አዲሱ የእኛ አገር ፖለቲካ ሰውን “ኧረ ፖለቲካ ውስጥ አትግባ” የምትባል ፖለቲካ ናት። እንዲህ ለሚሉ ሰዎች ትክክለኛውን ምላሽ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ቆዝሜያለኹ። አሁን እንኳን በዚህች መሸዋወድ የለም። በነገራችን ላይ፤ ፖለቲካ ውስጥ እንዳትገባ የሚነግሩህ ማንነትህን በሚመጥን መልክ ነው።1. ሃይማኖተኛ ከመሰልካቸው፣ ለዚያ የሚስማማ ጥቅስ እና አባባል አዘጋጅተዋል።2. “ምሁር ነገር” ከመሰልካቸው ምሁርነት ከአገራችን ፖለቲካ በላይ በመሆኑ ራስህን በዚያ ውስጥ እንዳታቆሽሽ ያስጠነቅቁሃል።3. ንግድ ላይ ካለህ በፖለቲካ መነካካት ሊያመጣ የሚችለውን መአት ያመለክቱሃል።4. ዳያስጶራ ብትሆን አገር ቤት ያሉ ዘመዶችህ ላይ ሊመጣ ያለውን ችግር ያመለክቱሃል፤ ራስህም ብትሆን እዚያችን አገር ድርሽ እንደማትል ያስጠነቅቁሃል።
ፖለቲካ በተለይ የፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ እንዳልገባህ ስለምታውቀው “እኔ ፖለቲካ ውስጥ አልገባሁም” ብትላቸው ከቻልክ ዝም ማለት፣ ካልቻልክ መንግሥትን መተባበር እንጂ እንኳን ሌላ ነገር “የመንግሥትን ጭካኔ እንኳን መቃወም” መጥፎ ፖለቲካ መሆኑን ይነግሩሃል።የእነርሱ ደጋፊ ብትሆንስ? እሱ ፖለቲካ ውስጥ መግባት አይደለም። ሃይማኖተኛ ከሆንክ መንግሥትን መደገፍ ማለት “እግዚአብሔር የሾመውን ማክበር” ነው ትባላለህ። ምሁር ከሆንክ “የማንም ደጋፊ ሳትሆን ሚዛናዊ ሰው ነህ ማለት ነው፤ ወይም የአገር ልማት ደጋፊ” ትባላለህ። ነጋዴ ከሆንክ “ልማታዊ ነጋዴ” ትባላለህ። ዳያስጶራ ከሆንክ “የኢትዮጵያን ዕድገት የሚናፍቅ፣ አገራችን እኮ አደገች” ባይ ትባላለህ።ስለዚህ አዲሱ ፖለቲካ “ፓለቲካ ውስጥ አትግባ” ናት
No comments:
Post a Comment