Tuesday, December 2, 2014

” በፀሀዩ መንግስታችሁና ሀይማኖታችሁ መካከል አለመጣጣም ቢከሰት የቱን ትመርጣላችሁ?”

በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀና ” የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሠራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል ለምርጫ 2007 የተሻሻለ ጥቅምት 2007″ የሚለውን 23 ገፅ የያዘ ማንዋል አነበብኩት። ሰነዱን ለላካችሁልኝ የዘወትር ተባባሪዎቼ ምስጋና ይድረሳችሁ።
ማንዋሉን አንብቤ ስጨርስ የተዘበራረቀ ስሜት ተሰምቶኛል ። የግል ስሜቴን ለጊዜው በመተው ማን እንዴት ሊጠቀምበት ይችላል የሚለውን ወደ ማሰብ ተሸጋገርኩ። በቅድሚያ ፊትለፊቴ የመጡት በሐገር ቤት በምርጫ ቦርድ ተመዝግበው የሚንቀሳቀሱት ሰማያዊና አንድነት ፓርቲዎች ናቸው። ለጀመሩት ትግል ማጠናከሪያ እንዲሆን ተቀናጅተው አንድ ነገር ማድረግ የሚችሉ ይመስለኛል።

ሰነዱን እንዳየሁት ከሆነ ህገ መንግሥቱን ይጥሳል። የምርጫ ህጉን፣ በ2001 የወጣውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዋጅ አፈር ከድሜ ያስግጣል። ሁለት አብነቶች ብቻ ላንሳ፣
በገፅ 22 ላይ ቀልጣፉነትና ውጤታማነት በሚለው ርእስ ስር፣
“… የዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንቶች ውጤታቸው የሚሞላላቸው ለምርጫው በሚያዘጋጁት የድጋፍ ሀይል ይወሰናል ” ይላል።
በመግቢያው ላይ ደግሞ፣
” በምርጫው ሊፈጠር የሚችለውን የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ሁከት እና ብጥብጥ ለማስቆም በማደራጀት መረጃ ለመጥለፍ አመችነቱ የላቀ እንደሚሆን ታምኖበታል” ይላል።
እነዚህ ሁለት ቁንጵል ሀረጐች ብቻ ” ኢ _ህገመንግስታዊ መመሪያ በማውጣት፣ …የሃገሪቷን ህጐችና አዋጆች በመጳረር፣ የህዝብ ንብረትና ጊዜን ለፓርቲ ስራ ማዋል… ወዘተ ” በሚባሉ ጭብጦች ኢህአዴግን እና ትምህርት ሚኒስቴርን በፍርድ ቤት መክሰስ የሚቻል ይመስለኛል። የካንጋሮ ፍርድቤቱ የሚወስነው ቢታወቅም ። ከዚህ ጐን ለጐን ሰነዱን በመተርጐም ለኤምባሲዎችና አለማቀፍ ተቋማት ማሳወቅ ተገቢ ይመስለኛል።
***
ለሌሎቻችን ከሰነዱ ውስጥ እጅግ የገረመኝ አርፍተ ነገር በገፅ ስድስት የተከተበው ነው። እንዲህ ይላል፣
” ተማሪዎች ከመንግስት ሃይማኖታቸውን እየመረጡ ትምህርታቸውን ትተው ሲኮበልሉ ተመልክተናል።”
እዚህ ላይ ለጋሽ ሃይሌ፣ለሽፈራው ሽጉጤ ፣ ለዶክተር ሽፈራውና ለአለማየሁ ተገኑ አንድ ጥያቄ ማንሳት ፈለኩ። እንዲህ የሚል፣
” በፀሀዩ መንግስታችሁና ሀይማኖታችሁ መካከል አለመጣጣም ቢከሰት የቱን ትመርጣላችሁ?”

Ermias Legess / የ መለስ ትሩፋቶች/


No comments:

Post a Comment