገዛዝ ተቋም እና በህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲ መካከል ለይምሰል እንኳን ልዩነት አለመኖሩ በግላጭ የሚታይበት ሰነድ በመሆኑ በዚህ ርዕሰ አንቀሳችን በስፋት ልንዳስሰው ወስነናል።ሰነዱ በትምህርት ሥርዓቱ ላይ መርዙን መርጨት የሚጀምረው ገና በመግቢያው ስለማንዋሉ አስፈላጊነት ሲገልጽ ነው። ማንዋሉ “ከምንም በላይየብጥብጥና የሁከት መንስኤ የሆነውን ተማሪ በኢህአዴግ አመራር አባላት እየታገዙ ለመያዝ የሚያስችል ነው” በማለት ህወሓት ተማሪውን የሚመለከተው “ከምንም በላይ በብጥብጥ መንስኤነት” መሆኑ፤ ለዚህ መድሀኒቱ ደግሞ ተማሪውን በኢህአዴግ አመራር አባላት “መያዝ” መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ይገልፃል። ቀጥሎም “በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሁከትና ብጥብጥ ለማስቆም በማደራጀት መረጃ ለመጥለፍ አመችነቱ የላቀ እንደሚሆን ታምኖበታል” በማለት መረጃ መጥለፍ የዩኒቨርስቲዎችና የትምህርት ሚኒስቴር ሥራ እንደሆነ አድርጎ ያቀርባል።የማንዋሉን ዓላማዎች በሚገልፀው ክፍል ደግም “… የከፍተኛ ትምህርት የትምህርት የልማት ሰራዊት ግንባታን ወይም የፓለቲካ ሰራዊት ግንባታ በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተደራጀና በተናቀጀ ሁኔታ በማቀጣጠ

ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በድጋሚ ተከሰሰች!

የ‹‹ ቆንጆ ›› መፅሔት ዋና አዘጋጅና የ‹‹ ጃኖ›› መፅሔት ዓምደኛ የነበረችው መልካም ሞላ ሀምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ዜና እወጃ ላይ ‹‹ህገ-መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በመንቀሳቀስ፣ ህዝቡን ለዓመፅ ማነሳሳትና የሽብር ስራን ለምስራት ማቀድ ›› በሚል የፍትህ ሚኒስቴር ክስ የመሰረተባት መሆኑን በዜና አቅራቢው ተመስገን በየነ በኩል የተከሰሰች መሆኑን የሰማችና ከዚያም ባሉት ተከታታይ ቀናት የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ለጥያቄ እንደሚፈልጋት ጥሪ ከደረሳት በኋላ የምትወዳትን ሀገሯን፣ ሙያዋንና ቤተሰቦቿን ትታ ዿግሜ 4 ቀን 2006 ዓ.ም ከሀገር መሰደዷ ይታወቃል ፡፡

ይሁን እንጂ የማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ በያዝነው ህዳር ወር 2007 ዓ.ም ከሀገር ከመውጣቷ በፊት በዋና አዘጋጅነት ትሰራበት ለነበረው የ‹‹ቆንጆ›› መፅሔት ሥራ አስኪያጅ ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ካሣን የወንጀል ምርመራ ቢሮ በማስቀረብ በጥር ወር 2006 ዓ.ም ማለትም ከአንድ ዓመት በፊት ‹‹ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት ምን እየሰራ ነው ? በሚል ርዕስ ሥር በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማዊነት መስፋፋትን በተመለከተ በፃፈችው ፁሁፍ ‹‹ ህዝቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጋለች ›› በሚል ክስ እንደመሰረተባትና ለጥያቄ እንደሚፈልጋት በመግለፅ ሥራ አሥኪያጁ እንዲያቀርባት ታዟል፡፡ ይሁንና ጋዜጠኛ መልካም ሞላ በሀገር ውስጥ የሌለች በመሆኑ ከዚህ በፊት በሎሚ፣ በጃኖ ፣በአዲስ ጉዳይና በሌሎች የመፅሔት አሳታሚዎች ላይ እንደቀረበው የአሸባሪነት ክስ በቆንጆ መፅሔት አሳታሚ ላይም ይህ የክስ ፋይል እንደሚከፈት የታመነ ሲሆን ለጊዜው ግን ከአንድ ዓመት በፊት በፃፈችው ፁሑፍ ‹‹ ህዝቡን በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ አድርጋለች›› በሚል ክስ የቀረበባት ጋዜጠኛ መልካም ሞላን ካለችበት ቦታ አስሮ እንዲያቀርብ የፌደራል ፖሊስ የከባድ ወንጀል ምርመራ ክፍል የታዘዘ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በ21ኛው ክ/ዘመን መንግሥት አላባዋ ሀገር ፣መንግሥት አልባው ሕዝብ ።

