Sunday, December 7, 2014

አሁንስ ሰዎቹ ጫካ የነበሩም አልመስልህ አለኝ።ጫካ የነበረ እኮ ከአራዊቱም ከእፅዋቱም ሕግ ይማራል

ሕግ ሕግ ሕግ!!! ቅንጣት ታክል ሕግ የማያከብሩ ለማክበርም ፍላጎት የሌላቸው ሰዎች ተሰብስበው መንግስት መሆናቸው እየቆየ ይብሱን የሚያንገበግብ ጉዳይ እየሆነ ነው።የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢህአዴግ/ወያኔዎች የዛሬ 20 ዓመት አፀደቅነው ያሉትን ሕግ እየጠቀሰ ሲሞግታቸው እና ሕግ አክብሩ ሲላቸው ዓመታትን አስቆጠረ።በሕግ ስልጣን ባትይዙም በሕግ ስልጣን  ለሕዝብ አስረክቡ ቢባሉም አልሰሙም።ከሽግግሩ ጊዜ ጀምሮ ብዙዎች ብዙ ሊመክሩ ሞክረዋል። በ''ዞን 9'' ጦማርያን፣በፖለቲከኞቹ አንዱዓለም አራጌ፣በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ቀደም ብሎም በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ዳኛ ብርቱካን ደሜቅሳ እና ሌሎችም ስማቸውን ያልተጠቀሰው ሁሉ ሕግ የማክበርን 'ሀሁ' ለማስተማር ቢጥሩም ሰሚ አጡ።ሁሉም ስለ የሕግ የበላይነት ተናግረዋል፣ፅፈዋል።ሰሚ የለም።ይብሱኑ ከአመት ዓመት ትዕቢት ቤቷን እየሰራች በልቦናቸው ላይ እንደ ሸረሪት ድር እያደራች የሚናገሩት እሬት እሬት የሚል የሚሰሩት የውድቀታቸውን ጥልቀት የሚያሳይ ሆነ።
ሕግን ከመከራ ሰሞኑን በያዝነው በኅዳር ወር መጨረሻ ''የሕገ መንግስቱ ሰነድ የፀደቀበት'' እያሉ በሚወተውቱን ሰሞን የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 30 ''የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት'' በሚለው ርዕስ ስር ቁጥር 1 ስር ''ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በመሆን መሣሪያ ሳይዝ በሰላም የመሰብሰብ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነጻነትና፣ አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው
ሕግ ካላወቅህ ለምን እንደመለስከውም አትናገርም

አዲስ ዘመን እና የፀጥታው መስርያ ቤት


ጉዳያችን
ህዳር 28/2007 ዓም (ደሴምበር 7/2014)

No comments:

Post a Comment