የኢትዮጵያውያን ደም እንደውሻና እንደ ድመት በአረብ ሀገር አውራ ጎዳና ላይ መፍሰሱ የተለመደ በመሆኑ ዛሬ ዛሬ እንደዜና ለወሬም አልተመቸም አሰልች ሁኗል ።

ትላንት ውባለም የተባለች አንዲት ኢትዮጵያዊት  ቤይሩት ኢጀኑብ (ኢዘሪሂ) በሚባለው ከከተማው ወጣ ባለ አካባቢ ራሷን
ከሶስተኛ ፎቅ ላይ በመጣል ህይወታ ሊያልፍ ችልዋል።

በትላንትናው እለት የ20 አመት እድሜ ያላት ውባለም የተባለች አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ በደቡብባዊ ሊባኖን ከአሰሪዎቿ ቤት 2ኛ ፎቅ ላይ ወድቃ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ፡፡

አንዳንድ አለምአቀፍ ድርጅቶች የቤት ሰራተኞች ሰብዓዊ መብቶች በስፋት በሚጣስባት ሊባኖን ሰራተኞች ጥቃት እዳይደርስባቸው ለመከላከል እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ዴይሊ ስታር ሲዘግብ

በአረብ ሀገራት የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጥቃት የሚደርስባቸው ቢሆንም በየአረብ ሀገራቱ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ወይም ቆንፅላ ጽ/ቤቶች ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ጥረት እንደሌለ አንዳንድ በአረብ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተናግረዋል፡፡

የዜጎች መብትን ማስጠበቅ ካልተቻለ የኤምባሲዎቹና ቆንፅላ ጽ/ቤቶች እዛ መገኘት ፋይዳው ግልፅ አይደለም ይላሉ ችግሮቹን በቅርበት የሚመለከቱ ኢትዮጵያውያን፡፡


Wednesday, November 26, 2014

ቆንጆ መጽሔት ተከሰሰች

ከሁለት ሳምንት በፊት ከማዕከላዊ የምርመራ ቢሮ ከወዲያኛው ጫፍ የደወለው ሰው እንደነገረኝ ‹‹ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ነው›› ብሎ ደወለልኝ፡፡ ደዋዩ ቆንጆ መጽሔት መሆኑን ካጣራ በኋላ ዋና አዘጋጇ ስልክ ላይ ብደውል ዝግ ነው ፤ ጥር ወር ላይ ባወጣችሁት ዘገባ እኛ ጋ ክስ ተመስርቶባችኋል አለኝ፡፡ ስለሆነም ለዋና አዘጋጇ መልዕክት አድርሱ መጥታ ቃሏን ትስጥ አለኝ፡፡ ለጊዜው በቅርብ እንደሌለች ነገርኩት፡፡ ‹‹እሺ›› ብሎ ስልኩን ዘጋው፡፡ ድጋሚ ባለፈው ሳምንት አንድ ስልክ ተደወለ፡፡ በወቅቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ስለነበርኩ ስልኩን ማንሳት አልቻልኩም፡፡ ስወጣ ግን ደወልኩ፡፡ ስልኩን ያነሳችው ሴት ‹‹የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዋና (ማዞሪያ ስልክ)›› መሆኑን ነገረችኝ፡፡ እንግዲህ ይህ ስልክ ግቢ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ የሚጠቀሙበት በመሆኑ እንደ እኔ ሞባይሉ ላይ ሚስድ ኮል አይቶ መልሶ ለደወለ ማን እንደደወለለት ገና ተጠያይቆ ነው የሚታወቀው፡፡

ርዮት አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንድቅ አላማ በላይዋ ላይ ለብሳ በክብር ከቃሊቲ ትወጣለች – ግርማ ካሳ

በሃይ ስኩል የእንግሊዘኛ አስተማሪ ነበረች። በሕገ መንግስቱ ላይ የተደነገገዉን መብት በመጠቀም፣ በተለያዩ አገር ውስጥ በሚታተሙ ሜዲያዎች ትጽፋለች። «እነርሱ እንዲጻፍ ከሚፈልጉት ዉጭ እንዲጻፍ የማይፈልጉ ባለስልጣናት፣ የሃሰት ክስ መሰርተዉ፣ ዳኛ ለተብዬዎች መመሪያ ሰጠዉ፣ መሰረተ ልማቶችን ለማፍረስ አሴራለች፣ ሽብርተኛ ናት» ብለዉ ፈረዱባት።

ይች እህት ርዮት አለሙ ትባላለች። ጡቷ አካባቢ ችግር ስላለበት ክትትል እንደሚያሰልጋት እየታወቅም ክትትል እንድታገኝ አልተደረገም። ወደ ሶስት አመት ገደማ ባላጠፋችዉ ጥፋት፣ ኢሕአዴግን ስለተቃወመች ብቻ፣ እየማቀቀች ነዉ። የርዮት ወንጀል አገሯ፣ ሕዝቧን መዉደዷ ነዉ።

ቦታ ጠበብኝ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ታላቁ መንግስታችን የኢትዮጵያዊነት እሴቶች የሆኑት ነገሮች ሁሉ መደርመሱን ቀጥሎበታል። የነጻነት እና የማንነት ተምሳሌት የሆኑት አብይ ኩነቶችን ጭቃ ከመቀባት እስከ አፈር ማልበስ፣ ከማብጠልጠል እና ማናናቅ እስከ መቀበር፣ ከ መዝረፍ እና ማዘረፍ እስከ ፍጽሞ ማጥፋት እየሄደበት ያለውን መነገድ አስፋፍቶ ቀጥሎበት ትናንት ደሞ የ ታላቁን ወ-መዘክር መጻሕፍት ቤት ታሪካዊ መጽሐፍቶች ( የባለ ብዙ ዘመን እድሜ መጽሐፍቶች ) በኪሎ እንደሸጠው ሰምተናል። እነዚህ መጽሐፍቶች በውስጣቸው የያዙት ቁም ነገሮች ትውልድ የሚቀርሱ ፣ የማንነት መቅርጫዎች፣ የአእምሮ መሳያዎች ነበሩ። ዛሬ ግን ስኩዋርና እጣን መጠቅለያ ይሆኑ ዘንድ ተፈርዶባቸው በየ -ስርጡ ተወሽቀው ይገኛሉ። የሚገርመው እነዚህም መጽሐፍቶች ” ቦታ ጠበበኝ

Tuesday, November 25, 2014

በለገጣፎ ከተማ ከ32,000 ሺህ በላይ ዜጐች ቤት አልባ ሊሆኑ ነው

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ለ12 ዓመታት በአካባቢው መኖሪያ ቀልሰው ኖረዋል፡፡ ሆኖም “የከተማ ሰው ወሮናል” የሚል ተቃውሞ በገበሬው እንዲነሳ ያደረጉ የከተማው ባለሥልጣኖች በ2 ቀናት ውስጥ ቤታችን ሊያፈርሱ ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡ የካ ሰዴን ወረዳ የሚገኙት የጉራ፣ሰፈራ፣ድሬ፣ ዳሌ እና ቀርሳ የሚባሉ አካባቢዎች ውስጥ የሚገኙ ወደ 3000 ሺህ የሚጠጉ ቤቶች እንዲፈርሱ ምልክት ተደርጎባቸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ቅዳሜ ህዳር 13 ቀን 2007ዓ.ም በከተማው በመሰባሰብ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል፡፡ በነጋታው እሁድ ዕለትም ከ1000 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎች በመሰባሰብ ባጋጠማቸው አደጋ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ የነዋሪዎቹን ችግር ለማዳመጥ ፈቃደኛ ያልሆኑት የከተማው የመንግስት ባለስልጣናት ግን በቅዳሜው በስብሰባው ላይ ባለመገኘታቸው ነዋሪዎቹ በነጋታው እሁድ ከ1000 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች በወረዳው ጽ/ቤት በመገኘት ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ሰኞ ህዳር 15 ቀን 2007 ዓ.ም በድጋሚ በመሰባሰብ 10 ተወካዮቻቸውን ወደ 4 ኪሎ ፓርላማ መላካቸውን በስፍራው የተገኘው የፍኖተ ነፃነት ዘጋቢ አረጋግጧል ፡፡


Monday, November 24, 2014

ለስብሰባ ሲቀሰቅሱ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ተጨማሪ 7 ቀናት ተቀጠረባቸው


የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 7/2007 ዓ.ም ጠርቶት ለነበረው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ አርብ ህዳር 5/2007 ዓ.ም በቅስቀሳ ላይ እንደነበሩ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ 7 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ም/ሰብሳቢና የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ወጣት ማቲያስ መኩሪያ እና የምርጫ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ወጣት ሳምሶን ግዛቸው በቅስቀሳ ወቅት ተይዘው አራዳ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩ ሲሆን ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ችሎት ቀርበው የ7 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ወጣቶቹ ‹‹ሽብር በማነሳሳት›› የሚል ‹ክስ› የተመሰረተባቸው ሲሆን ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ ሌሊት ደህንነቶች በተደጋጋሚ በኃይልና በዛቻ እንደሚመረምሯቸው መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡

ባለፈው የፍርድ ውሎ ታሳሪዎቹ ህጋዊ እውቅና ለተሰጠው ስብሰባ የቀሰቀሱ መሆኑን ጠቅሰው መታሰራቸው ህገ ወጥ በመሆኑ እንዲፈለቀቁ ቢከራከሩም፤ ፖሊስ ‹‹ሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ስላልተያዙ መያዝ አለብን፡፡ እነሱም ከተለቀቁ መረጃ ያጠፉብናል›› በሚል የ7 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተቀባይት አግኝቷል ለዛሬ በቀጠሯቸው መሰረት ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ አንድ ሳምንት ጊዜ ለፖሊስ ፈቅዶለታል፡፡ በአንጻሩ ታሳዎቹ የቀረቧቸው ቅሬታዎችና መከራከሪያዎች ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡

Sunday, November 23, 2014

በሰሜን ጎንደር የሕወሓት አማሳኞች ሰርገው የበመግባት ወጣቱን እያጋደሉ መሆኑ ተሰማ::

-ከከተማው ለስራ የሄዱ ወጣቶች ንብረታቸውን እና ገንዘባቸውን ሳይሰበስቡ አከባቢውን ለቀዋል
በኢትዮ ሱዳን ድንበር ላይ ለስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን መንደር እየለዩ በመቧደን በከፍተኛ ጭፍጭፍ ውስጥ እንደሚገኙ ከአከባቢው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል::

ከሱዳን ጋር በተያያዘው እና የታች አርማጮ መሬት ከሆነው ሰቲቱ ሁመራ ማይካድራ ሉግዲ አብዲራፍ አብድራሃጀር መተማ ሸዲ የተወሰነውን ጠገዴ ያሉት የጎንደር መሬቶች ላይ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተማሩ የሕወሓት አባላት የሆኑት የጊዜው ባለሃብቶች በቀተሯቸው እና ከአማራው ክልል ጎንደር ጎጃም እና ወሎ የመጡ ወጣት ገበሬዎችን እርሲ በራስ በመንደር እና በጎጥ በመከፋፈል እንዲተራረዱ እንዲጨራረሱ የሰሩበትን ገንዘብ ሳይሰበስቡ አከባቢውን በፍርሃት ለቀው እንዲሄዱ እያደረጉ መሆኑን መረጃዎቹ የሰሞኑን ከፍተኛ ግጭት አስመልክተው ጠቁመዋል::

በሉግዲ አከባቢ በዚህ ሰሞን ብቻ በጎንደር እና በጎጃም በወሎ እና በሸዋ በሚል የተቧደኑ ሰዎች በሕወሓት ኢንቨስተሮች ነገር አስፋፊነት ከፍተኛ ግጭት በመከሰቱ በርካታ ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን ቀሪዎቹ ንብረታቸውን እና ገንዘባቸውን ሳይሰበስቡ ድንገት ግጭቱን ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሄዱ መሆናቸው ታውቋል::

የሕወሓት አማሳኞች እና ሰላዮች በወጣቶቹ መካከል ሰርገው በመግባት እሪስ በ እርስ ጎጥና መንደር እንዲለይ አድርገው በማቧደን እርስ በ እርስ ሕዝቡ እንዲተራረድ አድርገዋል ሲሉ ምንጮቹ በላኩት መረጃ ተናግረዋል::በዚህ ሳምንት ብቻ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ሬሳዎች ወደ ሉግዲ ከተማ የተጓጓዙ ሲሆን ይህ የሕወሓት ሰላዮች/አማሳኞች የሚቀሰቅሱት የሰርጎ ገብነት ዝሴራ እስከ ማይካድራ ድረስ ተስፋፍቶ ከፍተኛ የደም መፋሰስ እና የዘር መጠፋፋት እየተደረገ መሆኑን አክለው ገልጸዋል::

ታሪክን ማደብዝዝም ማጥፋትም አይቻልም!

በአለማችን በተለይ አፍሪካ ዉስጥ የአገርን ብሄራዊ ኃብት የሚዘርፉ፤የህዝብን መብት የሚረግጡና አገርን እነሱ ባሰኛቸዉ አቅጣጫ ብቻ ይዘዉ የሚነጉዱ አያሌ ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት አሉ። እነዚህ ህዝብን የሚበድሉ መንግስታት ሁሉም በጥቅሉ አምባገነን ይባሉ እንጂ በመካከላቸዉ ጎላ ብሎ የሚታይ ትልቅ ልዩነት አለ። ሀኖም የቱንም ያክል ልዩነት ቢኖርም እንደ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ የሚንቁና የኛ ነዉ የሚሉትን አገር የሚጠሉ አምባገነን መንግስታት የሉም፤ በታሪክም ኖረዉ አያዉቁም። አምባገነን መንግስታት የስልጣን ዘመናቸዉን ለማራዘምና ከስልጣን ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን ክብር፤ ዝናና ጥቅማ ጥቅም እንዳይቋረጥ ሲሉ የሚቃወማቸዉንና ለስልጣን ዘመናቸዉ አደጋ ነዉ የሚሉትን ሁሉ ያስራሉ፤ ይደበድባሉ ወይም ይገድላሉ።

ሰበር ዜና የበይነ መረብ ዘመቻው ኢህአዴግን አሳስቦታል

አንድነት ፓርቲ በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያካሂድ ይፋ ያደረገው የበይነ መረብ ዘመቻ ግቡን እንዳይመታ በቅርቡ አሰልጥኖ ባሰማራቸው የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ብሄርን፤እምነትን እና የአንዱ ፓርቲ ደጋፊና የሌላው ፓርቲ ነቃፊ በመሆን አጀንዳዎን በማንሳት የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎችን ትኩረት ለመሳብና የፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች ወደ ጋራ አጀንዳ እንዳይሰባሰቡ ሳምንቱን ሙሉ በንቃትና በጥንቃቄ መስራት እንዳለባቸው በኢህአዴግ ጽ/ቤት በኩል በዛሬው እለት ማስጠንቀቂያዊ ትዕዛዝ መተላለፉን ማስጠንቀቂያው የደረሳቸው ተሳታፊ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገልፀዋል ፡፡እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ገለፃ ምን አልባትም ዘመቻው ትኩረት እየሳበ የሚሄድ ከሆነ በቴሌ አማካኝነት የኔት ወርክ መስተጓጎል እና ማቋረጥ ለመፍጠርም መታሰቡን አያይዘው ገልፀዋል፡፡አንድነት ፓርቲ የበይነ መረብ ዘመቻ በቀጣይ ሳምንት እንደሚያደርግ በትላንትናው እለት ለመገናኛ ብዙሀን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡


Friday, November 21, 2014

ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ ዲያስፖራውን ወቀሱ “ዲያስፖራው ገዥው ፓርቲ የሚሰራው ሥራ ሁሉ ጥፋት ነው ብሎ ራሱን አሳምኖ ቁጭ ያለ ነው”

ከአንድ ዓመት ላላነሰ ጊዜ በአሜሪካን ሀገር በቺካጎ ከተማ በሚገኝ አንድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲያስተምሩ ቆይተው በቅርቡ ወደሀገር ቤት መመለሳቸውን የተናገሩት የወቅቱ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ዲያስፖራውን ወቅሰዋል።

ፕሮፌሰሩ በዛሬው ዕለት ለንባብ ከበቃው መንግስታዊው ዘመን መጽሄት የጥቅምት 2007 ዕትም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ “ዲያስፖራው ተስፋ የቆረጠና የተናደደ ነው፡፡ ተስፋ ስለቆረጠና ስለተናደደ ገዥው ፓርቲ የሚሰራው ሥራ ሁሉ ጥፋት ነው ብሎ ራሱን አሳምኖ ቁጭ ያለ ነው፡፡ በዚህም የሚናደድና የሚንቦገቦግ ነው፡፡

እናም ከእነዚህ ጋር ውይይት ማድረግ አይቻልም፡፡» ብለዋል። ፕሮፌሰር በየነ በዚሁ ቃለምልልሳቸው “ዲያስፖራውን ለመምከር እንሞክራለን» ካሉ በኃላ በአሜሪካ ቆይታቸው ወቅት እርሳቸው ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙ ሰዎች እንዲበተኑ እንደተደረገ ተናግረዋል።

መጽሄቱ በእሳቸው ላይ ይህ ለምን እንደተደረገ ጠይቆአቸው በሰጡት ምላሽ “እኔ እውነቱን ስለማወጣ ነው» የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኢህአዴግ በአንድ በኩል እኛን ትክክል ባልሆነ ምስል ያስቀምጠናል ያሉት የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ዲያስፖራው ደግሞ የባሰ በመሆኑ መቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡


አንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች” የሚል ዘመቻ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ ከህዳር 14 እስከ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚቆይ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች” የሚል የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ አዘጋጅቷል። በዚህ ዘመቻ ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ለታዋቂ ግለሰቦች፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ለልዩ ልዩ የሚዲያ ድርጅቶች በኢንተርኔትና በሶሻል ሚዲያ በኩል መልዕክት በመላክ በሀገራችን ያሉት የፖለቲካ እስረኞች ሁኔታና አያያዝ በተመለከተ መረጃ በመስጠት ተገቢ የሆነ አያያዝ እንዲኖራቸው፤ ከእስር እንዲፈቱ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን ማሰርና ማዋከብ እንዲቆም በመንግስት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል። በዚህ ዘመቻ ላይ ሁሉም የዘመቻው ደጋፊና በሀገሪቱ ዴሞክራሲያው ስርዓት እንዲመሰረትና የዜጎች ሰብዓዊ መብት እንዲከበር የሚሹ ሁሉ ከላይ ለተጠቀሱት ግልሰቦችና ተቋማትን ጨምሮ ሚሊዮኖች ለሚያውቁትና ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል ለሚሉት ሰው ሁሉ መልዕክት በኢንተርኔትና በሶሻል ሚዲያ በመላክ ድምፃቸውን ያሰሙ ዘንድ ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም. አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና ጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ፓርቲው ከዚህ በፊት ከህዝቢ ከፍተኛ ድፍ ያስገኘለትን “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት” እና “…ለመሬት ባለቤትነት” የሚሉ የተለያዩ ህዝባዊ ስብሰባዎችን እና የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎችን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ማድረጉ ይታወቃል፡፡  የዛሬውን ሙሉ ዝርዝር መግለጫ ከታች ይመልከቱ፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ምርጫ ሲባል አማራጭ ሳያሳጡ መሆን ይኖርበታል
 ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ()  ጋዜጣዊ መግለጫ

በሀገራችን ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ ሀገራዊ ምርጫ እንደሚደረግ በመንግስት በኩል በከፍተኛ ደረጃ የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት የተከናወኑት አራት ምርጫዎች ያየን እንደሆነ በሀገራችን የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ወደፊት ሊወስዱ እንዳልቻሉ እሙን ነው፡፡ ይህም ሆኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ፍላጎት በተለያየ መንገድ ሲገልፅ ቆይቷል፡፡ በተቃራኒው መንግስትና ገዢው ፓርቲ በፍፁም መለየት በሚያስቸግር ሁኔታ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ሆነው ተቀናጅተው ለአንድ ለአውራ ፓርቲ ግንባታ እየሰሩ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ይህ የመንግሥትና የገዢው ፓርቲ ተግባር ምርጫን ያለ አማራጭ እንዲሆነ እያደረገው እንደሆነ ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡

በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ዘመቻ በሚባል ደረጃ እየተካሄደ ያለው አፈናና እስር፤ ከዚህም ባሻገር ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙ ክልከላውና ወከባው ተጠናከሮ መቀጠሉ፤ ገዥው ቡድን የምር ተቃዋሚ ፓርቲ ናቸው ብሎ የሚያስባቸው ፓርቲዎች ለማዳከምና ከምርጫው ውድድር ውጪ ለማድረግ ያለው ቁርጥ አቋም የሚያሳይ ነው። ይህ የገዢው ቡድን አካሄድ በሀገራችን ዴሞክራሲያዊ የሆነ የመድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲመሰረት ፍላጎት እንደሌለው በደንብ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ነፃና ፍትሐዊ በሆነ ምርጫ የሚፈልገውን ፓርቲ እንዲመርጥ እድል ሊጠሰው ሲገባ በሥርዓቱ በእኩል ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ እንዳያካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉበት የሚካሄዱት ምርጫዎች ሁሉ ትርጉም አልባ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ይህ የገዢው ቡድን ሀላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ በተግባር የሚደግፈው ከሠላማዊ ትግል ይልቅ የኃይልና የአመፅ መንገድ እንደሚሆን የተረዳ አይመስልም፤ ይልቁንም በሠላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን ፓርቲዎች ወደ አላስፈላጊ መስመር በመግፋት ሀገራችን ወደ ብጥብጥና ወደ እርስ በእርስ ጦርነት እንድትገባ የሚያደርግ ሁኔታ እየተከተለ ነው የሚገኘው። በሥልጣን ላይ ያሉት ወገኖች ይህ አሳሳቢ ሁኔታ በትክክል እንዳያዩ ጭፍን የሥልጣን ጥም ጋርዷቸዋል፡፡

በቀጣይ ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚደረገው ምርጫም በመንግስት በኩል የመድበለ ፓርቲን ስርዓት ለማጎልበት ምንም ዓይነት ምቹ ሁኔታ እንዳይፈጠር ከአሁኑ የተለያዩ እንቅፋቶችን በመደርደር ላይ ነው። የአንድነት አመራሮችና አባላት በግፍ በማሰር ፓርቲው በምርጫው እንዳይሳተፍ ከፍተኛ የሆነ ጫና እየተደረገ ቢሆንም አንድነት ፓርቲ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሆኖ ህዝቡ እንዲሳተፍ በመቀስቀስና በማበረታታት የተዘጋውን የዴሞክራሲ በር በምርጫ ካርዱ ሊያስከፍት እንደሚችል ከፍተኛ እምነት አለው፡፡

ከሁሉም በላይ ደግሞ እንደከዚህ ቀደሙ ኢህአዴግ ደጋፊዎቼ የሚላቸውን ብቻ በመራጭነት አስመዝግቦ ምርጫ የሚያደርግበት ሁኔታ ማብቃት ይኖርበታል ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ተግባራዊ እንዲሆን በእኛ በኩል ደጋፊዎቻችን በመራጭነት እንዲመዘገቡ ከማበረታት ጀምሮ የህዝብና የፓርቲ ታዛቢ በመሆን የምርጫ ሂደቱን በሙሉ በንቃት እንዲከታተል እንዲሳተፍ የበኩላችንን ጥረት በማድረግ የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ከጅማሮው ህዝባዊ እንዲሆን ትግላችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህ እርምጃም ህዝቡን የስልጣን ባለቤት ለማድረግ ወሳኝ እርምጃ ነው የሚል እምነት አለን፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በገዥው ቡድን መልካም ፍቃድ ወይም በማንኛውም ውጫዊ ተፅዕኖ የፖለቲካ ምህዳሩን እንደማይሰፋ ሊገነዘብ ይገባል። ምህዳሩ የሚሰፋውና ትክክለኛ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ የሚኖረው ህዝቡ በጠቅላላ ከፍርሀት ቆፈን ተላቆ በሙሉ ልብ ለመብቱ ሲቆም፣ ለፓርቲዎች ተገቢው ድጋፍ ሲሰጥ፤ ከፍ ሲልም ወደ ትግሉ ሲቀላቀል መሆኑ መገንዘብ ያስፈልጋል።

በዚህ አጋጣሚ አንድነት ፓርቲ ከህዳር 14 እስከ 20 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚቆይ “የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች” የሚል የሶሻል ሚዲያ ዘመቻ አዘጋጅቷል። በዚህ ዘመቻ ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ለታዋቂ ግለሰቦች፣ ለዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማትና ለልዩ ልዩ የሚዲያ ድርጅቶች በኢንተርኔትና በሶሻል ሚዲያ በእኩል መልዕክት በመላክ በሀገራችን ያሉት የፖለቲካ እስረኞች ሁኔታና አያያዝ በተመለከተ መረጃ በመስጠት ተገቢ የሆነ አያያዝ እንዲኖራቸው፤ ከእስር እንዲፈቱ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚታሉትን ማሰርና ማዋከብ እንዲቆም በመንግስት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለመፍጠር ያለመ ነው። በዚህ ዘመቻ ላይ ሚሊዮኖች ለሚያውቁትና ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል ለሚሉት ሰው ሁሉ መልዕክት በኢተርኔትና በሶሻል ሚዲያ በመላክ ድምፃቸውን ያሰሙ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
ህዳር 11 ቀን 2007 ዓ.ም.
አዲስ አበባ